Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 10 November 2012 15:03

ዳንኤል ዴይ ሊውስ “የፕላኔታችን ምርጡ ተዋናይ” ተባለ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ዳንኤል ዴይ ሊውስ በመሪ ተዋናይነት የሚሰራበትና ከሳምንት በኋላ በመላው ዓለም መታየት የሚጀምረውን ‹‹ሊንከን››  ፊልምን ያዘጋጀው ዕውቁ የፊልም ዳይሬክተር ስቲቨን ስፒልበርግ ነው፡፡ ፊልሙ ዶሪስ ኪርኔስ የተባለ ደራሲ ‹‹ቲም ኦፍ ራይቫልስ፡ ዘ ፖለቲካል ጂኒዬስ ኦፍ አብርሃም ሊንከን›› በሚል ከፃፈው የታሪክ መፅሃፍ በተወሰደ መነሻ ሃሳብ የተሰራ ነው፡፡ላለፉት ሰላሳ ዓመታት በፊልም ተዋናይነት የዘለቀው የሁለት ጊዜ ኦስካር ተሸላሚው ዳንኤል ዴይ ሊውስ፤ “በህይወት ያለ የፕላኔታችን ምርጥ ተዋናይ” ተብሎ በታይም መፅሄት ተመረጠ፡፡ ተዋናዩ ምንም እንኳን በመስኩ በቆየባቸው ዓመታት ከ20 ያልበለጡ ፊልሞችን ቢሰራም በእነዚሁ ጥቂት ስራዎቹ ከፍተኛ ተሰጥኦውን አስመስክሯል ሲል አድንቆታል - ታይም፡፡

በሙሉ ስሙ ዳንኤል ማይክል ብሌክ ዴይ ሊውስ ተብሎ የሚጠራው ተዋናዩ፤ የብሪትሽና የአይሪሽ ጣምራ ዜግነት ያለው ሲሆን በየአምስት ዓመቱ አንድ ዩተወዳጅ ፊልም መስራትን ልምዱ አድርጐታል ተብሏል፡፡ ዳንኤል ዴይ ሊውስ  ከተወነባቸው ፊልሞች መካከል ‹‹ዘ ላስት ኦፍ ዘ ሞሂካንስ›› ፣ ‹‹ ዘ ቦክሰር›› ፣ ‹‹ጋንግስ ኦፍ ኒውዮርክ›› ፣ ‹‹ዜር ዊል ቢ ብለድ››፣ ‹‹ናይን›› እንዲሁም ዘንድሮ የሰራው ‹ሊንከን›› ይጠቀሳሉ፡፡ ለታይም መፅሄት አስተያየት የሰጡ የፊልም ሃያሲያን፤  ዳንኤል ዴይ ሊውስ ‹‹ሊንከን›› በተባለው አዲስ ፊልም 16ኛውን የአሜሪካ ፕሬዝዳንት አብርሃም ሊንከን ፍፁም በመመሳሰል ያሳየው የትወና ብቃት ለዘንድሮው የኦስካር ሽልማት ግንባር ቀደም ተፎካካሪ እንደሚያደርገው መስክረዋል፡፡ በ1989 እ.ኤ.አ በሰራው ‹‹ማይ ሌፍት ፉት››  እና በ2008 በተወነው ‹‹ዜር ዊ ልቢ ብለድ›› የኦስካር ሽልማትን በምርጥ ተዋናይነት ያሸነፈው ዳንኤል፤ ዘንድሮ ኦስካርን ለሶስተኛ ጊዜ ከወሰደ በሆሊውድ ታሪክ የመጀመርያው ተዋናይ በመሆን ትልቅ ክብር ይቀዳጃል፡፡ እንደ ዳንኤል ዴይ ሊውስ ሁለቴ የኦስካር ሽልማትን በምርጥ ተዋናይነት የወሰዱት ዘጠኝ  ተዋናዮች ብቻ ናቸው -  ማርሎን ብራንዶ፣  ደስቲን ሆፍማን፣  ጃክ ኒኮልሰን፣  ሺን ፔን እና ቶም ሃንክስ፡፡ ለኦስካር በሚደረገው ፉክክር የዳንኤል ዴይ ሊውስ የቅርብ ተፎካካሪዎች እንደሚሆኑ ከተገመቱት መካከል “ዘ ማስተር” በተባለው ፊልም ላይ የተወነው ጆአኪን ፎኒክስ እና “ፍላይት 4” ላይ የሰራው ዴንዝል ዋሽንግተን ይገኙበታል፡፡ለሶስተኛ ኦስካር እየተጠበቀ ነው

Read 2519 times