Monday, 05 March 2012 14:06

ለነርቭ ሥርዓት ጠቀሜታ ያለው ትራስ ተመረተ

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(0 votes)

የጭንቅላት፣ የአንገት፣ የትከሻና የህብረሰረሰር አቀማመጥን ጤናማ እንዲሆን በማድረግ ነፃ የነርቭ የአየርና የደም ፍሰት እንዲኖር ያደርጋል የተባለ ትራስ አገራችን ውስጥ ተመረተ፡፡ ሰርቪካል ትራስ የሚል ስያሜ የተሰጠው ይኸው ትራስ በደንገል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እዚሁ አገራችን ውስጥ መመረት የጀመረ ሲሆን ትራሱ በአንገት አካባቢ ጡንቻዎች ላይ የሚከማችን ጫና በማርገብ የአእምሮ መረጋጋትን እንደሚፈጥርና የአየር ዝውውርን በማስተካከል በተለይ ለደም ግፊት ህሙማን ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚሰጥ የነርቭ የአጥንትና የጡንቻ ስፔሳሊስት የሆኑት ዶ/ር ሠላም አክሊሉ ገልፀዋል፡፡

ድርጅቱ አዲሱን ምርት አስመልክቶ ባለፈው ሐሙስ በኢትዮጵያ ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አቶ ዳዊት ደስታ እንደተናገሩት፤ እነዚህ ምርቶች ቀደም ሲል ከውጭ አገራት በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወደ አገር ውስጥ ይገቡ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን እነዚህኑ ልዩ ትራሶች በአገር ውስጥ በማምረት የውጭ ምንዛሪውን ለማስቀረት መቻሉን ጠቁመዋል፡፡ ትራሱ የጭንቅላት፣ የአንገትና የትራስን ቅርፅ ተከትሎ እንዲደግፍ ተደርጐ በልዩ ሁኔታ መሠራቱን የገለፁት አቶ ዳዊት፤ በመኝታ ወቅት ጭንቅላታችን፣ አንገታችን፣ ትከሻችንና ህብለ ሰረሰራችን ትክክለኛውን ቅርፅ ይዞ እንዲደላደል በማድረግ ከበርካታ ህመሞች ሊከላከል ይችላል ብለዋል፡፡

ደንገል ኃ.የተ.የግ.ማህበር ቀደም ሲል የተለያዩ የህፃናትና የእርጉዝ እናቶችን ምቾት ለመጠበቅ የሚያስችሉ ትራሶችን ሲያመርት የቆየ ድርጅት ነው፡፡

 

 

Read 3236 times Last modified on Monday, 05 March 2012 14:17