Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 10 November 2012 15:53

ዳንኤል ክሬግ “ምርጡ ቦንድ” ተባለ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

በመላው ዓለም መታየት ከጀመረ ሁለት ሳምንት ባለፈው 23ኛው የጀምስ ቦንድ ፊልም “ስካይ ፎልስ” ላይ የተወነው ዳንኤል ክሬግ፤ በትርፋማነቱ “ምርጡ ቦንድ” በሚል ተደነቀ፡፡በ2006 እ.ኤ.አ በተወነው “ካሲኖ ሮያሌ” እና በ2008 እ.ኤ.አ በሰራው “ኳንታም ኦፍ ሶላስ” በተባሉት 21ኛው እና 22ኛው የጀምስ ቦንድ ፊልሞች 1.22 ቢሊዮን ዶላር ገቢ በማስገባት የቦንድን ፊልም ከሰሩ ስድስት ተዋናዮች መካከል ዳንኤል ክሬግ የመሪነት ደረጃውን ሊይዝ በቅቷል፡፡ አዲሱ የቦንድ ፊልም ላይ ተዋናይ “ከት ትሮት ራዘር” የተባለውን ፂም መላጫ በመጠቀም ያሳየው ትወና የምርቱን ገበያ በ405 ፐርሰንት ማሳደጉን የገለፀው ዴይሊ ቴሌግራፍ፤ ከ60 እስከ 300 ዶላር ዋጋ ያለው ፂም መላጫ ተፈላጊነቱ በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል ብሏል፡፡

የቀድሞው የቦንድ ፊልም ተዋናይ ሮጀር ሙር፤ በፊልሙ “ምርጡ ቦንድ” ዳንኤል ክሬግ እንደሆነ የተናገረ ሲሆን ዳንኤል ክሬግ በበኩሉ፤ ምናልባት አንድ ሁለት ተጨማሪ የቦንድ ፊልሞችን ሰርቶ ገፀባህርይውን መተው እንደሚፈለግ ገልጿል፡፡በእንግሊዛዊው ደራሲ ኢያን ፍሌሚንግ የስለላ መፅሃፍ ላይ የተሰሩት የጀምስ ቦንድ ፊልሞች የወርቅ ኢዮቤልዩ በመላው ዓለም ከወር በፊት የተከበረ ሲሆን የመጀመርያው የጀምስ ቦንድ ፊልም “ዶክተር ኖ” በሚል ርእስ መሰራቱ ይታወቃል፡፡

Read 2763 times