Saturday, 24 September 2011 08:59

የመስቀል በዓል የአበቦች በዓል ነበር

Written by  ተፈሪ መኮንን
Rate this item
(0 votes)

ከትናንት ወዲያ ..የፈረንሳይ ሳሎን.. ስል ከሰየምኩት የጓደኛዬ ቤት ሄድኩ፡፡ ወደ እዚህ ቤት ስሄድ የ..ሰለሞን ሰዓት..ን ጠብቆ በሚመጣ ጨዋታ ኢትዮጵያ ትዘከራለች፡፡ በዚህ የጓደኛዬ ቤት የማያትን ኢትዮጵያ አላውቃትም፡፡ የማውቀው ታሪኳም ልዩ ቅኔ ሆኖ ሊታየኝ ይፈልጋል፡፡ ..ታላቁ እስክንድር.. በምለው በዚህ ጓደኛዬ ህሊና ውስጥ ያለችው ኢትዮጵያ ዜጋ መሆንም አብዝቶ ያኮራኛል - ሁሌም፡፡

ዛሬ ..ታላቁ እስክንድር.. እና አቢይ የጋለ ሙግት ገጥመዋል፡፡ ..ቆይ ልጨርስ.. እየተባባሉ የኢትዮጵያን ታሪክ እየፈቱ ይገጥማሉ፡፡ ከህይወት እና ከፊደል ያገኙትን ሃቅ እየጠቀሱ ይከራከራሉ፡፡ ደግሞ ይወያያሉ፡፡ ደግሞ ይሟገታሉ፡፡ የአባት እና የአያታቸውን ቃል እየጠቀሱ፤ እየተስማሙ ይለያያሉ፡፡ እየተለያዩ ይስማማሉ፡፡ ወሬ ጠነን ሲል የማይወደው ..ታናሹ እስክንድር.. እና Xn¤\ በአድማጭነት ታድመናል፡፡ ከ..ሰለሞን ሰዓት.. በረንዳ ቁጭ ብዬ፤ ገና እንቆቅልሹ ያልተፈታውን የኢትዮጵያን ጉዳይ እሰማለሁ፡፡
ሰፊው ..የፈረንሳይ ሳሎን..\ የብሉይ እና የሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ታሪክን በአንድ ላይ እያስተናገደ ነው፡፡ ከምሥራቅ እና ከምዕራብ አቅጣጫ ብርሃን ይገባል፡፡ ታላቁ እስክንድር የኢትዮጵያን ታሪክ ..በእምነት እየሸመነ፣ በግጥም ልሳን እያደመቀ፣ በሣይንስ ቀለም እየፃፈ.. ይተርካል፡፡
በ..ታላቁ እስክንድር.. ሃሳብ፤ የጥበብ ሁሉ ምንጭ ወይም መገኛ ኢትዮጵያ ናት፡፡ ..ታላቁ እስክንድር..፤ ኢትዮጵያ የጥበብ ምንጭ ስለመሆንዋ ሲያወራ፤ ታሪክን እና ሳይንስን ዋቢ እያደረገ ነው፡፡ እርሱ እንኳን ማስረጃ እየጠቀሰ ተናግሮ፤ በደፈናው ሲናገርም እንድትቀበሉት የሚያደርግ ሁኔታ አለው፡፡ ግን ያለ ማስረጃ አይናገርም፡፡ ..ኢትዮጵያWÃN ይህን እንዴት አድርገው አዩት፤ ያን ለምን እንዲያ አደረጉት፤ እኔ እኮ የሚገርመኝ ይኸ ነው.. እያለ ያወራል፡፡
እንግዳ አስተያቶቹ ሁሉ በሳይንስ ችሎት የመቆም ብቃት እንዳላቸው እየተሰማችሁ ነው የምትከታተሉት፡፡ ..ታላቁ እስክንድር.. የሚያውቀውን ነገር ሁሉ እንዳልነገራችሁ ወይም የሆነ ምስጢር እንደ ደበቃችሁ እየተሰማችሁ፤ የሚናገረውን ታደምጣላቸሁ፡፡ ታዲያ አንዳንዴ ..ይህ ሰው ብዙ ምስጢር ይዟል፡፡ ታዲያ ለምን አይፅፈውም?.. የሚል ስሜት ይመጣብኛል፡፡ ሆኖም ለምን አትፅፈውም? ብዬ ጠይቄው አላውቅም፡፡ ራሴ፤ ..ይህ ሰው ታሪክ ለመፃፍ ጊዜ የለውም፡፡ የሚያውቀው ብዙ ከመሆኑ የተነሳ ልፃፈው ብሎ ቢነሳ ከሚያውቀው ግማሹን እንኳ ሳይገልፀው መቶ ዓመት ይነጉዳል.. ብዬ አስቤ ጥያቄውን እተወዋለሁ፡፡ አንዳንዴ ደግሞ፤ ፀጋዬ ገ/መድህን ..ባለ ቅኔው፤ ስለ ግሥ፣ ስለ ሰዋሰው ከማተት ይልቅ፤ ቅኔ መቀኘቱ ይበልጥበታል.. እንዳለ፤ ለእርሱ ማውራቱ ይበልጥበታል እላለሁ፡፡ ዓመተ ምህረት ወይም ማጣቀሻ ማደራጀት ስለሚሰለቸው ቁጭ ብሎ ማውራቱን የመረጠ ይመስለኛል፡፡
ዛሬም እንደ ሌላው ቀን ..እንትና ቢያጫውታችሁ... ጉድ ትሉ ነበር.. እያለ፤ ከእርሱም የላቀ ሰው መኖሩን እየነገረኝ ሲያስደምመኝ ቆይቶ፤ ድንገት ሳላስበው ..ግን እኮ እኔ ኢትዮጵያን እንደምወዳት እሷ አትወደኝም.. አለ፤ ታላቁ እስክንድር፡፡ አነጋገሩ አሳዝኖኛል፡፡ ታዲያ በንግግሩ ..ይቺ አሮጊት ለሚወዳት ደንታ የላትም.. የሚል ቃል ከአንደበቱ ባይወጣም ቅላፄው ወይም ድምፀቱ እንደዛ ዓይነት መልዕክት ያላቸው መስሎ ተሰማኝ፡፡
ያ የድምፀቱ መልዕክት ያዘኝ እንጂ በዚያው ቅፅበት፤ ..ኢትዮጵያ ሀገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ..... የሚለው የተለመደ ሙሾ ወደ አዕምሮዬ ሊገባ ሲንደረደር እግዚሃር አተረፈኝ፡፡ በሙሾው ፈንታ፤ ..አይ ኢትዮጵያ ትወድሃለች.. አልኩት፡፡ የኔን ቃል ተከትሎ፤ ..እርሷ እኮ ለሚውዳት ደንታ የላትም.. አለ፤ ከመካከላችን አንዱ፡፡
..ታላቁ እስክንድር.. ቀጠለ፡፡ ..በቀደም አንዱ ፈረንጅ ትንሽ ታበዛዋለህ አለኝ...ግን እኔ ናሽናሊስት ነኝ እንዴ? በፍፁም አይደለሁም.. አለ፡፡ ከብሄርተኝነት ጠንቅ ራሱን ለመጠበቅ ንቁ ዘብ ያለው ይመስለኛል፡፡ ቀልድ ባለዘበው የንግግር ለዛ ዘርጠጥ የማድረግ ድፍረት አለው፡፡
..ኢትዮጵያ ጀግኖችዋን አታከብርም.. የሚል ሃሳብ ሳመነዥክ ሳለሁ፤ ..ታላቁ እስክንድር.. ኢትዮጵያን መውቀስ እንዳልፈለገ ዓይነት ..ግን ጀግኖችዋን የማትወድ ብትሆን ሥልጣኔን ልታገኝ አትችልም ነበር፡፡ አሁን ጠፍቶባት ይሆናል እንጂ ጀግኖችዋን ሳታከብርማ ይህን ስልጣኔ ልታይ አትችልም.. አለ፡፡
..ኢትዮጵያ ታላቅ ዕድገት እና ሥልጣኔ ላይ የደርሰችው እንደ ንጉስ አርማህ ወይም አል ነጃሺ ዓይነት መሪዎች ሥልጣን በያዙ ጊዜ እንጂ ማካቬላዊ መርህን የሚከተሉ ነገስታት በመጡ ጊዜ አይደለም.. አለ፤ ታላቁ እስክንድር፡፡ አቢይ፤ በጥቅሉ ይትብሃሉ ላይ ሳይሆን ዝርዝር ላይ ተቃውሞ ነበረው፡፡
አቢይ ያነሳት አንዲት የመከራከሪያ ነጥብ ሰበብ ሆና በፊታችን ረቡዕ ስለሚከበረው የመስቀል በዓል ማውራት ጀመርን፡፡ ..የመስቀል በዓል ከክርስትና ጋር ተያይዞ የመጣ አይደለም፡፡ ከዚያ የቀደመ ታሪክ ያለው ነው.. አለ አቢይ፡፡ ይህን ሃሳቡን የምታስረዳም አንዲት አነስተኛ መጽሐፍ ይዞ መጣ፡፡ አውጥቶም እንዳነባት ሰጠኝ፡፡
መፅሐፍዋ በ1956 ዓ.ም የተፃፈች ናት፡፡ አዘጋጅቶ ያሳማትም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተKRStEÃN ጠቅላይ ቤተ ክህነት የታሪክና ድርሰት ዝግጅት ክፍል ነው፡፡ ..ርዕዩ ጽጌያተ ገዳም.. (የዱር አበቦችን tmLkt$) በሚል ርዕስ በታተመችው በዚህች መፅሃፍ፤ የአበባ በዓል በሚል የሚከበር ዓውደ ዓመታዊ በዓል በኢትየጵያ እንደ ነበር ጠቅሶ፤ ..በየዘመኑ የተነሡ ሰዎች ከፍ ያለ ውበትና ሥን የተጎናጸፈ ጥበበኛ እጁን ያላሳረፈበትን የዱር አበቦች ጌጥ ተመልክተው እጅግ ይደሰቱ ነበር.. ሲል ሃተታውን ይጀምራል፡፡
አበባ ለሰዎች አስደሳች መሆኑን እና በኢትዮጵያም የደስታ እና የአክብሮት መግለጫ ሆኖ ሲያገለግል መቆየቱን የጠቀሰው የዝግጅት ክፍሉ፤ በኢትዮጵያ አበቦች በሚያብቡበት ወራት ..ወዳጅ ለወዳጁ፤ ልጅ ለአባቱ፤ ሎሌ ለጌታው፤ ደንገጡር ለእመቤትዋ፤ አበቦችን እየቆረጡ በልዩ ልዩ መልክ እያሠሩ ያበረክቱ እንደ ነበር.. ይጠቅሳል፡፡
አበባ የመስጠት ልማዱ በህዝብ ዘንድ የተወሰነ ሣይሆን ..ከዚያም አልፎ ሕዝብ እና ካህናት በአንድነት ሁነው ለንጉሣቸው እና ለንግሥታቸው በክብር ምልክታቸው ወይም በዘውዳቸው አምሳል አበቦችን እያሠሩ ወደ ቤተ መንግሥታቸው እየሄዱ.. አበባን ያበረክቱ እንደ ነበር ያወሳው የዝግጅት ክፍሉ፤ ..ይህም የአበቦች በዓል በቤተ ክርስቲያን ቋንቋ ዓፄ መስቀል የሚል ስያሜ ይዞ እናገኘዋለን.. ይላል፡፡ በዚሁ ጊዜ ..ተቀጸል ጽጌ አፄጌ.. የሚል እና ሌላም እሱን የመሰለ መዝሙር በመዘመር ደስታቸውን ከፍ ባለ ሁኔታ ይገልጡ እንደ ይጠቅሳል፡፡
..ይህ ልማድ መቼ እንደ ተጀመረ ለማወቅ እጅግ አዳጋች ነው.. የሚለው ፅሑፍ፤ ..የሰው ስሜት ሥነ ጥበብን ማጥናት ከጀመረባት ጊዜ አንሥቶ ነው ብንል የተሻለ አስተያየት መስሎ ታይቶናል.. ሲል ይደመድማል፡፡ የአበቦች በዓል ከውበት አንጻር ብቻ ታይቶ የሚከበር ሳይሆን የሰውን ህይወት በምሳሌነት የሚያስረዳ ከመሆኑ አንፃር የሚከበር በዓል መሆኑን ጠቅሷል፡፡
የአበቦች በዓል ሲከበር ሁለት ነገሮች እንደሚታሰቡ Ahùû ይገልፃል - ሞትና ትንሣዔ፡፡ ስለዚሁ ጉዳይ ሲያብራራም ..አበባ የተሰጠው ሰው# የወዳጁ፣ የዘመዱ መታሰቢያ በመሆኑ በአበቦች ማስቀመጫ አድርጎ፤ ውኃ ጨምሮ ለብዙ ጊዜ እንዲቆይለት ሲጣጣር እንደዚያ አምሮ፤ ለምልሞና ሠምሮ የነበረው ውበቱ እልም ብሎ ጠፍቶ ሲረግፍና እንደ ቆሻሻ ነገር ተጠርጎ ወደ ጓሮ ሲጣል እያዩ እጅግ ያዝኑ ነበር.. ይላል፡፡
ዝግጅት ክፍሉ ይህን ካለ በኋላ ..መለስ ብለው ምሳሌውን ለራሳቸው አድርገው ወስደው እኛስ ብንሆን ምንድን ነን? እነሆ ዛሬ አምረን፣ ሠምረን፤ ቆንጅተን ለተመልካች አስደስተንና አስጎምጅተን፤ ቤታችን ደምቆና ሞቆ እንታያለን፡፡ ግን ... እንደ አደይ አበባ በድንገት ጠውልገን፤ ደርቀን፤  ውበታችን ተለይቶን፤ ቀልተን የነበርነው፣ ጠቁረን፤ ጠንካሮች የነበርነው፣ ደክመን፤ መናገር፣ መራመድ፣ መንቀሳቀስና ማየት ተስኖን፤ በጠቅላላው ሰውነታችን አልታዘዝ ብሎን፤ እንደቀላልና እንደ ትንሽ ዕቃ በወዳጆቻችንና በዘመዶቻችን  ከሞቀው ቤታችን ወጥተን፣ በጣም ወደ ቀዘቀዘው፤ በርና መስተዋት ወደ ሌለበት ወደ መቃብር የምንሄድ ከሆነ፣ እኛስ ከአበቦች የምንለይበት ምክንያት xlN)!´ b¥lT bxbÆW Múl¤nT ህይወታቸውን እንደሚመለከቱ ያብራራል፡፡
ዝግጅት ክፍሉ ባቀረበው ፅሁፍ ሰዎች ..የአበቦቹን ሁኔታ ተመልክተው፤ ለውጡን ተረድተው የአበባ በዓልን ባከበሩ ቁጥር ይህን ሐሳብ በልቡናቸው ሳያወጡትና ሳያወርዱት ፈጽመው አያልፉም ነበር.. ይላል፡፡
ይህ ሞትን እንዲያስቡ የሚያደርግ አንደኛው የአበባ ምሳሌ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የአበባውን ..ፈጥኖ ጠውልጎ መጥፋት አይተው ሲያዝኑ፤ ቀረ ጠፋ ብለው ሲያስቡ ተመልሶ ሰዓቱንና ቀኑን ቆጥሮ፤ ሳያፋልስ ሲመላለስና በየዓመቱ ሲያስደስታቸው ተመልክተው፣ ትንሣኤ ሙታን መኖሩን ተገንዝበው ‘ysW ልጅ ፈርሶ በስብሶ አይቀርም ይነሣል፤ ክብሩን እንደገና YlBúL’.. የሚል ተስፋ ይይዙ እንደነበረ ፅሁፉ ያመለክታል፡፡ ዝግጅት ክፍሉ ባቀረበው በዚሁ Ah#F# ከልደተ ክርስቶስ በፊት የነበሩት ሰዎች እንኳን ሳይቀሩ የአበባን ሁኔታ በማየት ትንሣኤ ሙታንን ተቀብለውና አምነው እንደኖሩ ይገልፃል፡፡ ..ከዚህም አልፈው የአበቦችን ውበት፤ የውሆችን አፈሳሰስ፤ የመዓልትና የሌሊትን፤ የበጋና የክረምትን ለውጥ በመመልከት ፍጡራንን አልፈው፤ የእግዚአብሄርን መኖር ተረድተው ከአምልኮ ጣዖት ባርነት ነፃ የወጡ ሰዎች ቁጥር እጅግ በርከት ያለ ነበር.. በማለት ይቀጥላል፡፡
አያይዞም ..አሁንም ቢሆን ይህንን የአበባ በዓል ስናከብር የአባቶቻችን ኅሊና ሲዋኝበት ወደኖረው ወደ መመራመርና አበቦችን ሳይሆን በብዙ ኅብርና ጥበብ የፈጠራቸውን አምላክ ወደ ማመስገን ባሕር ገብተን እንድንንሳፈፍ እንጠየቃለን.. የሚለው ይህ ጽሁፍ፤ የአበቦች በዓል ..ዓፄ መስቀል.. ለምን እንደ ተባለ ሲገልፅ፤ የአበባ በዓል በልዩ ልዩ አህጉር ሲከበር የቆየና በሀገራችንም እንግዳ እንዳልሆነ አመልክቷል፡፡ በነገሥታቱም ሆነ በደሀው ቤት ይከበር የነበረ በዓል መሆኑንም ከጠቀሰ በኋላ# ከአፄ ገብረ መስቀል ታሪክ ጋር የሚያያዝበት ጉዳይ መኖሩን አመልክትዋል፡፡ ..እንደ እኛ ቤተ ክርስቲያን አነጋገር በ524 ዓ.ም ግድም ዓፄ ገብረ መስቀል የተባሉት ኢትዮጵያዊ ገናና ንጉሥ ነግሠው ነበር፡፡ እኒህ ንጉሥ ከጀግንነታቸውና ከሀገር ፍቅራቸው ሌላ ሙዚቃ ይወዱ ነበር፡፡
..በዘመናችው ያሬድ የተባለው ኢትዮጵያዊ ሊቅ ኑሯል፡፡ እርሳቸው ይህንን የተማረ ሊቅ ወደ ቤተ መንግሥታቸው እያስጠሩ በየጊዜው ልዩ ልዩ ዜማዎችን እያሰማ ልቡናቸውን በጣዕመ ዜማ ሲያረካቸው ኑሯል፡፡
ታዲያ ወደ ቤተመንግስት በመሄድ በአበቦች በአል ዕለት ለነገስታት ዝማሬ ማቅረብ በቅዱስ ያሬድ እንዳልተጀመረ የሚያወሳው ይህ ፅሁፍ፤ ሆኖም ስርአት እና መልክ የያዘው በቅዱስ ያሬድ ጥበብ እንደሆነ ይጠቁማል፡፡ ስለዚሁ ጉዳይ ሲያብራራም ..ከዚያ በፊት ሕዝቡ በስድ ንባብ ወይም ባልተቃና ዜማ ሲጠቀምበት የነበረውን የደስታ መግለጫ ቃል ቅዱስ ያሬድ በአማረና በለዘበ ዜማ አዚሞታል..... sþL YtRµLÝÝ
..ከዚያ ሲያያዝ በመጣው ልማድ መሠረት... ካህናት ዜማውን በማለዘብ በልዩ ዘዴ የተጌጠውን ቀጭን ኩታና ካባ ለብሰው በንጉሠ ነገሥቱ ፊት ቆመው በመዘመርና ልዩ ልዩ ተሐውሶዎችን በማድረግ የሚያሳዩት ውዝዋዜ ቀላል አይደለም፡፡ የብዙዎችን የውጭ አገር ተመልካቾች ልቡና ማርኳል፡፡ ያላዩትም እንግዶቻችን ለማየት ሲሉ ከሩቅ አገራቸው ተነሥተው ብዙ ወጭ አድርገው እንዲመጡና እንዲመለከቱ ግድ ሆኖባቸዋል.. ይላል፡፡ ይህም በዓል እስከ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ድረስ ሲከበር መቆየቱን ይጠቅሳል፡፡
በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ክረምቱ የሚጀምረው ወይም ..በዓተ ክረምት.. የሚሆነው ሰኔ 25 እንደሆነና ክረምት የሚወጣው ወይም ..ፅዓተ ክረምት.. የሚሆነው ደግሞ መስከረም 25 መሆኑን የጠቀሰው ይኸው ፅሁፍ፤ ..የአበባ በዓልም ለብዙ ጊዜ መስከረም 25 ሲከበር ኑሯል.. ይላል፡፡ ነገር ግን ይህ የአበባ በዓል በአፄ ዳዊት ዘመነ መንግሥት ከመስከረም 25 ወደ መስከረም 10 እንደ ተዛወረ እና የበዓሉም ስም ..ተቀጸል ጽጌ፤ ዓፄ መስቀል.. ተብሎ መሰየሙንም ያመልክታል፡፡ ለውጥ የተደረገበትንም ምክንያት ሲያብራራ ..አፄ ዳዊት የጌታ ግማደ መስቀሉ ከኢየሩሳሌም እንዲመጣላቸው ጠይቀው ከብዙ ድካም በኋላ መስከረም 10 ቀን ደርሶላቸው ክርስቲያናዊ መንፈሳቸው በጣም ተደስቶ ታላቅ በዓል ማድረግ ጀመሩ፡፡ በዚህ ጊዜ መኳንንቱና ካህናቱ በአንድ ወር ውስጥ ሁለት በዓል ማድረግ አስቸጋሪ መሆኑን ተገንዝበው የጥንቱ በዓል የሚከበርበት ቀን ተለውጦ ከአዲሱ ከመስቀል በዓል ጋር አጣምረው በአንድነት እንዲከበር ወስነዋል፡፡
..ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የጥንቱ የአበባ በዓልና የመስቀል በዓል በአንድነት ሲከበሩ ኖረዋል፡፡ ስማቸውም የሁለቱም ሳይቀር አንድ ጊዜ ‘xÉ@ መስቀል’ አንድ ጊዜ ‘tq[L ጽጌ’ በመባል ቆይቷል.. ይላል፡፡
ጽሁፉ አክሎ ..በተለይ መስከረም 10 ቀን ‘ ብለን የምናከብረው ከጥንት ሲያያዝ የመጣውን የሰሎሞንን ታሪክና መጽሐፍ በመመልከት ነው፡፡ ሰሎሞን የአባቱን መንግሥት እጅ ካደረገና ሕዝቡም እንደተቀበሉት አይቶ የክረምት ወራት አልፎ የበጋ ወራት የሚጀመርበትን የመጀመሪያውን ዘመን ያከብረውና ያስከብረው ነበር.. ይላል፡፡
ስለ አከባበሩ ሁኔታ ሲያትትም፤ ..ንጉሡ ሰሎሞን አምስት መቅረዝ በቀኝ፤ አምስት መቅረዝ በግራ የሚገኝባት ተቅዋም አሠርቶ እሱ ከመካከሏ ይቀመጣል፡፡ ልብሰ መንግሥቱንም ለብሶ ለሕዝቡና ለመኳንቱ ይታይ ስለነበር ህዝቡ ተሰብስበው ካህናቱም ተስማምተው ‘tq[L ጽጌ’ ብለው አመስግነውታል፡፡ አምስት መቅረዞች በስተቀኝ፤ አምስት መቅረዞች በስተግራ ከፍ ባለ ሥፍራ ፊት ለፊት ከአበቦችና ከማብሪያዎችም፤ ከመኮስተሪያዎቸም ጋራ ሁሉን ከጥሩ ወርቅ አደረገ ይላል (
ነገሥት 7፤ 49):: ነገሥታቱ ይህን በዓል ከፍ ባለ ክብር ማክበራቸው በዚህ ዘመን ጽጌያት በአማረ አበባና በመልካም ሽታ አጊጠውና አሸብርቀው ስለሚታዩ ነው፡፡ በዚሁ ዕለት ነገሥታቱም ልብሰ መንግሥትታቸውን ለብሰው እንደ ጽጊያት አብበውና አሸብርቀው ከፍ ባለ አክብሮት ለሕዝቡና ለካህናቱ ይገለጣሉ፡፡ ሕዝቡም ‘ዘመነ#N ዘመነ ሰላም፤ ዘመነ ተድላ ያድርግልን፤ ለንጉሣችንም ዕድሜና ጤና YS_LN’ ይላሉ፡፡ ወዲያው ካህናቱ ልብሰ ተክህኖ ለብሰው፤ መዘምራኑም ለበዓሉ ተስማሚ የሚሆነውን ቀለም ከመጽሐፍ ቅዱስ እያውጣጡ ጣዕም ባለው ዜማ ሲያሸበሽቡ ይውላሉ፡፡ ይህን አርዓያና ምሳሌ በመከተል የኢትዮጵያ ነገሥታት መስከረም 10 ቀን ወርቅና ብር የተሳለባቸውን ልብስ ለብሰው፤ በዙሪያው አበባ የፈነዱበትን መጎናጸፊያ ተጎናጽፈው፤ ከፍ ባለ ቦታ ላይ ሁነው ለሕዝቡ ይታያሉ.. ሲል ሀተታውን ይደመድማል፡፡

 

Read 3981 times Last modified on Saturday, 24 September 2011 09:06