Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 13 August 2011 10:06

አምስቱ ምርጥ የኢትዮጵያ አይዶል ተወዳዳሪዎች ይለያሉ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

በ2001 ዓ.ም. ተጀምሮ በአዲስ አበባና በየክልል ከተሞቹ ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያን አይዶል ውድድር እነሆ ወደመቋጫው ተቃርቧል፡፡ በስድስት ዙሮች የተካሄደውን የድም ውድድር አሸንፈው ለሰባተኛው ዙር ያለፉት አስር ተወዳዳሪዎችም ተመርጠዋል፡፡ የሐረሯ ተወዳዳሪ ህፃን ሃና ግርማ በልዩ ተወዳዳሪነት ለሰባተኛውና ምርጥ አምስቱ ብቻ ለሚመረጡበት ዙር በማለፍ yተወዳዳ ቁጥር አስራ አንድ አድርሳዋለች፡፡

ጠንከር ያለ ውድድር ታይቶበታል በተባለው የዘንድሮው የአይዶል ውድድር፣ ዳኝነቱንና አጠቃላይ የውድድር ሂደቱን አስመልክቶ ለምርጥ አስር ከተመረጡት አስር ተወዳዳሪዎች፣ ከውድድሩ ዳኞችና ከሙዚቃ ባለሙያዎች ጋር የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ መታሰቢያ ካሳዬ ቆይታ አድርጋለች፡፡
..በውድድር ያመለጠኝን የመሰናዶ ፈተና በቀጣዩ ዓመት እወስዳለሁ.. ዳዊት አለማየሁ (ውቅሮ)
በዘንድሮው ውድድር ከ38 ሺ በላይ የህዝብ ድም በማግኘት የመሪነቱን ስፍራ የያዘው የውቅሮው ተወዳዳሪ ዳዊት እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ያለው ትምህርቱን የተከታተለው የደረጃ ተማሪ ሆኖ ነው፡፡ በአብዛኛው ዙር ውድድሮች በሙሉቀን ዘፈኖች ሲወዳደር የቆየው የአስራ ስድስት ዓመቱ ታዳጊ ወጣት፤ በስድስተኛው ዙርና ምርጥ አስሮች በተመረጡበት ውድድር የዳኞችን ግሳና ማስጠንቀቂያ ተቀብሎ ምርጥ አስሮቹን ተቀላቅሏል፡፡ ..ባለፈው ዙር ውድድር ታምሜ ለጥቂት ቀናት ተኝቼ ነበር፡፡ ድምም ልክ አልነበረም፡፡ ልምምድ እንኳን ያደረኩት ለሁለት ቀናት ብቻ ነው፡፡ በውድድሩ አሸንፌ ምርጥ አስሮቹን እቀላቀላለሁ ብዬም አላሰብኩም ነበር፡፡ አሁን ግን በጥሩ ብቃት ጥሩ ልምምድ እያደረኩኝ በመሆኑ አሸንፋለሁ ብዬ አስባለሁ.. ይላል፡፡ በዘንድሮው ዓመት በአይዶል ውድድር ምክንያት የተስተጓጐለውን የመሰናዶ ትምህርት ፈተናውን በቀጣዩ ዓመት በሙሉ ልቡ እንደሚወስደውም አጫውቶናል፡፡

  • ..ዳኞቹ አንዳንዴ እንደ ጀማሪ አያዩንም..

ይድነቃቸው ገለታ (አ.አ)
እዚሁ አዲስ አበባ ሽሮ ሜዳ አካባቢ ተወልዶ አደገ፡፡ ከልጅነቱ ጀምሮ አጥብቆ ይወደው ወደነበረው የሙዚቃ ሙያ ለመግባት አቋራጩ መንገድ የኢትዮጵያ አይዶል ውድድር መሆኑን በማመኑ በሁለተኛው የአይዶል ውድድር ወቅት ለተሳትፎ ገባ፡፡ ውጤት ባይቀናውም ለቀጣዩ ውድድር ጥሩ ተፎካካሪ ሊሆን የሚችልበትን ልምድ አግኝቶበታል፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት በተጀመረው በዚህ በ3ኛው የአይዶል ውድድር በጥሩ ፉክክር ከምርጥ አስሮቹ ውስጥ ለመግባት በቅቷል፡፡ የዘንድሮውን የአይዶል ውድድር ቀደም ካሉት ውድድሮች ጋር ሲያነጻጽረው ይኸኛው ለየት ያለ መሆኑን ይናገራል፡፡ ከተወዳዳሪዎች ጠንካራነት፣ ከዳኞቹ አቅም ከፍተኛነት በላይ ኦርጅናሊቲን በመጠበቁ ረገድ የዘንድሮው በጣም ይለያል ይላል””|በዚህ የውድድር ዘመን ዘፋኞቹን አስመስሎ መጫወት በጣም ክልክል ነው፡፡ የራስን ማንነት የመፈለግና የማግኘት ጉዳይ ነው ያለው፡፡ ይህ ደግሞ በነጻነት የማንንም ሥራ ለመሥራት እንድንችል አድርጐናል፡፡ ዳኞቹ የሚሰጡን አስተያየት ከዙር ዙር ለምናደርገው መሻሻል በጣም ጠቅሞናል፡፡ በዳኞቹ አቅምና ችሎታ ላይ አንዳችም ጥርጣሬ የለኝም፡፡ ግን አንዳንዴ እኛን እንደ ጀማሪ አያዩንም፡፡ ልጁ በውድድሩ ላይ ባሳያቸው ሥራዎች ነው አቅሙ መለካት ያለበት እንጂ ከኦርጅናል ዘፋኞች ጋር እሱን ማነጻር ተገቢ አይመስለኝም ይላል አስተያየቱን ሲሰጥ፡፡ የዘንድሮው የአይዶል ውድድር ከዳኝነቱ፣ ከተወዳዳሪዎቹ ጠንካራነት፣ ከዘፈን አመራረጡና በአጠቃላይ ከውድድሩ ይዘት አንፃር ሲታይ ከቀድሞዎቹ እጅግ የተለየ መሆኑንም ይገልፃል፡፡


..ድም የሚመቸውን ዘፈን መርጫለሁ..

ከልጅነቷ ጀምሮ ፍላጐቷና ስሜቷ ለውጪ ዘፈኖች ያደላል፡፡ በቴሌቪዥን የምትመለከታቸው የውጪ ዘፋኞችን ዘፈኖች ስታቀነቅን ያዩ ጓደኞቿና ቤተሰቦቿ ወደ ውድድሩ እንድትገባ ያበረታቷት ነበር፡፡ በዘንድሮው የአይዶል ውድድር በከፍተኛ ውጤት ወደ ምርጥ አስሮቹ ከገቡት ተወዳዳሪዎች አንዷ የሆነችው ዮሐና፤ ዳኞቹ በውድድሩ ላይ ይሰጧት የነበረው አስተያየት እጅግ እንደጠቀማት ትናገራለች፡፡
..ይሰጠን የነበረው አስተያየት ወደ ጥሩ ዘፋኝነት የሚመራ መንገድ ነበር፡፡ በዳኞቹ እውቀትና ችሎታ ላይ ፈጽሞ አልጠራጠርም፡፡ ጐበዞች ናቸው.. ትላለች፡፡ ለነገው የምርጥ አምስቶቹ ውድድር የግርማ በየነን ..መጀመሪያ አንቺን ሳገኝ ተሳስቼ.. የሚለውን ዜማ እንደመረጠችና ዜማው ከድም ጋር እንደሚስማማ ትናገራለች፡፡ መድረክ ላይ ፍርሃት ካልገጠማትም በውድድሩ እንደምታሸንፍ እርግጠኛ ነች፡፡



..ድም ያላቸው ልጆች ሲወድቁ ሳይ ብልጥ መሆን እንዳለብኝ ገባኝ.. ይርጋ ሁናቸው (ባህር ዳር)

በባህር ዳር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በላብራቶሪ ቴክኒሺያንነት ትምህርቱን ይከታተል በነበረበት ወቅት ነው ወደ ውድድሩ የገባው፡፡ በውድድሩ የመቀጠል ሀሳብ ባይኖረውም በየዙሩ የሚደረጉትን ውድድሮች ማለፉ ስሜቱ ወደዛው እንዲሳብ አደረገው፡፡ ትምህርቱን አጠናቅቆ ሲመረቅም በአንድ ልቡ ትኩረቱን ውድድሩ ላይ አደረገ፡፡ ከአራተኛው ዙር በኋላ ውድድሩን በአሸናፊነት ያጠናቅቃሉ ብሎ የሚያስባቸው ልጆች ዙሮቹን ማለፍ እያቃታቸው ሲወጡና እሱ ሲያልፍ የተሻልኩ ነኝ እንዴ እያለ ማሰብ ጀመረ፡፡ በጓደኞቹና በአወዳዳሪ ዳኞቹ የሚሰጡትን አስተያየቶች መቀበልና ሥራ ላይ ማዋል የጀመረውና የውድድር መንፈስ እያደረበት የሔደውም ያኔ ነው፡፡ ..ድምጻዊ ብቻ መሆን በውድድሩ ላይ ለመቆየት እንደማያስችል የገባኝ ቆይቶ ነው፡፡ በጣም ድም አላቸው ብዬ የማስባቸው ልጆች በየዙሩ እየወደቁ ሲመጡ ብልጥ መሆን እንዳለብኝ ማሰብ ጀመርኩ፡፡ የምመርጠው ሙዚቃ ከእኔ ጋር መሔድ መቻል አለመቻሉን በሚገባ ማወቅ እንዳለብኝ ገባኝ፡፡.. ይላል፡፡ ተወዳዳሪዎቹ ያላቸው የእርስ በርስ መግባባትና ፍቅር እንደሚያስገርመውም ይርጋ ይናገራል፡፡ ..አንዳንዴ ልምምድ ስናደርግ ዳኞች እየመጡ ያዩናል፡፡ እዛው ዝም ብለው አይተው የሚሰጡትን አስተያየት ሰምተን ለተወዳዳሪው ጓደኛችን ለመንገር የምናደርገው ችኰላ ውድድር ላይ መሆናችንን ሁሉ ያስረሳናል፡፡ እሱ ቢያልፍ እኔ ልወድቅ እንደምችል ሁሉ ረስቼ እስክነግረው እቸኩላለሁ፡፡ ይኼ ነገር ሁሌም ያስገርመኛል.. ይላል፡፡ ይርጋ ሰባተኛውን ዙር ውድድር ..አሣው ተከማችቶ.. በሚለው የቴዎድሮስ ታደሰ ዘፈን ለማድረግ ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

..የጠፈር ተመራማሪ መሆን እፈልጋለሁ..
ህፃን ሐና ግርማ (ሐረር)
በቲቪ መስኮት ያያት ሁሉ በህፃኗ ኦፔራ ተጫዋች እጅግ ይደነቃሉ፡፡ በህፃን አንደበቷ የምትጫወተው የኦፔራ ሙዚቃ የአይዶል ውድድርን ተወዳጅ ለማድረግ የበኩሉን አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ የአስራ አንድ ዓመቷ የአይዶል ልዩ ተወዳዳሪ ህፃን ሐና ግርማ ከህፃንነት ዕድሜዋ ጀምራ የቶም ኤንድ ጄሪ ፊልሞች ላይ የሚሰሙትን የኦፔራ ሙዚቃዎች ትወድ እንደነበርና ቤተሰቦቿ በተለይም የዩኒቨርስቲ ተማሪ ወንድሟ ታደሰ ግርማ ለውድድሩ እንድትበቃ ያበረታቷት እንደነበርም ትናገራለች፡፡ ለትምህርቷ ልዩ ትኩረት እንደምትሰጥ የምትናገረው ሐና፤ ዘንድሮ ወደ ሰባተኛ ክፍል ማለፏንና የደረጃ ተማሪ መሆኗን አጫውታኛለች፡፡ትኩረቴን ሁሉ ወደ ሙዚቃው ማድረግ አልፈልግም፡፡ ትምህርቴ ላይ ነው ማተኰር የምፈልገው፡፡ ለእኔ ሙዚቃ ሆቢዬ ነው፡፡ የምደሰትበት ነገር ስለሆነም ሙዚቃን መተውም አልፈልግም፡፡ በትምህርቴ ግን ጠንክሬ የጠፈር ተመራማሪ የመሆን ምኞት አለኝ ትላለች፡፡
..የዘንድሮው ውድድር በየክልል ላሉት ልጆች እድል ሰጥቷል.. ተመስገን ታፈሰ (ከሚሴ)

ከአዳማ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት ሙያ በዲግሪ ተመርቆ ጐሃ ጽዮን እየተባለች በምትጠራው ከተማ ውስጥ በሚገኝ አንድ ትምህርት ቤት በስፖርት መምህርነት እያገለገለ የሚገኘው የከሚሴው ተወዳዳሪ ተመስገን ታፈሰ፤ የዘንድሮው የአይዶል ውድድር ችሎታ ኖሯቸው ገንዘብ ለሌላቸው የክልል ተወዳዳሪዎች እድል የሰጠ መሆኑን ይገልጻል፡፡
የውድድሩ ዳኞች በሙያው የበሰሉና ከፍተኛ እውቀት ያላቸው ወጣቶች መሆናቸውን የሚናገረው ተመስገን፤ ዳኝነቱን ይሰጡ የነበረው በቲኦሪ ብቻ እንዳልነበርና እንዴት መሆን እንደነበረበት ጭምር ተግባራዊ አስተያየት ይሰጧቸው እንደነበር ይናገራል፡፡ ይህም በየዙሮቹ ለነበረው መሻሻል ትልቅ አስተዋጽኦ እንደነበረውም ተመስገን ይገልጻል፡፡

..አይዶል ዕውቅና ሰጥቶኛል.. ዮሐንስ ግርማ (አ.አ)የሙዚቃ ሥራን የጀመረው በ1997 ዓ.ም. ነው፡፡ ለህፃናት ልማትና ዕድገት ድርጅት ፈቃደኛ ሆኖ በሙዚቃ ሥራ ያገለግል ነበር፡፡ በኢትዮጵያ አይዶል ውድድር ውስጥ ከገባ ጊዜ ጀምሮ ያገኘውን ትምህርት በህይወቱ ካጋጠሙት ሁሉ የላቁ ናቸው ይላል፡፡ ..ዳኞቹ በሥራዬ ላይ የሚሰጡኝ አስተያየቶች ሁሉ እስኪገርሙኝና ይህ ሁሉ ስህተት እኔ ላይ ያለ ነው እስክል ድረስ አድርጐኛል፡፡ ምን ያህል ጠቀሜታ እንደሰጠኝም መግለጽ አልችልም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በውድድሩ ውስጥ ከመግባቴ በፊት የነበረው ህይወቴና ዛሬ ያለሁበት ህይወቴ በእጅጉ ይለያያሉ፡፡ አይዶል እውቅናንም ሰጥቶኛል.. የሚለው ተወዳዳሪው፤ ለቀጣዩ የምርጥ አምስቶቹ ውድድር የወንድሙ ጅራን ..ውቢት.. የተሰኘ ዜማ እንደመረጠ ይናገራል፡፡

|ስለ
ንጐራጐር እንጂ ስለ መዝፈን አላውቅም ነበር.. ማስተዋል እያዩ (ባህርዳር)

የባህር ዳሩ ተወዳዳሪ ማስተዋል እያዩ የዘንድሮው የአይዶል ውድድር ትልቅ ትምህርት ያገኘበትና ራሱን የፈተሸበት ውድድር እንደነበር ይናገራል፡፡ወደ ውድድሩ ስገባ ስለ እንጂ ስለመዝፈን አንዳችም እውቀት አልነበረኝም፡፡ መዝፈን የሚለውን ሙያዊ ነገር ያስተማሩኝ ዳኞቹ ናቸው ይላል፡፡ የፕሪፓራቶሪ ተማሪው ማስተዋል የዘንድሮው ውድድር ቢሳካና ቢያሸንፍ የኢትዮጵያን የሙዚቃ ኢንዲስትሪ በአንድ ደረጃ ከፍ የማድረግ ህልም እንዳለው ይናገራል፡፡


..ዳኞቹ ስህተታችንን በቲኦሪ ብቻ አይደለም የሚነግሩን፤ በተግባርም ያሳዩናል..ዮናስ ግዛው (አ.አ)

በሁለተኛው የአይዶል ውድድር ተወዳድሮ በአራተኛነት ደረጃ ውድድሩን ላጠናቀቀው የጉርድ ሾላው ዮናስ የዘንድሮው ዳኞች ከቀድሞዎቹ ለየት ብለውበታል፡፡
..ዳኞቹ ሥራችን ላይ የሚሰጡን አስተያየት በጣም ሙያዊ ነው፡፡ ስንሳሳት ስህተታችንን መንገር ብቻ ሳይሆን እንዴት ማድረግ እንደነበረብንም ጭምር ነው የሚያሳዩን፡፡ ይህም የዳኞቹን አቅምና በራስ መተማመን የሚያሳይ ነው የሚል እምነት አለኝ.. ይላል፡፡
ዮናስ በውድድሩ ወቅት በየዙሩ ላሳያቸው መሻሻሎች ዳኞቹ የሚሰጡት አስተያየት በእጅጉ እንደጠቀመውም ይናገራል፡፡ የእንግሊዝኛ መምህሩ ዮናስ እስከዛሬ የነበሩትን ውድድሮች በቴዎድሮስ ታደሰና በመሀሙድ ዘፈኖች ነበር የተወዳደረው ምርጥ አምስቶቹ ለሚመረጡበትና ነገ ለሚካሄደው ሰባተኛው ዙር ውድድር ደግሞ የማዲንጐ አፈወርቅን ..ማህሌት.. የተሰኘ ዜማ እንደሚያቀርብ ይናገራል፡፡

Read 3824 times Last modified on Saturday, 20 August 2011 12:10