Print this page
Saturday, 10 November 2012 14:21

አዲስ አበባ Featured

Written by  ብርሃኑ ሰሙ
Rate this item
(4 votes)

በአዲስ አበባ ከተማ በግልፅ ለሚታዩ ብዙ የልማት ሥራዎች የሚሰጥ አድናቆትና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ በመጣው የኑሮ ውድነት ላይ የሚቀርበው ቅሬታ እርስ በእርስ እየተጋጨ ልዩነቱ አንድ ችግር ሆኖ በሚታይበት ወቅት ነው የከተማዋ ምሥረታ 125ኛ ዓመት በመከበር ላይ ያለው፡፡ በዓሉ ለአንድ ዓመት በተከታታይ እንዲከበር በ2004 ዓ.ም ከተወሰነ በኋላ ወደ ማጠናቀቂያው ሲቃረብ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ያልተጠበቀ ህልፈት፤ በተመሳሳይ የኢዮቤልዩ በዓላት እንደታየው፤ ሀዘን፣ ጭንቀትና ስጋትን አስከትሎ ነበር - እንደተፈራው ግን አልሆነም፡፡ ከ125ኛ ዓመት ማጠናቀቂያ ዝግጅቶች አንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን የሚዘክር የሩጫ ውድድር ባለፈው እሁድ ተካሂዷል፡፡ በአምስቱ የኢዮቤልዩ ዓመታት ዋዜማና ማግስት የተስተዋሉት ችግሮች ግን አስደማሚ ናቸው፡፡ 125ኛ ኢዮቤልዩ ዘመኑ ደርግ ስልጣን የያዘበት 12ኛ ዓመት  ነው፡፡

ብዙ ሰዎች የደርግ አገዛዝ ዘመን የሚታሰባቸው ከእንግልት መከራና ሰቆቃው ጋር ነው፡፡ የአዲስ አበባ ከተማን ምሥረታ 100ኛ ኢዮቤልዩ ያከበረው የደርግ መንግሥት፤ ለከተማዋ ታሪክ ቋሚ ሆነው ሊቀሩ የቻሉ ተግባራትን አከናውኖበታል፡፡ እንጦጦ ማርያም ቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ የሚገኘውን ሙዚየም ማቋቋሙ አንዱ መልካም ተግባሩ ሲሆን በመስቀል አደባባይ በራስ ብሩ መኖሪያ ቤት የአዲስ አበባ ከተማን የመቶ ዓመት ታሪክ የሚያስቃኘው ሙዚየም ሌላኛው ትልቅ ተግባሩ ነው፡፡ 100ኛ ኢዮቤልዩ የታህሳስ ግርግር በመባል የሚታወቀው የ1953 ዓ.ምቱ መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ከተከናወነ ከአንድ ዓመት በኋላ ነበር የአዲስ አበባ ከተማ ምሥረታ 75ኛ ዓመት የሞላው፡፡ ይህም የኢዮቤልዩ ዘመን በከተማዋ ታሪክ ከችግር፣ ከጭንቀትና  ከስጋት ጋር የሚታወስ ነው፡፡ በ1948 ዓ.ም አፄ ኃይለሥላሴ ዙፋን የደፉበትን 25ኛ የወርቅ ኢዮቤልዩ በደመቀ ሁኔታ አክብረዋል፡፡ በ1958 ዓ.ም ጠላት የተባረረበት 25ኛ ዓመትም ደማቅ በሚባል ሁኔታ ነበር የተከበረው፡፡ በዚህ ወቅት ብሔራዊ ባንክ ለመታሰቢያ እንዲሆን የወርቅ ሳንቲም ሁሉ አሳትሟል፡፡ በሁለቱ ዘመን መሐል በሚገኘው በ1954 ዓ.ም ለአዲስ አበባ 75ኛ ኢዮቤልዩስ ምን ተደረገ? 75ኛ ኢዮቤልዩ ይህም የችግር፣ የሰቆቃና የመከራ ዘመን ነበር፡፡ በህዳር ወር 1929 ዓ.ም አዲስ አበባ የተመሠረተችበት 50ኛ ዓመት ሲሆናት ፋሽስቱ ጣሊያን ኢትዮጵያን ወርሮ፤ ንጉሠ ነገሥቱ ወደ እንግሊዝ ተሰደው፤ ለአገር፣ ለሕዝብና ለባንዲራ ክብርና ነፃነት ለመታገል የቆረጡ አርበኞች በየጫካው “ዱር ቤቴ” ብለው የዘመቱበት ዘመን ነው፡፡ የ30ሺህ ሰዎች ሕይወት በአሰቃቂ ሁኔታ ያለፈበት የየካቲት 29 ቀን 1929 ዓ.ም ጭፍጨፋም በአዲስ አበባ ከተማ ምሥረታ 50ኛ ዓመት ላይ የተከሰተ ነው፡፡ 50ኛ ኢዮቤልዩ  አፄ ምኒልክን ለስድስት ዓመታት ያህል ያሰቃየው በሽታም ታህሳስ 3 ቀን 1906 ዓ.ም ሕይወታቸውን በመውሰድ ተጠናቀቀ፡፡ የአዲስ አበባ ምሥረታ 25ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዩ በዓል ዋዜማና ማግስት እንዲህ በጭንቀትና ችግር የታጠረ ነበር፡፡ “አፄ ምኒልክ እና የኢትዮጵያ አንድነት” በሚል ርዕስ በተክለጽድቅ መኩሪያ ተዘጋጅቶ በ1983 ዓ.ም በታተመው መጽሐፍ ውስጥ እንደተመለከተው፤ ራስ ተሰማ ናደውም ሚያዝያ 3 ቀን 1903 ዓ.ም ሞቱ፡፡ ሞግዚታቸው ሲሞቱ የ15 ዓመት ልጅ የነበሩት ልጅ ኢያሱ፤ ዕድሜያቸው ላልተገባ ተግባር ሲዳርጋቸው በኋላ ለውድቀታቸው ምክንያት የሆኑ ተግባራት ተፈፀሙ፡፡የልጅ ኢያሱ ሞግዚት እንዲሆኑም ራስ ተሰማ ናደው ተሾሙ፡፡ በእቴጌ ጣይቱና በራስ ተሰማ መሐል ስልጣንን ማዕከል ያደረገው ግጭት እየተካረረ በመሄዱ፣ ሌሎች የዘመኑ ባለስልጣናት መጋቢት 11 ቀን 1902 ዓ.ም በፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ መኖሪያ ቤት እቴጌ ጣይቱ ከአስተዳደር ውጭ ሆነው ተቀምጠው ምኒልክን ያስታሙ ተብሎ ተወሰነ፡፡ ዘመኑ 1904 ዓ.ም ነው፡፡ ከዚህ ዓመት ሁለት ዓመት ቀደም ብሎ የአፄ ምኒልክ ጤንነት አስጊ ሁኔታ ላይ ስለደረሰ ግንቦት 10 ቀን 1901 ዓ.ም ንጉሱ አልጋ ወራሻቸው ልጅ ኢያሱ መሆኑን ለባለስልጣኖቻቸው፣ ለሕዝብና ለውጭ መንግሥታት ወኪሎች አሳወቁ፡፡ 25ኛ ኢዮቤልዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል በ1993 ዓ.ም ባሳተመው የአማርኛ መዝገበ ቃላት ውስጥ “ኢዮቤልዩ” የሚለውን ቃል “አንድን ትልቅ ድርጊት ወይም ሁኔታ ለማስታወስ በየሃያ አምስት ዓመት የሚከበር በአል፡፡ የወርቅ ኢዮቤልዩ /የብር ኢዮቤልዩ” በሚል ይተረጉመዋል፡፡ አዲስ አበባ የብር፣ የወርቅና የአልማዝ ኢዮቤልዩ ዓመቷ ላይ በደረሰችበት ወቅትስ ምን መልክ ነበራት?የመጨረሻና የማጠናቀቂያ ዝግጅቶች በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት እንደሚቀርቡ ሞቅ ያሉ ዜናና ማስታወቂያዎች ያመለክታሉ፡፡ ለመሆኑ አዲስ አበባ ከተማ የኢዮቤልዩ በዓሏን ማክበር መቼ ጀመረች? 25ኛ፣ 50ኛ፣ 75ኛ፣ የምሥረታ ዓመቷ ተከብሯል ወይ? ለዚህ ጥያቄ የተፃፈ ነገር ማንበቤን ወይም የተሰጡ ምስክርነቶችን መስማቴን አላስታውስም፡፡ በዓላቱ ተከብረው ከነበር በምንና እንዴት እንደተከበረ የሚያውቁ ቢነግሩን እንማርበታለን፡፡ አዲስ አበባ ከተማ የተመሠረተችበትን 125ኛ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ፣ ባለፈው አንድ ዓመት የተለያዩ ተግባራት ሲከናወኑ ቆይቷል፡፡ ከ1879 ዓ.ም በፊት አዲስ አበባን የማዕከላዊ መንግሥታቸው መቀመጫ ለማድረግ የጠሩት ነገሥታት ሙከራ ማድረጋቸውን የሚያመላክቱ የካ ዋሻ ሚካኤል መሰል ሥራዎች ትተው ሲያልፉ “ይህ ቦታ የልጅ ልጄ ይነግስበታል” የሚል ትንቢት ከተናገሩትና ከንጉሥ ሣህለሥላሴ ቤተሰብ የተገኙት አፄ ምኒልክና ባለቤታቸው የብዙዎችን ምኞት እውን ማድረግ ቻሉ፡፡ ከአፄ ምኒልክና ከእቴጌ ጣይቱ በፊት በዛሬዋ አዲስ አበባ ላይ በመንቀሳቀስ ቀዳሚ መሆናቸውን የሚያመለክት የአፄ ምኒልክ አያት ሳህለሥላሴ ሥራዎች አሉ፡፡ አሁን በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ አብያ ክርስቲያናት አንዱ የሆነው፣ በ1816 ዓ.ም በንጉሥ ሣህለሥላሴ የተሰራው ቀራኒዮ መድሐኒዓለም ቤተክርስቲያን አንዱ ማሳያ ነው፡፡ ከንጉሥ አብርሐ እና አጽብሐ በኋላ አዲስ አበባን የማዕከላዊ መንግሥታቸው መቀመጫ ለማድረግ ጥረት ያደረጉ ነገሥታት ነበሩ፡፡ የበላይ ግደይ መጽሐፍ ንጉሥ ዳዊት በ15ኛው ክፍለ ዘመን እንጦጦ ተራራ ላይ ከተማ መስርተው ስለመቀመጣቸው በብራና ጽሑፍ ሰፍሮ እንደሚገኝ ያመለክታል፡፡ የግራኝ አህመድ ወረራ እንቅፋት ባይሆንበት ንጉሥ ልብነድንግልም አዲስ አበባን የመንግሥቱ መቀመጫ የማድረግ እቅድ እንደነበረው “የኢትዮጵያ ታሪክ በ16ኛው ክፍለ ዘመን” በሚል ርዕስ በይልማ ደሬሳ ተዘጋጅቶ በ1959 ዓ.ም በታተመው መጽሐፍ ውስጥ ሰፍሯል፡፡ “ሁለቱ ወንድማማቾች አብርሃና አጽብሐ በንጉሠ ነገሥትነት ደረጃ እኩል ስልጣን ኖሮዋቸው እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ በመሆን ኢትዮጵያን ባንድነት ያስተድድሩ እንደነበረ ያንድነቱ ሥራቸው ያረጋግጣል፡፡ ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ግዛት በጣም ሰፊ ስለሆነ ለሁልጊዜውም መንበረ መንግስታቸውን አክሱም ከተማ አድርገው ሕዝባቸውን በቅርብ እየተገኙ ለማስተዳደር ስለተቸገሩ፣ አገሩን ለሁለት ተካፍለው ለማስተዳደር ተገደዱ፡፡ በዚህም መሰረት ንጉሥ ኢዛና (አብርሃ) አክሱም ላይ ተቀምጦ ሰሜንና ምሥራቁን እስከ የመን ድረስ ሲያስተድድር ንጉሥ አጽብሃ ደግሞ በሸዋ ውስጥ በየረር ጋራ ላይ ቤተመንግሥቱን መሥርቶ ደቡብ፣ ምዕራብና ምሥራቅ ኢትዮጵያን ያስተዳድር ነበር፡፡”አዲስ አበባ፤ ከአፄ ምኒልክና እቴጌ ጣይቱ ጋር የተያያዙ የምሥረታ ታሪኳ እውን ከመሆኑ ብዙ ዓመታት በፊት ኢትዮጵያን ያስተዳደሩ መንግሥታት መቀመጫቸው እንድትሆን ከመመኘት ባለፈ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ያደርጉ ነበሩ፡፡ ቀዳሚዎቹ አክሱማዊያኑ ወንድማማቾች አብርሐ እና አጽብሐ ናቸው፡፡ በ4ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያን የመሩት ሁለቱ ወንድማማቾች በአዲስ አበባ የሚገኘው የካ ዋሻ ሚካኤል ቤተክርስቲያንን ያሰሩበት ምክንያት ምን እንደነበር “አዲስ አበባ ያብባል ገና” በሚል ርዕስ በበላይ ግደይ ተዘጋጅቶ በ1997 ዓ.ም በታተመው መጽሐፍ ውስጥ በዚህ መልኩ ቀርቧል፡፡ ከአክሱማዊያን እስከ 125ተኛ ኢዮቤልዩ

Read 5693 times Last modified on Saturday, 10 November 2012 17:09