Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 10 November 2012 13:56

ብዙ ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የመንግስት ንብረቶች በግለሰብ ቤት ተያዙ

Written by 
Rate this item
(8 votes)

በቁጥጥር ሥር በዋሉት ተጠርጣሪዎች ላይ ፖሊስ የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆ ምርመራውን እያካሄደ መሆኑም ታውቋል፡፡ ከፍተኛ ገንዘብ ያወጣሉ የተባሉት እነዚህ ንብረቶች በሞያሌ በኩል ወደ ኬኒያ ተወስደው ሊሸጡ በዝግጅት ላይ እንደነበሩና ዕቃዎቹን በሞያሌ በኩል ወደ ኬኒያ የሚያጓጉዙ ተረካቢዎችም እንዳሉ ተጠቁሟል፡፡ ፖሊስ በጉዳዩ ላይ ምርመራ እያካሄደ ሲሆን ከወንጀሉ ጋር ተያያዥነት ያላቸውና ገና ያልተያዙ ሰዎችም እንዳሉበት ታውቋል፡፡ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን፣ ከውሃና ፍሳሽ አገልግሎትና ከኢትዮ ቴሌኮም መ/ቤቶች የተውጣጡ ተወካዮች በፍተሻው ወቅት የተገኙትን ንብረቶቻቸውን እንዲለዩ ተደርጐ ተዘርፈው የተከማቹት ንብረቶች በሁለት ገልባጭ መኪኖች ወደ ፖሊስ መጋዘን እንዲጓጓዙ ተደርጓል፡፡ ዕቃዎቹም በኤግዚቢትነት ተይዘዋል፡፡

10 ሜትር በሚደርስ ርዝመት በታጠረው ግቢ ውስጥ በየዕለቱ የሚገቡና የሚወጡ የጭነት መኪኖች ይዘው የሚወጡትና ወደ ግቢው ይዘው የሚገቡት ነገር ግራ ያጋባቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ጥርጣሬያቸውን ለፖሊስ በማመልከታቸው ፖሊስ በአካባቢው ክትትል ማድረግ ይጀምራል፡፡ የነዋሪዎቹን ጥርጣሬ የሚያጐላ ምልክት ማየቱን ያረጋገጠው ፖሊስ፤ በቤቱ ላይ የፍተሻ ፈቃድ በማውጣት ቤቱን ባለፈው ሳምንት ድንገት ሲያስከፍት በግቢው ውስጥ በሚሊዮኖች የሚገመት ዋጋ ያወጣሉ የተባሉትን የስልክ መስመር ኬብሎች፣ የመብራት መስመሮች፣ ቆጣሪዎች፣ የውሃ ቆጣሪዎችና የተለያዩ መሣሪያዎች ተከማችተው ያገኛል፡፡ ከወንጀሉ ጋር ንክኪ አላቸው ያላቸውንም ዘጠኝ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር አውሏል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በወረዳ 13 ልዩ ስሙ ሎሚ ሜዳ እየተባለ በሚጠራው ሥፍራ ከአካባቢው ነዋሪዎች ለፖሊስ በደረሰ ጥቆማ መሠረት፣ ቤቱ ሲፈተሽ በርካታ የቴሌ፣ የውሃና የመብራት ኃይል ንብረቶች ተገኝተዋል፡፡ ከተለያዩ ቦታዎች እየዘረፉና በህገወጥ መንገድ እየሰበሰቡ የተከማቹና ወደ ውጪ አገር ተወስደው ለመሸጥ በዝግጅት ላይ የነበሩ በሚሊዮኖች የሚገመት ዋጋ የሚያወጡ፣ የስልክ፣ የመብራትና የውሃ መስመሮች ኬብሎችና ልዩ ልዩ ዕቃዎች በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ግቢ ውስጥ ተከማችተው ተያዙ፡፡ ዘጠኝ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል

Read 3321 times

Latest from