Print this page
Saturday, 03 November 2012 12:57

በድሬዳዋ በ600 ሚ.ብር የውሃ ተቋም ግንባታ ሊካሄድ ነው

Written by  መታሠቢያ ካሣዬ /ከድሬዳዋ/
Rate this item
(1 Vote)

ከአለም ባንክ በተገኘ የብድር ገንዘብና ከከተማ መስተዳድሩ በጀት እንዲሁም ከህብረተሰቡ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በድሬዳዋ ከተማ ስድስት መቶ ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ገንዘብ አዲስ የውሃ ተቋም ግንባታ ሥራ ሊካሄድ ነው፡፡ ግንባታውን ለማካሄድ የሚያስችሉ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውንና በቅርቡም የቁፋሮው ሥራ እንደሚጀመር ተገልጿል፡፡ በድሬዳዋ ከተማ ውሃና ፍሣሽ ባለስልጣን አስተባባሪነትና በሌሎች አጋር ድርጅቶች ድጋፍ በተዘጋጀውና ዛሬ በሚጠናቀቀው 6ኛው የኢትዮ ውሃ አገልግሎቶች ፎረም ላይ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትር አቶ ከበደ ገርባ እንደተናገሩት፤ ድሬዳዋ የውሃ ችግር አለባቸው ከሚባሉት የአገሪቱ ከተሞች አንዷ ስትሆን ይህንኑ በከተማዋ በተደጋጋሚ የሚከሰተውን የውሃ አቅርቦት ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ እንዲቻል አዲስ የውሃ ተቋም ግንባታ ለማካሄድ ዝግጅቱ ተጠናቋል፡፡

ወደ ስድስት መቶ ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ወጪ ይገነባል የተባለው የውሃ ተቋም ከአለም ባንክ በተገኘ የብድር ገንዘብ፣ ከከተማው መስተዳድርና ከህብረተሰቡ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚሰራም ተገልጿል፡፡ ግንባታውን ለማካሄድ የሚያስችል ቅድመ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውንና በቅርቡም የቁፋሮ ስራ እንደሚጀመር ተናግረዋል፡፡ 
በተያያዘ ዜናም የውሃ ፍጆታ አገልግሎት ክፍያን አሠራር የሚለውጥና በአገልግሎት ፍጆታ ታሪፍ አሰባሰብ ላይ ያሉትን ችግሮች ለማስቀረት ያስችላል የተባለ የቅድሚያ ክፍያ አገልግሎት የሙከራ ሥራ በድሬዳዋ ከተማ የሙከራ ትግበራ የጀመረ ሲሆን በቀጣይም በየክልሎችና በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ መደረግ እንደሚጀምር ምክትል ሚኒስትሩ አቶ ከበደ ገርባ ገልፀ````````ዋል፡፡

Read 2358 times