Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 17 November 2012 10:23

አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ 394 ሚሊዮን ብር አተረፈ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ብር ሳይዙ በአዋሽ ካርድ መገበያየት ይቻላል
በግል ባንኮች ምሥረታ ቀዳሚ የሆነው አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ ባለፈው ዓመት ከታክስ በፊት 531 ሚሊዮን ብር ማትረፉን እንዲሁም 394.4 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡ የባንኩ ጠቅላላ ገቢ ከ1.1 ቢሊዮን ብር በላይ፣ የባንኩ የተከፈለ ካፒታል ከ912 ሚሊዮን ብር በላይ መድረሱንና ጠቅላላ ሀብቱም ከ19 ቢሊዮን ብር በላይ መሆኑን ገልጿል፡፡
ተደራሽነቱን ለማስፋት ባደረገው እንቅስቃሴ ባለፈው ዓመት 16 አዳዲስ ቅርንጫፎች በመክፈት በአገሪቱ ያሉትን የቅርንጫፎች ብዛት 88 ማድረሱን ጠቅሶ፤ በዚህ ዓመትም 20 አዳዲስ ቅርንጫፎች ለመክፈት ማቀዱን አስታውቋል፡፡

የቴክኖሎጂና አቅሙን በማሳደግ ለደንበኞቹ ምቹና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ማይሲክ ከተባለ የእንግሊዝ ኩባንያ ጋር የ3.5 ሚሊዮን ዶላር የቴክኖሎጂ ማስፋፊያ (ኮር ባንኪንግ) እየሠራ መሆኑን ጠቅሶ፣ ማስፋፊያው ሲጠናቀቅ ደንበኞች በርካታ ዘመናዊና በአገሪቱ ያልተለመዱ ልዩ አገልግሎቶችን ያገኛሉ ብሏል፡፡ 
አዋሽ ኢንተርናሽናል ከንብ ኢንተርናሽናልና ከሕብረት ጋር በመተባበር ያቋቋሙት ፕሪምየም ስዊች ሶሉሽንስ የመጨረሻ ዝግጅት እየተጠናቀቀ በመሆኑ “አዋሽ ካርድ” ማዘጋጀቱን ጠቅሶ፣ ካርዱን የያዘ ደንበኛ በቅርቡ ወዳገኘው የሦስቱ ባንክ ቅርንጫፍ ጐራ ብሎ ኤቲኤም መሳሪያ በመጠቀም አገልገሎት ማግኘት እንደሚችል ገልጿል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ካርዱን የያዙ ደንበኞች “የአዋሽ ካርድ እንቀበላለን” የሚል ምልክት በተሰቀለባቸው የንግድ ድርጅቶች፣ ጥሬ ገንዘብ ከመያዝ ስጋት ተላቀው በካርዱ መገበያየት እንደሚችሉ አስታውቋል፡፡

Read 3396 times