Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 10 November 2012 15:50

የሄሊ ቤሪ ትወና ተደነቀ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ወደ ትወና ከገባች በኋላም በሆሊዉድ በአንድ ፊልም እስከ 10 ሚሊዮን ዶላር ከሚከፈላቸው ተዋናዮች አንዷ ለመሆን የበቃች ስኬታማ ተዋናይት ናት፡፡ ሄሊ ቤሪ በ2001 እ.ኤ.አ በሰራችው “ሞንስተርስ ቦል” የተሰኘ ፊልም በምርጥ ተዋናይነት ኦስካር ተሸልማለች፡፡ዘንድሮ ከአዲስ ፍቅረኛዋ ከፈረንሳዊው ኦሊቨር ማርቲኔዝ ጋር  ቀለበት ያሰረችው ሄሊ ቤሪ፤ በዚሁ ዓመት ከዚሁ ፍቅረኛዋ ጋር ትዳር ለመመስረት የነበራት እቅድ ከሽፎባታል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ከሦስተኛ ባሏ ገብሬል አውብሪ ጋር የጀመረችውን የፍርድ ቤት ክርክር ባለማጠናቀቋ እንደሆነ ታውቋል፡፡ በ40ዎቹ እድሜ መጀመሪያ  ላይ የልጅ እናት መሆኗን የወደደችው  ሄሊ ቤሪ፤ ሌላ ልጅ የመውለድ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት ሰሞኑን ተናግራለች፡፡ “ከአራት ዓመት ልጄ ከናሃላ ጋር ማታ ማታ ሌላ ልጅ እንዲሰጠኝ አምላክን በፀሎት እንማፀናለን” ብላለች -  ለ”ፒፕል” መፅሄት በሰጠችው ቃለ ምልልስ፡፡

የ46 ዓመቷ ሄሊ ቤሪ፤ ሥራ የጀመረችው በፋሽን ሞዴልነት ሲሆን በአሜሪካ የቁንጅና ውድድሮች ላይ በመሳተፍም ትታወቃለች፡፡ ከቶም ሃንክስ ጋር  “ክላውድ አትላስ” በተባለው ፊልም ላይ የተወነችው ሄሊ ቤሪ፤ ሦስት የተለያዩ  ገፀባህርያትን ወክላ በመጫወት ድንቅ የአተዋወን ብቃቷን እንዳሳየች ተገለፀ፡፡ አርቲስቷ ለዚህም በየቀኑ አራት ሰዓት ተኩል የሚፈጅ ሜክአፕ ትሰራ እንደነበር የጠቀሰው “ሆሊውድ ሪፖርተር”፤ ትጋቷን አድንቋል፡፡ ይህቺ ጥቁር አሜሪካዊት ተዋናይ በ1993 እ.ኤ.አ “ሚስ ዳውት ፋየር” የተሰኘው ፊልም ላይ ከሰራው ሮቢን ዊልያምስ ቀጥሎ ብዙ ሜክአፕ በመስራት አዲስ ክብረወሰን አስመዝግባለች፡፡ ታዋቂ የፊልም ሃያስያንም በ”ክላውድ አትላስ” ፊልም ላይ ሶስት ገፀባህርያትን ወክላ ምርጥ አተዋወን አሳይታለች ሲሉ አወድሰዋታል፡፡

Read 3002 times