Saturday, 10 November 2012 13:57

34 ተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫው ፍትሃዊነት ላይ ጥያቄ አለን አሉ

Written by  መታሰቢያ ካሣዬ
Rate this item
(7 votes)

ኢህአዴግ ሚዲያውን ለምርጫ ቅስቀሣም ሆነ ፖሊሲውን በስፋት ለህዝቡ ለማድረስ እየተጠቀመበት እንደሆነና በፓርቲው ንብረትና በኢትዮጵያ ህዝብ ንብረት መካከል ያለው ልዩነት እንደማይታወቅ በመግለፅ ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ የሚያቀርቡትን አቤቱታ ተቀባይነት የለውም ያሉት ኃላፊው፤ ህዝቡ ኢህአዴግን መንግስት አድርጐ ሲመርጥ ፖሊሲውን በስፋት እንዲያስተዋውቅ እውቅናና ይሁንታ ሰጥቶታል ብለዋል፡፡ በተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚቀርቡትን ቅሬታና አቤቱታዎች በጋራ ምክር ቤት እያዩ መፍትሔ እንደሚፈልጉና በተባለው ጉዳይ ግን የቀረበላቸው አንዳችም ቅሬታ አለመኖሩን አቶ ተመስገን ጨምረው ገልፀዋል፡፡    የምርጫ ሥነ ምግባር ህግ ከፈረማችሁ በኋላ የዚህ ዓይነት ጥያቄ ማቅረብ የሥነ ምግባር ህጉን እንደመጣስ አያስቆጥራችሁም ወይ ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ በ2002 ዓ.ም ምርጫው በተካሄደ በ3ኛው ቀን ኢህአዴግ በምርጫው ማሸነፉን በመግለፅ የምርጫ ሥነ ምግባሩን በግንባር ቀደምትነት ጥሶታል ብለዋል፡፡

የምርጫ ቦርድ ለጥያቄያቸው ተገቢ ምላሽ ካልሰጣቸው ሰላማዊና እርምጃ እንወስዳለን ይህ እርምጃም ሰላማዊ ሰልፍን ጨምሮ ህዝባዊ ንቅናቄ እስከመፍጠር የሚደርስ ነው ሲሉም አክለዋል፡፡ የምርጫ ቦርድ የህዝብ ግንኙነት ማስተባበሪያ ኃላፊ ወ/ሮ የሺ ፈቃድ፤ ፓርቲዎቹ ስላቀረቡት ጥያቄ የሚያውቁት ነገር አለመኖሩን ገልፀው፣ ጥያቄያቸው በቦርድ የሚፈታና አግባብነት ያለው ከሆነ በወቅቱ ምላሽ እንደሚሰጧቸው ተናግረዋል፡፡ ቦርዱ ለገዥው ፓርቲ የሚያዳላና ገለልተኛ አይደለም በማለት ፓርቲዎቹ ያቀረቡትን አቤቱታ አስመልክቶ ሲናገሩም የ2002 ምርጫ ሲጠናቀቅ ቦርዱ አዘጋጅቶት በነበረው የምርጫ ግምገማ መድረክን ጨምሮ ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ በቦርዱ ቅሬታ እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የዚህ አይነት ቅሬታ የሚያቀርቡት ሁልጊዜም ምርጫ ሲቀርብና የምርጫ ሙቀት ሲኖር ነው በማለትም አክለዋል - ወ/ሮ የሺ፡፡ የኢህአዴግ የአጋር ድርጅቶችና አደረጃጀቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተመስገን ጥላሁን በበኩላቸው፤ ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ በምርጫው ሂደት ላይ የሚያነሷቸው ቅሬታዎች አግባብ ናቸው የሚል እምነት እንደሌላቸው ጠቁመው፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ ምርጫ ቦርድንም ሆነ ሚዲያውን ከኢህአዴግ ጋር ለማላተም የሚያደርጉት ሙከራ ህገወጥ ነው ብለዋል፡፡የኢህአዴግ አምባገነናዊ ሥርዓት እየተባባሰ ሄዷል ያሉት የፓርቲዎቹ ተወካዮች፤ ከምርጫ 2002 በኋላ በርካታ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ለእስር መዳረጋቸውንና የመናገርና የመፃፍ ነፃነትን በማፈንም የፕሬስ ሕትመቶችን እስከመዝጋት የደረሰ እርምጃ መወሰዱ፤ የሽብርተኝነት አዋጅ መውጣቱም የኢህአዴግ አምባገነንነት ውጤት ነው ሲሉም የፓርቲዎቹ ተወካዮች በመግለጫው ላይ ተናግረዋል፡፡ፓርቲዎቹ ትናንት በአንድነት ፓርቲ ቢሮ ውስጥ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ፤ የመድረክ ፓርቲ የስራ አስፈፃሚ አባልና ለዚሁ ጉዳይ የተቋቋመው ኮሚቴ ሰብሣቢ የሆኑት አቶ አሥራት ጣሴ እንደተናገሩት፤ ምርጫ ቦርድ በግንቦት ወር በሚካሄደው የአካባቢ ምርጫ አፈፃፀም የጊዜ ሰሌዳ ላይ ለመወያየት በአዳማ ከተማ ጥቅምት 15 ቀን 2002 ዓ.ም አዘጋጅቶት በነበረው ስብሰባ ላይ ከጊዜ ሰሌዳው በፊት በምርጫው ፍትሃዊነት ላይ በቅድሚያ ሊወያዩ እንደሚገባ ለቦርዱ ጥያቄ ማቅረባቸውን ገልፀዋል፡፡ ምርጫ ቦርድ በወቅቱ ጥያቄያቸውን ተቀብሎ ተገቢ ምላሽ ሊሰጣቸው ባለመቻሉ በስብሰባው ላይ ከነበሩት የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር የጋራ ምክክር አድርገውና ፒቲሽን ተፈራርመው ጥያቄያቸውን በጋራ ለምርጫ ቦርዱና ለጠቅላይ ሚ/ር ፅ/ቤት ማቅረባቸውን ተናግረዋል፡፡ምርጫ ቦርድ ለጥያቄያችን ተገቢና በቂ ምላሽ ሰጥቶን ባያውቅም ጥያቄዎቻችንን ከማቅረብ ወደኋላ አንልም ያሉት የፓርቲዎቹ ተወካዮች፤ ቦርዱ ከፈረሱ በፊት ጋሪውን በማስቀደም ከምርጫው ነፃ መሆንና ከፍትሃዊነቱ አስቀድሞ በምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ላይ  ለመወያየት መሞከሩ አግባብነት የሌለው ነው ብለውታል፡፡ ከምርጫ ቦርድ መልካም መልስ የማግኘት የዋህነት ባይኖረንም ጥያቄያችንን ከማንሳት ወደ ኋላ አንልም ያሉት ፓርቲዎቹ ለጥያቄያችን ተገቢና በቂ ምላሽ እስካላገኘን ድረስ ምርጫውን ለማጀብ ፍቃደኞች አይደለንም ብለዋል፡፡ በመጪው ግንቦት ወር የሚካሄደውን የአካባቢና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምርጫ አስመልክቶ ከምርጫው ጊዜ አስቀድሞ በምርጫው ፍትሃዊነት፣ ዲሞክራሲያዊነትና ነፃ መሆን ላይ ውይይት መካሄድ እንደሚገባው በማሳሰብ ሰላሣ አራት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለምርጫ ቦርድ ጥያቄ ማቅረባቸውን ገለፁ፡፡ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅ/ቤት ያቀረቡት ጥያቄ ደብዳቤው ማህተም የለውም በሚል ምክንያት ተቀባይነት ሣያገኝ መቅረቱንም ተናግረዋል፡፡ ምላሽ የሚሰጠው ተገቢ ጥያቄዎችን ሲያቀርቡ ነው - ምርጫ ቦርድ ምርጫ ቦርድን ከኢህአዴግ ጋር ማላተማቸው አግባብ አይደለም - ኢህአዴግ  ለጥያቄያችን ምላሽ ካልተሰጠን ምርጫውን ለማጀብ ፍቃደኞች አይደለንም -  ፓርቲዎች

 

Read 2882 times Last modified on Saturday, 10 November 2012 17:05