Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 10 November 2012 15:14

ሆረር ፊልም መመልከት ክብደት ይቀንሳል

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ይህ በእንዲህ እንዳለ በሰሜን አሜሪካ ባለፈው ሰሞን ለእይታ የበቁ እና ታላላቅ ተዋናዮችን ያሳተፉ ፊልሞች ብዙም ገበያው እንዳልቀናቸው የቦክስኦፊስሞጆ ሪፖርት አመልክቷል፡፡ ለገበያው መቀዛቀዝ በመላው አሜሪካ የተከሰተው የሃሪኬን ሳንዲ የተፈጥሮ አደጋ ምክንያት እንደሆነ ታውቋል፡፡ ቤን አፍሌክ ዲያሬክት ያደረገው “አርጎ” የተሰኘ ፊልም 12.1 ሚሊዮን ዶላር በማስገባት የሰሜን አሜሪካን ገበያ እንደሚመራ የገለፀው ቦክስ ኦፊስ ሞጆ ፤ ቶም ሃንክስ የተወነበት “ክላውድ አትላስ” 9.6 ሚሊዮን ዶላር በማስገባት በሁለተኛነት እንደሚከተል አስታውቋል፡፡ ከሁለት ሳምንት በፊት በመላው ዓለም በ25 አገራት  ለእይታ የበቃው የጀምስ ቦንድ 23ኛ ፊልም “ስካይ ፎልስ” በ80.6 ሚ. ዶላር የቦክስ ኦፊስን የዓለም የገቢ ደረጃ እንደሚመራ ታውቋል፡፡የሰውነት ክብደታቸውን ለመቀነስ የሚሹ ፊልም አፍቃሪዎች ከሌሎች የፊልም ዘውጐች ይልቅ ድንጋጤና ፍርሃት የሚለቁ ሆረር ፊልሞችን እንዲመለከቱ ጥናቱ መክሯል፡፡

በቅቤ የተለወሰ ፈንዲሻ እየበሉ ፊልሙን መመልከት ግን አይመከርም፡፡ የእንግሊዝ የዌስትሚኒስቴር ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች፤ ሆረር ፊልም በሚመለከቱ ሰዎች ላይ ባደረጉት ጥናት ነው ፊልሞቹ በሰውነት ውስጥ ያለን  ካሎሪ በማቃጠል የሰውነት ክብደት እንደሚቀንሱ ያረጋገጡት፡፡ ተማራማሪዎቹ ፊልም ተመልካቾች የተለያዩ ሆረር ፊልሞችን ሲመለከቱ የልብ ምታቸውን፣ የኦክስጂን አወሳሰዳቸውንና፣ የሚያስወጡትን የካርቦንዳይኦክሳይድ መጠን በመለካት ጥናቱን እንደሰሩ እንዳካሄዱ የዘገበው “ቴሌግራፍ”፤ የሚቃጠለውን የካሎሪ መጠንም ለክተዋል ብሏል፡፡ ካሎሪ ያቃጥላሉ ከተባሉት ሆረር ፊልሞች መካከል “Jaws”፣ “The Exorcist”፣ “Alien” እና  “Soul” ከሁለተኛ ደረጃ ይዘዋል፡፡  በ1980 እ.ኤ.አ የተሰራው ስነልቦናዊ ይዘት ያለው “ዘ ሻይኒንግ” የተሰኘ ሆረር ፊልም 180 ካሎሪን በማቃጠል በጥናቱ የመጀመርያ ደረጃ ተሰጥቶታል፡፡ ፊልሙ በስቴፈን ኪንግ መፅሃፍ ላይ ተመስርቶ የተሰራና በስታሊን ኩብሪክ ዲያሬክት የተደረገ እንዲሁም የኦስካር ተሸላሚው ጃክ ኒኮልሰን የተወነበት ነው፡፡ ሰዎች ሆረር ፊልሞችን ሲያዩ የኦክሲጅን አወሳሰዳቸው እንደሚጨምር፤ የልብ ምታቸው እንደሚፈጥንና የካርቦንዳይ ኦክሳይድ አወጣጣቸው እንደሚበዛ የገለፁት ተመራማሪዎቹ፤ በዚህም የተነሳ የደም ዝውውር፣ የስኳር አጠቃቀም እና የኢንዛይሞች አረጫጨት ከመደበኛው ሶስት እጥፍ እንደሚጨምር አረጋግጠዋል፡፡ ሆረር ፊልሞችን መመልከት ሰውነት ውስጥ ተከማችቶ የሚገኝን ቅባት በማቃጠል ክብደት እንደሚቀንስ በጥናት መረጋገጡን “ቴሌግራፍ” ጋዜጣ ዘገበ፡፡ ጥናቱ እንደሚያሳየው አንድ ግለሰብ የ90 ደቂቃ ርዝማኔ ያለውን ሆረር ፊልም በመመልከት እስከ 200 ካሎሪ ያህል ቅባት ከሰውነቱ ማቃጠል ይችላል፡፡

Read 5243 times