Print this page
Saturday, 10 November 2012 13:54

የ“ሆላንድ ካርስ” ደንበኞች ያዘዝነው መኪና አልደረሰንም አሉ

Written by  መልካሙ ተክሌ
Rate this item
(5 votes)

እሱም ስላለቀ ተጨማሪ ብድር እየፈለግን የደረሰውን እያስረክብን ነው፡፡ ውላችንን ለመፈፀምና ለቀጣይ ገበያ ስንል በኪሳራ እናስረክባለን፡፡” ብለዋል - አቶ ሰለሞን ታሪኩ፡፡  “በዶላር የምንዛሬ ለውጥ፣ በመለዋወጫዎች መናር፣ በመኪና ቀረጥ መጨመርና በሌሎች ምክንያቶች የገንዘብ እጥረት ገጥሞናል፡፡ 120ዎቹን ደንበኞች ገንዘብ ፈልገን በራሳችን ኪሳራ እናስረክባለን፡፡ እስካሁን 22 ሚሊዮን ብር ተበድረናል፡፡ ስለ ጉዳዩ ማብራሪያ የተጠየቁት የሆላንድ ካርስ ሃላፊ አቶ ሰሎሞን ታሪኩ፤ ገንዘብ ይመለስልን ያሉ ደንበኞችን የገንዘብ እጥረት እስከገጠማቸው ጊዜ ድረስ ማስተናገዳቸውን ገልፀው፤ ለ”አባይ” መኪና 80ሺህ ብር፣ ለ“አዋሽ” 100ሺህ ብር ማስረከባቸውን ተናግረዋል፡፡ለመኪና አምራቹ “ሆላንድ ካርስ” የመኪና ግዢ ትእዛዝ ያስተላለፉ 120 ደንበኞች እስከ 100ሺ ብር ቢያሲዙም መኪናው እንዳልደረሳቸው ተናገሩ፡፡

ደንበኞች ድርጅቱ የሚያመርታቸውን አባይ፣ ተከዜ እና ሸበሌ የቤት መኪኖች ለመግዛት ከዓመት በፊት  ውል የገቡ ሲሆን ከ40ሺህ ብር እስከ 100ሺህ ብር እንዳስያዙ ጠቁመው፤ መኪናቸው እንዲሰጣቸው ወይም ገንዘቡ እንዲመለስላቸው ጠይቀው ምላሽ አለማግኘታቸውን ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡ አንዳንድ ደንበኞች ድርጅቱን ለመክሰስ እንደተዘጋጁ ታውቋል፡፡ የስድስት መቶ መኪኖች ግዢ ውል መቀበሉን ያመነው “ሆላንድ ካርስ” በበኩሉ፤ 480 መኪኖችን ማስረከቡንና የተቀሩት 120 ትእዛዞች የፋይናንስ እጥረት በመግጠሙ ማስረከብ አለመቻሉን ጠቅሶ፤ ገንዘብ እንደተገኘ በውሉ መሠረት ለደንበኞቹ እንደሚያስረክብ ገልጿል፡፡ መኪኖቹ ካልተሸጡልን ገንዘባችን ይመለስ ያሉ ደንበኞች፤ ጥያቄአቸውን ለድርጅቱ ካቀረቡ ከአራት ወር በኋላ “የሚመነዘር ቼክ ያለ ወለድ እንስጣችሁ” እንደተባሉና ይሄም አግባብ እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡ ድርጅቱ የገንዘብ እጥረት ገጥሞታል

Read 2816 times