Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 13 August 2011 09:37

የሆሊውዱ ጉድ ጎልጋይ በወህኒም ስራውን ቀጥሏል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በሆሊውድና በአሜሪካ መዝናኛ ኢንዱስትሪ ያሉ ዝነኞችን ገበና በመፈልፈል የሚታወቀው አንቶኒዮ ፔሊካኒ በወህኒም የተለመደ ስራውን እንደገፋበት ኒውስዊክ ገለፀ፡፡ ፔሊካኒ የዝነኞችን ምስጥራዊ ሰነድ በመፈልፈል፤ ስልክ በመጥለፍና የደህንነት መረብን ሰብሮ በመግባት አደገኛነቱ የተመሰከረለት ጉድ ጎልጓይ ጋዜጠኛ ነው፡፡ በሎስአንጀለስ ከተማ በግል መርማሪነት ይሰራ የነበረው ፔሊካኒ ከ3 ዓመት በፊት ጥፋተኛ ሆኖ በተገኘባቸው 76 ወንጀሎች የ15 ዓመት ኑ እስራት ተፈርዶበት በወህኒ ቤት ይገኛል፡፡

በወህኒ ቆይታው ዝነኞች ገበናቸውን እንዲሸሽግላቸው፣ የፍትህ አካላት ደግሞ እንዲያጋልጥ በሚያደርጉት ጉትጎታ መቸገሩን ከኒውስዊክ ጋር ባደረገው ሰፊ ቃለምልልስ የተናገረው ፔሊካኒ፤ ትላልቅ የሚዲያ ተቋማት በእጁ ያሉትን ምስጥራዊ መረጃዎች እንዲሰጣቸው ደጅ ጥናት እንዳበዙ ገልል፡፡ ከፔሊካን ደንበኞች ከነበሩት መካከል ሸዋዚንገር፣ ማዶና፣ ማይክል ጃክሰንና ሌሎችም ይገኙበታል””በወህኒ ቤት በየቀኑ በመቶዎች በሚቆጠሩ ሰዎች እየተከበበ ቢሆንም የህይወት ታሪኩን የያዘ መጽሐፍ ለማዘጋጀት ጥረት እያደረገ መሆኑን የገለፀው አንቶኒዮ ፔሊካኒ፤ የተወሰነበት የእስር ቅጣት ተገቢ እንዳልሆነ የሚገልጽ ባለ 86 ገ ደብዳቤ አዘጋጅቶ ፍ/ቤት ይግባኝ ብሏል፡፡ ይግባኙ ተቀባይነት አግኝቶ የተበየነበትን እስር ከመጨረሱ ስድስት ዓመት ቀደም ብሎ በ2013 እ.ኤ.አ ላይ በነፃ እለቀቃለሁ የሚል ተስፋ እንዳለው ፔሊካን ተናግሯል፡፡ የ67 ዓመቱ ፔሊካኒ የፍርድ ብይን ያልተሰጠባቸው ከ30 በላይ የፍትሐብሔር ክሶች እንዳሉበትም ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

Read 2445 times Last modified on Saturday, 13 August 2011 09:39