በዚሁ መሠረት “ቢዝነስ፣ ሞባይል 100” ተጠቃሚዎች በወር 52 ብቻ ከፍለው 100 ደቂቃ የስልክ ጥሪ፣ 30 የጽሑፍ መልእክት እና አምስት ሜጋቢትስ የኢንተርኔት አገልግሎት የሚያገኙ ሲሆን ቢዝነስ ሞባይል 250፣ 500 እና 1000 ሺህም ከ122 ብር እስከ 470 ብር ከፍለው ለየአይነቱ የተፈቀደውን አገልግሎት ያገኛሉ፡፡ ኢትዮ ቴሌኮም (ቴሌ) ከትናንት በስቲያ ጀምሮ አዲስ የሞባይል አገልግሎት ማሻሻያ ማድረጉን አስታወቀ፡፡ የድርጅቱ የውጭ ግንኙነት መምሪያ ሃላፊ አቶ አብዱራሂም አህመድ ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት፤ “with in Business Mobile” በተሰኘውና የማስተዋወቂያ ፕሮግራሙ እስከ ጥር 23 በሚቆየው አዲሱ መርሃግብር ግዙፍ፣ መካከለኛ እና አነስተኛ የንግድ ተቋማት አምስት አይነት አገልግሎት የሚያገኙ ሲሆን አምስት እና ከዚያ በላይ ሠራተኞች ያሏቸው ተቋማት ለእርስ በርስ ሞባይል ጥሪ የአገልግሎቱን አዲስ መርሃ ግብር ለመቀላቀል ካሰቡ ከግማሽ በላይ ቅናሽ ይደረግላቸዋል፡፡ ለ “with in Business Mobile” ተጠቃሚዎች አገልግሎቱ ትላንት በስቲያ ጀምሮ ተለቋል፡፡