Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 10 November 2012 16:07

በኦባማ መመረጥ ዝነኞች ተደስተዋል

Written by 
Rate this item
(2 votes)

44ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በድጋሚ በመመረጣቸው ታዋቂ የሆሊውድ እና የመዝናኛው ኢንዱስትሪ ዝነኞች ተደሰቱ፡፡ በሌላ በኩል የኦባማ ተፎካካሪ የነበሩት ሮምኒ ደጋፊ የሆኑት ዶናልድ ትራምፕ፤ “አብዮት ያስፈልገናል” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ዝነኞች በትዊተር ማስታወሻቸው ላይ ደስታቸውን የሚገልፁ ፅሁፎች ያሰፈሩ ሲሆን ኬቲ ፔሪ “ተሳካ”፤ ኮሜድያን ስቲቭ ማርቲን “የኦባማን ድል መታሰቢያ ያደረገ የሻይ ፓርቲ እደግሳለሁ”፤ ሪኪ ማርቲን “እኩልነት ያወጣል”፤ አንጋፋዋ ድምፃዊ ሼር “አሸነፍን አሸነፍን! ታላቁ አምላክ አሸነፍን፤”  ታዋቂዋ የቲቪ ተዋናይት ኢቫ ሎንጎርያ “እንባዬ መጣ በኦባማ አገሬ ወደፊት ትገሰግሳለች፤”  ሌዲ ጋጋ “ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ኮራሁብህ፤ አሜሪካዊነት እጅግ ያኮራል፤ አዎ አዎ አዎ በአሜሪካዊነቴ እኮራለሁ” እያሉ በትዊተር ማስታወሻቸው ፅፈዋል፡፡

በዘንድሮ የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በዲሞክራቱ ባራክ ኦባማና በሪፐብሊካኑ ሚት ሮምኒ መካከል ከፍተኛ ፉክክር የተደረገ ሲሆን የማታ ማታ ኦባማ በድጋሚ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት በመሆን ለመመረጥ  በቅተዋል፡፡ እንደባለፈው ምርጫ ሁሉ በዘንድሮውም ምርጫ የሆሊዉድና የመዝናኛው ኢንዱስትሪ ዝነኞች ለኦባማ ድግፋቸውን እንደሰጡ ታውቋል፡፡ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማን ከደገፉት የሆሊዉድ ዝነኞች መካከል ጆርጅ ኩልኒ፤ ሊዮናርዶ ዲካርፒዮ፤ የዊል ስሚዝ ቤተሰብ፤ ኦፕራ ዊንፍሬይ እንዲሁም በርካታ የቴሌቪዥን እውቅ ተዋናዮችና የቶክሾው አቅራቢዎች ይገኙበታል፡፡ ከድምፃውያን ደግሞ ሌዲ ጋጋ፣ ስኑፕ ዶግ፣ ጀስቲን ቲምበርሌክ፣  ኬቲ ፔሪና ሌሎችም የኦባማ ደጋፊ ነበሩ ተብሏል፡፡ ተፎካካሪያቸውን ሚት ሮምኒን በመደገፍ የፊልም ባለሙያው ክሊንት ኢስትውድና ቻክ ኖሪስ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ሮምኒ እንደ ዶናልድ ትራምፕ ካሉ የአሜሪካ  ባለሃብቶችም ከፍተኛ ድጋፍ አግኝተዋል - በምርጫው ባይቀናቸውም፡፡

Read 3278 times