Saturday, 10 November 2012 14:18

የእኛ ሰዎች በየመን

Written by  አልአዛር ኬ
Rate this item
(2 votes)

ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በተከታታይ የሚቀርቡት በየመን የሚገኙ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን የፍዳና የመከራ ታሪኮች ዋነኛ አላማም ይሄው ብቻ ነው፡፡ ተገቢውና ትክከለኛው መረጃ ቢኖራቸው ኖሮ በየአመቱ በዚህን ያህል ብዛት ወደ የመን መሰደድ መቻላቸው ያጠራጥራል፡፡ እናም በየመን የሚገኙ ስደተኛ ወገኖቻችንን ትክክለኛ ህይወትና የቀን ተቀን የኑሮ ሁኔታ ማሳወቅ ወደ የመን ለመሰደድ ልባቸው ያቆበቆበ ዜጐቻችን እግራቸውን ለስደት ከማንሳታቸው በፊት አንዴ ሳይሆን ሁለትና ሶስት ጊዜ በጥሞና እንደያስቡና ተነግሮ ከማያልቅ አካላዊና ስነልቦናዊ የምድር ላይ ፍዳ ራሳቸውን እንዲያድኑ ሊያግዛቸው ይችላል፡፡ ስለእነዚህ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በእርግጠኝነት መናገር የሚቻለው አንድ ነገር ነው፡፡ ከእነሱ በፊት ወደ የመን የተሰደዱት ኢትዮጵያውያን ወገኖቻቸው በየመን እንዴት ያለ ህይወት እንደገጠማቸውና እንዴት ያለ እጅግ አስከፊ የምድር ላይ ፍዳ እየተቀበሉ እንዳሉ አንድም ጭራሹኑ አላወቁም አሊያም ያላቸው መረጃ በጣም የተሳሳተ መሆኑን ነው፡፡ ስደቱ አሁንም አላቆመም፡፡

በያዝነው የ2012 ዓ.ም የመጀመያ አምስት ወራት ብቻ ሃምሳ አንድ ሺ አራት መቶ አርባ አንድ ኢትዮጵያውያን በህገወጥ መንገድ ወደ የመን በስደተኝነት ገብተዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ ወደ የመን የገቡት በህገወጥ መንገድ ነው፡፡ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን በየአመቱ ወደ የመን የሚሰደዱትን ኢትዮጵያውያን ብዛት አስመልክቶ ባለፈው ወር ባወጣው ይፋ መረጃ መሠረት፤ ከ2006 ዓ.ም እስከያዝነው 2012 ዓ.ም የጁን ወር ድረስ ብቻ ሁለት መቶ ሠላሳ ሺ ኢትዮጵያውያን ወደ የመን በስደተኝነት ገብተዋል፡፡ ከፈርጀ ብዙው እርዳታ ምናልባትም ከዋነኞቹ አንዱ በየመን የሚገኙ ስደተኛ ወገኖቻችን የሚገፉትን የገሃነም ውስጥ ህይወት ለተቀረው ህዝብ ማሳወቅና ተገቢውን ግንዛቤ እንዲጨብጥ ማድረግ ነው፡፡ የችግራቸውና የፈተናቸው መጠኑና ጥልቀቱ ዲካ የለሽ ነው፡፡ እናም የእያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ ጥረትና ዙሪያ መለስ ርብርብ ይጠይቃል፡፡ በየመን የሚገኙ ስደተኛ ወገኖቻችንን ካሉበት አስከፊ ሁኔታ ለመታደግ የመንግስትና የአለም አቀፉ እርዳታ ድርጅቶች ጥረትና እገዛ ብቻ ከቶውንም በቂ ሊሆን አይችልም፡፡ ይህ አይነቱ ዜና በእርግጥ ዛሬም ቢሆን ጨርሶ አልቀረም፡፡ አሁን አሁን ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን በሚመለከት ከወደ የመን የሚሠራጨው ዜና ግን በአይነቱም ሆነ በይዘቱ ከሌላው ጊዜ በእጅጉ የተለየና በድንጋጤ ልብ ማቆም የሚችል ነው፡፡ ባለፉት ጥቂት ወራቶች ስለ እነዚህ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን ተጓዦች ስንሰማው የነበረው  እዚህ ግባ የማይባል ከርካሳ ጀልባ በጉዞ ላይ እንዳለ ተስብሮ አሊያም ተገልብጦ በአስርና አልፎ አልፎም በመቶ የሚቆጠሩት የባህር ውሃ ሲሳይ ሆነው የማለቃቸውን ዜና ነበር፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በልባቸው ያቀዱትን ምናልባትም ለዘመናት ሲያልሙት የነበረውን የተሻለ ህይወት እውን ለማድረግ፣ እንደሌሎች ሀገራት ሁሉ ወደ የመንም በስደት ሲጓዙ ኖረዋል፡፡ የተሻለ ህይወት ፍለጋ በየክፍለ አለማቱ በስደት እንደሚባዝኑት የአለም ሀገራት ዜጐች ሁሉ ኢትዮጵያውያንም ወደ ተለያዩ የአለማችን ሀገራት ቤት ልጄን፣ ጨርቄን ማቄን ሳይሉ ለስደት ይጓዛሉ፡፡ ነገሩ እንዲህ ከሆነ ቀጥሎ የሚቀርበው ጥያቄ ወደ የመን መሠደዱ ከሌላው ስደት የተለየ የሚያደርገው ምንድን የሚለው ነው፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ መልሱ ቀላል ነው፡፡ የመንን የተለየ የሚያደርጋት በአሁኑ ወቅት  ለኢትዮጵያውያን ስደተኞች ገሀነም ስለሆነችና የበርካታ ስደተኛ ኢትዮጵያውያንን ህይወት ለመግለጽ በሚያስቸግር መጠንና ስቃይ እየቀጠፈች በመሆኗ ብቻ ነው፡፡ እነዚህ ከየመን ስደት የተመለሱ ኢትዮጵያውያን ግን ጠቅላላውን ታሪክ ጨርሶ አይወክሉም፡፡ እነሱ የስደተኝነትን እጅግ አስከፊ ህይወትና የስደተኞች መጠን ጥቂት እራፊዎች ብቻ ናቸው፡፡ ባለፈው ጊዜ ወደ ሀገራቸው የተመለሱት ኢትዮጵያውያን የተሻለ ህይወትን ፍለጋ የተሰደዱትም ወደዚችው የመን ነበር፡፡ እናም ሰዎች ይሰደዳሉ፡፡ ወደ አሜሪካና አውሮፓ ብቻ ሳይሆን ቀይ ባህርን ተሻግሮ ወደምትገኘው የመንም ጭምር፡፡  የገጠማቸው የተወሳሠበ የኢኮኖሚ ምስቅልቅል የዜጐቻቸውን ህይወት ከፍ ያለ ፈተና ላይ ጥሎታል፡፡ እናም በእነዚህ ሀገራት ውስጥ በስደተኝነት መኖርም ሆነ ስደተኛ ሆኖ መሄድ ለማንኛውም ሰው የሚመከር ነገር አይደለም፡፡ የሰው ልጆች የተሻለ ህይወት የመኖር ፍላጐት ግን በምክር የሚገታ ዓይነት አይደለም፡፡  በሚሊዮን የሚቆጠሩ እነኝሁ የአለማችን ድሆች ወደ እነዚህ ሀገራት በመሠደድ የዘወትር ምኞትና ህልማቸውን እውን ማድረግ ችለዋል፡፡ አሁን የያዝነው ወቅት ግን ለእነዚህ ባለጠጋ ሀገራት የተመቸ አይደለም፡፡በኢኮኖሚያቸው ብልጽግና የተነሳ እጅግ ባለጠጋ የሆኑት የአሜሪካና የአውሮፓ ሀገራት በመላው አለም ለሚገኙ ምንዱባን የተሻለ ህይወት የዘወትር ምኞትና ህልም ናቸው፡፡የሰው ልጆች ስደት እንዲህ ያሉ መልካም ጐኖች እንዳለው ሁሉ መጥፎና አስቸጋሪ ጐኖችም እንዳሉት በግልጽ የታወቀ ነገር ነው፡፡ በዘር፣ በሀይማኖትና በቀለም ልዩነት ለበርካታ ችግሮችና ከፍተኛ ስቃይ ከተዳረጉት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ግንባር ቀደሞቹ በተለያዩ ሀገራት በስደተኝነት የሚኖሩት ናቸው፡፡   በስደት ለተቀላቀሉት ማህበረሠብም አዲስ ጉልበት ይሆናሉ፡፡ እዚህ እኛ ሀገር እንኳ ፒዛ፣ ከሪና ሱሺ የተባሉ የምግብ አይነቶችን ወደንና ፈቅደን የምንመገባቸው የእኛ ሆነው ሳይሆን ጣሊያኖች፣ ህንዶችና ጃፓኖች በተለያየ ምክንያት ወደ ሀገራችን መጥተው ሲኖሩ ሲመገቡ በማየታችን ወይም እንድንበላ ጋብዘውን አሊያም አሰራሩንም ሆነ አመጋገቡን ስላስተማሩን ነው፡፡  ለስደት ዋነኛው ምክንያት ደግሞ የሰው ልጆች የተሻለ ኑሮና የተሻለ ህይወትን ፍለጋ ያላቸው መቼም ቢሆን የማይበርድ ፍላጐትና እንቅስቃሴአቸው ነው፡፡ እናም እንዲህ በመሠለው የሰው ልጆች የስደት እንቅስቃሴ ውስጥ አዳዲስ ሀሳቦችን ያፈልቃሉ፣ አዳዲስ ግንኙነቶችንና አዳዲስ የአኗኗር ዘይቤዎችን ይፈጥራሉ፤ ያስተዋውቃሉ፡፡ የሰው ልጆችን ታሪክ በወሳኝ መልኩ መቀየር ከቻሉት ጥቂት ሁነቶች አንዱ ስደት ነው፡፡ በያዝነው ዘመን በየአለማቱ ክፍል የምናየው ዘርፈ ብዙ መልክና ዘረ ብዙውን ህብረተሠብ በወሳኝ መልኩ ከፈጠሩት ጥቂት ነገሮች አንዱ የሰዎች ከቦታ ቦታ፤ ከሀገር ሀገር እየተዘዋወሩና እየተሰደዱ መኖር ነው፡፡ለምን መሰላችሁ? እነዚህ ኢትዮጵያውያን በስደተኝነት የመን ውስጥ ለወራትም ሆነ ለአመታት ያሳለፉት ህይወት ስለ ገሀነም እየሰሙም ሆነ እያነበቡ ካደጉት እጅግ አስፈሪና አስጨናቂ የፍዳ ህይወት ጋር ተመሳሳይ ስለሆነና እንዲህ ያለውን የገሀነም ህይወት የገፉትም በየመን ስለሆነ ነው፡፡ ገሀነም እንዴት ያለ ቦታ እንደሆነ በአይኑ ያየ ወይም የት አካባቢ እንደሚገኝ በትክክል የሚያውቅ ሰው እንደሌለ ግልፅ ነው፡፡ ይሁን እንጂ እንዴት የመሰለ ቦታ ነው ተብሎ የተጠየቀ ማንኛውም ሰው ግን እንዲህ ነው ብሎ የሚሰጠው መልስ ያጣል ተብሎ ጨርሶ አይገመትም፡፡ ለምን ቢባል በእድሜ ዘመናችን ሙሉ በሀይማኖታዊም ይሁን በሌላ ጉዳይ ስለ ገሀነም እየተነገረን አሊያም ሌሎቹ ይመስላል ብለው የፃፉትን እያነበብን ስላደግን ከአዕምሯችን ጓዳ ከተጠራቀመው መረጃ ጨልፋን መናገርና ማስረዳት ስለምንችል ነው፡፡ ከእነዚህ ከስደት ተመላሽ ኢትዮጵያውያን አንዳቸውን ወይንም ሁሉንም ገሀነም እንዴት ያለ እንደሆነና የት እንደሚገኝ ብትጠይቋቸው ሁሉም ባንድ ቃል የሚመልሱላችሁ እንዲህ ብለው ነው፡- “አዎ! ገሀነም እንዴት ያለ እንደሆነ እናውቀዋለን፡፡ የሚገኘውም የመን ውስጥ ነው!” በቃ ይህንኑ ነው የሚሏችሁ፡፡አዕምሮን ጠፍሮና በሀዘን አንገት አስደፍቶ ለብዙ ቀናት ያስቆዝማል፡፡ የእነዚህን አሳዛኝ ከስደት ተመላሽ ኢትዮጵያውያን ህይወት አልባና ኦና አይኖቻቸውን ያየ ሰው በቀላሉ የሚረዳው፣ የተሰበረ ቅስማቸውንና በረዳት አልባ አቅመቢስነት ስሜት ተውጠው ተስፋቸውን የቆረጡ መሆናቸውን ብቻ ነው፡፡ ሁኔታቸው ያያቸውን ሰው ሁሉ አንጀት ይበላል፡፡ ከእነሱው መካከል ለዓመል ያህል እንጥፍጣፊ ጉልበት የቀራቸው፣ ተሽከርካሪውን ወንበር እንደ ነገሩ ገፋ መለስ እያደረጉ ሊያንቀሳቅሷቸው ይሞክራሉ፡፡  ይህንኑ ተሽከርካሪ ወንበር ለማንቀሳቀስ የሚሆን አቅም ስላልነበራቸውም ከአንዱ ጥግ ወደ አንዱ የሚንቀሳቀሱት በሌሎች ሰዎች እርዳታ ብቻ ነበር፡፡ አንዳንዶቹ በደረሠባቸው ጉዳት አስከፊነት የተነሳ ቆመውም ሆነ ራሳቸውን ችለው መንቀሳቀስ ስለሚያዳግታቸው በተሽከርካሪ ወንበር ላይ ተቀምጠዋል፡፡እግርና እጃቸው የተሰበረ፣ በጥይት የቆሰሉ፣ ፊታቸው የቆሰለና የተጋጋጠ፣ የአዕምሮ መዛባት የደረሠባቸው፣ ረሀብ አቅማቸውንና ወጣትነታቸውን ሠልቧቸው እንደ ሽማግሌ አጐንብሰው በከዘራ የሚራመዱ ወዘተ ይገኙባቸዋል፡፡ በአንድ ጊዜ እይታ ብቻ በየመን ያሳለፉት የስደተኝነት ጊዜ እንዴት ያለ እንደነበር በቀላሉ መገመት ይቻላል፡፡ የሰውነት አቋማቸውን ያየ በቅድሚያ የሚሠማው ስሜት ሀዘኔታ ሲሆን ቀድሞ ሊያስብ የሚችለውም “ምን አግኝቷቸው ይሆን?” የሚለውን ብቻ ነው፡፡ ሁሉም ስጋቸው አልቆ ከአጥንታቸው ጋር የተጣበቀና ልክ ለአይነት ወይም ለናሙና የቀረበ ይመስል አይነቱ የበዛ አካላዊ ጉዳት የተቀበሉ ናቸው፡፡መንገደኞቹ በኢትዮጵያ መንግስትና በአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) ትብብርና እርዳታ አማካኝነት በስደተኝነት ከኖሩበት የመን ወደ ሀገራቸው የተመለሱ ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡ ባለፈው ሁለት ወር ግድም የቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመቶዎች የሚገመቱ መንገደኞችን ተቀብሎ አስተናግዶ ነበር፡፡ እነዚህ መንገደኞች በዚያን ቀን በአውሮፕላን ማረፊያው ከተስተናገዱት በሺ የሚቆጠሩ ተመላሽ መንገደኞች መካከል ቢሆኑም ከሌሎቹ የተለዩ መንገደኞች ነበሩ፡፡

Read 4014 times