Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 16 June 2012 09:31

የዝነኞች ጥግ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ሁሉም ተዋናይ ቢያንስ አንድ ጊዜ ፊልም ዳይሬክት ማድረግ አለበት - በፊልም ሥራ ወቅት ያለውን

ችግር የመረዳት ትዕግስት እንዲላበስ፡፡ በእርግጥ ሁሉም ዳይሬክተርም መተወን አለበት፡፡

ክሊንት ኢስትውድ

(አሜሪካዊ የፊልም ተዋናይና ዳይሬክተር)

ስለተመልካቾች

ሙዚቃ ስጫወት ተመልካቹ ካንጓጠጠኝ ሙዚቃውን እየተሳደበ ነው፤ ስለዚህ መጫወቱን

አቆማለሁ፡፡ ሙዚቃ መስማት ካልፈለጉ እኔ ለምን እጫወታለሁ? ተመልካቹ እኔ ስጫወት ለማየት

መርጦኝ መጣ እንጂ እኔ ተመልካቹን አልመረጥኩትም እኮ!

ኒና ሲሞኔ (አሜሪካዊ ጃዝ ዘፋኝ፣

ፒያኒስትና የዘፈን ግጥም ደራሲ)

ሁለት ዓይነት ተመልካች ብቻ ነው የማውቀው - አንድ የሚያስልና አንድ የማያስል፡፡

አርተር ሽናቤል

(ኦስትሪያዊ ፒያኒስትና አቀናባሪ)

በጣም አታጨብጭቡ፤ ህንፃው በጣም አሮጌ ነው፡፡

ጆን ኦስቦርን

(እንግሊዛዊ የፊልምና የቴአትር ደራሲ)

በተቻለ መጠን ተመልካቹ እንዲሰቃዩ አድርግ፡፡

አልፍሬድ ሂችኮክ (ትውልደ - ብሪትሽ

አሜሪካዊ ኮሜዲያን እና የፊልም ተዋናይ)

ሁልጊዜ በእንግሊዝ ተመልካች ፊት መቅረብ ያስደስተኛል፡፡ መሳቅ ባይፈልጉ እንኳን ነገርዬው

እንደገባቸው ጭንቅላታቸውን በመነቅነቅ ያሳያሉ፡፡

ቦብ ሆፕ (ትውልደ - ብሪትሽ አሜሪካዊ

ኮሜዲያን እና የፊልም ተዋናይ)

ሁልጊዜ ፊልም ዳይሬክት ሳደርግ ተመልካቹን አስባለሁ - ምክንያቱም ተመልካቹ እኔ ነኝ፡፡

ስቲቨን ስፒልበርግ

(አሜሪካዊ የፊልም ዳይሬክተር)

 

 

Read 2066 times Last modified on Saturday, 16 June 2012 09:58