Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 12 May 2012 10:43

..ከ90 በላይ የሆኑትን የእናቶች ሞት ምክንያት ለማስወገድ ...

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በኢትዮጵያ ቅድመ ወሊደ የህክምና አገልግሎት ያገኛሉ የሚባሉት እናቶች ከአጠቃላዩ ሲታይ ወደ 80  አካባቢ ናቸው፡፡ ይህም ቁጥር ባለፉት ጥቂት አመታት ውስጥ እየጨመረ የመጣ ሲሆን ይህም በአገር ደረጃ የተሰማሩ የጤና ኤክስንሽን ባለሙያዎች በጤና ኬላዎች እና እናቶች ባሉበት ቦታ ሁሉ በየመኖሪያ ቤቱ ጭምር አገልግሎቱን መስጠት በመቻላቸው ነው፡፡ ከዛሬ አምስት አመት በፊት የነበረው አገልግሎት ከ30 በታች የነበረ መሆኑ አይዘነጋም፡፡

ዶ/ር ታደሰ ከተማ በኢፊድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስር የእናቶች ጤና አማካሪ

በኢትዮጵያ የእናቶች ሞት ምክንያት ምን እንደሆነ ለመለየትና መፍትሔ ለመስጠት የሚያስችል የዳሰሳ ጥናት በመካሄድ ላይ ነው፡፡ የዳሰሳ ጥናቱን የሚያደርጉት የኢፊድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስ ር ከተባባሪ አካላት ጋር ሲሆን የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበርም በበኩሉ በአጋር ድርጅቶች እገዛ ዳሰሳውን እያካሄደ ይገኛል፡፡ ለዚህ እትም በእንግድነት የጋበዝናቸው አቶ ብሩክ ተ/ስላሴ በኢሶግ የፊጎ ሎጂክ ኢንሼቲቭ የእናቶችና ጨቅላ ሕጻናት ጤና ፕሮጀክት አስተባባሪ እና በኢፊድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስር የእናቶችና ጨቅላ ሕጻናት ጤና ክብካቤ አማካሪ ዶ/ር ብርሀኑ ሰንደቅ ናቸው፡፡ በቅድሚያ ማብራሪያ የሚሰጡት አቶ ብሩክ ተ/ስላሴ ናቸው፡፡

አቶ ብሩክ እንደሚገልጹት አለምአቀፉ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር (ESOG) ከአለም አቀፉ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር (FIGO)  ጋር በመተባበር የእናቶችና  ሕጻናት ጤንነትን በመጠበቅ ረገድ ፕሮጀክት ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ኢሶግ  በተለያዩ መስተዳድሮች አስፈላጊውን ነገር ለማስረጽና ለውጥ ለማምጣት በመስራት ላይ ነው፡፡ በኢትዮጵያ የእናቶችን ሞት በመቀነስ ረገድ ከሚሰራው ስራ አንዱ በአራት ክልሎች ማለትም በአዲስ አበባ ሁለት ሆስፒታሎች በየካቲትና ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታሎች በአማራ ክልል ደብረማርቆስና ደብረብርሀን ፣በደቡብ ደግሞ ቡታጅራ ዱራሜና ሐዋሳ ሆስፒታሎች እንዲሁም በኦሮሚያ በቢሾፍቱ እና አሰላ ሆስፒታሎች ላይ ዳሰሳው በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ እንግዲህ በነዚህ ክልሎች ቅድሚያ ትግበራው ሲካሄድ ቀጣይ ስራውን ደግሞ ሌሎች በዚህ ፕሮጀክት ያልታቀፉት እንደ አንድ ምርጥ ስራ አምነው እንዲሳተፉበት እና ስራው በአገር አቀፍ ደረጃ ውጤታማ እንዲሆን ጥረት እየተደረገ ነው፡፡ ከዚህ ስራ ልምድ በመቅሰምም የአለም የጤና ድርጅት ከአፌድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስነር ጋር በመተባበር በአገሪቱ በሌሎች አርባ የጤና ተቋማት አገልግሎቱን ለማስፋፋት እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡

የመረጃ መሰብሰቢያው ብዙ ነገሮችን ያካተተ ሲሆን ር ...ለምሳሌ ኢሶግ ስራ በጀመረባቸው ዘጠኝ ሆስፒታሎች እናቶች በጠና የሚታመሙበትንና የሚሞቱበትን ሁኔታ ዝርዝር ከታወቀ በሁዋላ የትኞቹ በሽታዎች ለእናቶች ሕመምና ሞት አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ ይለያል፡፡ ለእናቶች ሞት ምክንያት ለሚሆኑት ችግሮች አስተዋጽኦ የሚያደርጉትንም  ምንድናቸው በሚል በሶስት ተከፍሎ እንዲታይ የሚደረግበት ሁኔታ ያ ሲሆን ከዚያም በመቀጠል በየትኛው እድሜ ምን አይነት ሁኔታ ላያ ያሉ ለሕመም እና ሞት ይዳረጋሉ የሚለውን በግልጽ የሚያሳይ በአጠቃላይም ከሁለት መቶ በላይ የሆኑ ነጥቦችን በግልጽ በሚያሳይ ሁኔታ የተዘጋጀ ነው፡፡

እንደ አቶ ብሩክ ማብራሪያ አሁን ስራው ያለበት ደረጃ አስፈላጊውን የመግባቢያ ሰነድ ከሚመለከታቸው የጤና ተቋማት ጋር በመሆን የጋራ መግባባት ላይ ለመድረስ ተችሎአል፡፡ ሁሉም አካላት አምነውበትም ስራ ከተጀመረወራትን አስቆጥሮአል፡፡ አተፐ ብሩክ አክለውም መረጃው የሚሰበሰብበት ምክንያት የእናቶች ሞት ምክንያት ምን እንደሆነ ሙሉ ለሙሉ የማይታወቅ ሆኖ ሳይሆን ነገር ግን አካባቢን ወይንም የአኗኗርን ሁኔታ መሰረት በማድረግ እንዲሁም እንደሀገር ነባራዊ የሆኑ ልምዶችና ባህሎች ታሳቢ ሆነው በተጨማሪም አንዳንድ ለየት ያሉ ነገሮች ሊገኙ ይችሉ ይሆናል ከሚል ነው፡፡ ሁኔታው ከታወቀ በሁዋላ እነዚህ ለእናቶች ሞት ምክንያት ይሆናሉ ተብለው የተለዩ ችግሮች በተመሳሳይ ወቅት እና በአፋጣኝ መፍትሔ ሊያገኙም ላያገኙም እንደሚችሉ የታወቀ ነው፡፡ ለምሳሌ የትምህርት ጉድለት፣ ድህነት ፣ጎጂ ልማድ ፣ሀይማኖታዊ እና የጾታ ተጽእኖ የመሳሰሉት ጊዜ የሚፈጁና  በአንድ አካል ብቻ መፍትሔ የማያገኙ ሲሆን ከዚህ በተለየ ደግሞ ቅጽበታዊ የሆኑና በቀላሉ ሊስተካከሉ የሚችሉ ...ለም ሳሌ...የግንዛቤ ጉድለት ፣የጤና ባለሙያ እጥረት፣ ወደሆስፒታል ለመድረስ እንደ ችግር የሚቆጠሩ ፣የመድሀኒት ችግር ፣የላቦራቶሪ ጉድለት ፣የደም እጥረት የመሳሰሉት ግን Kስተካከሉ የሚችሉ ናቸው፡፡ከዚህ አኩዋያ የምእተ አመቱን የልማት ግብ ለማሳካት በኢሶግ እና በአገር አቀፍ ጭምር የሚካሄደው የዳሰሳ ሂደት እገዛ እንደሚያደርግ ይታመናል፡፡

***

የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር (ESOG) ከአለም አቀፉ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር (FIGO  ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ፣አምሀራ ፣ደቡብ እና ኦሮሚያ መስተዳድሮች ከተለያዩ ዘጠኝ ሆስፒታሎች ጋር በመተባበር ለእናቶች ሞት ምክንያት የሚሆነው ምንድነው ?የሚለውን ለመለየት የዳሰሳ ስራ እየተሰራ መሆኑን ነበር በኢሶግ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ብሩክ ተ/ስላሴ ከላይ የገለጹት ፡፡ በአገር አቀፍ ደረጃ በመደረግ ላይ ያለውን ደሰሳ በሚመለከት ደግሞ በፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስር ዶ/ር ብርሀኑ ሰንደቅ በጤና ጥበቃ የእናቶችና የጨቅላ ሕጻናት ጤና እንክብካቤ አማካሪ እንደሚከተለው ገልጸዋል ፡፡

በኢትዮጵያ በየአምስትና አስር አመቱ የሚደረገው ጥናት የእናቶችን ሞት ቁጥርና በአብዛኛው ግልጽ የሆኑ ምክንያቶችን ይዞ ይወጣል፡፡ ከዚህ ባለፈ ግን እናቶች ለምን ይሞታሉ በሚል ምንያቶችን በመዘርዘር መፍትሔ ጠቋሚ ስላልነ በጤና ጥበቃ ሚኒስር በኩል በጤና ተቋማት ፣በግለሰቦች ፣ወይንስ በሙያተኞች አቅም ማነስ... ወዘተ የሚለውን በመፈተሸ ወደመፍትሔ ለመድረስ እንቅስቃሴ ተጀምሮአል፡፡ በእርግጥ በተወሰኑ አካባቢዎች በኢትጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህር የተጀመረ ዳሰሳ አለ፡፡ በጤና ጥበቃ ግን አዲስ ጅምር ነው፡፡

የዳሰሳው ጥናት የሚጀመረው በጤና ተቋማት ነው፡፡ በመንግስት ሆስፒታሎች ውስጥ የእናቶችን ሞት የሚያጠና ቡድን ተቋቁሞ የእናቶች ሞት ምክንያቱን በውል በመለየት መረጃ እንዲሰበሰብ ይደረጋል፡፡ ይህ ሲደረግ ግን ከባለሙያውም ይሁን ከቤተሰብ ወይንም ከተቋም ለጉዳዩ ምክንያቱ እከሌ ነው ከሚል ማንንም ከመወንጀል ወይንም ከማሳፈር ውጭ በሆነ መንገድ ይህች እናት የሞተችው ከምን የተነሳ ነው ...ከመጉዋጉዋዣ እጥረት...ከግንዛቤ እጥረት...ወይንስ ቀድሞውንም ከነበራት ሕመም የሚለውን በመለየት ይመዘገባል፡፡

የዳሰሳ ጥናት ማካሄዱ ምን ያህል መደጋገፍን እንደሚሻ የሚገልጹት ዶ/ር ብርሀኑ የእናቶችን ሞት ምክንያት ለማወቅ የሚደረገው የዳሰሳ ጥናት በእርግጥ በፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስር በእራሱ ብቻ የሚካሄድ አይደለም፡፡ የእናቶች ሞት የሚከሰትባቸው ምክንያቶች የተለያዩ እንደመሆናቸው የተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶችን በዳሰሳው ስራ የበኩላቸውን እንዲወጡ ማድረግ ይገባል፡፡ ለምሳሌ የግብርና ፣ መንገድና ትራንስፖርት እንዲሁም በጤና ጥበቃ ሚኒስርም በኩል እስከ ቀበሌ ድረስ በወረዳ ጤና ቢሮ በመሳሰሉት በተዋረድ የጤና ልማት ሰራዊት እና የጤና ኤክስንሽን ሰራተኞች ባሉበት ሁሉ ባካባቢያቸው ማንኛዋ እናት በምን ምክንያት እንደሞተች በቅርብ ክትትል በማድረግ የሚያውቁበት መንገድ ይዘረጋል፡፡

የዳሰሳ ጥናቱ ምን ለውጥ ሊያመጣ እንደሚችል ዶ/ር ብርሀኑ ሲገልጹ የእናቶችን ሞት ምክንያት ዳሰሳ በማድረግ ምላሽ መስጠትን የማከናወን ሂደት በተለይም ባደጉ አገሮች ከፍተኛ ለውጥ ያመጡበት መሆኑ በግልጽ ይታያል፡፡ የእናቶችን ሞት ምክንያት በመለየት እና አንኩዋር የሆኑትን በመምረጥ ለእያንዳንዱ ችግር መፍትሔ በመስጠት ከፍተኛ ለውጥ በማምጣት በኩል እንደእንግሊዝ ያሉት አገሮች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በእርግጥ ሙሉ በሙሉ ችግሩን ያስወግዳል ማለት ሳይሆን ግን ባብዛኛወ ከ90 በመቶ በላይ የሆኑትን የሞት ምክንያቶች ማስወገድ ይቻላል፡፡

እነደውጭው አቆጣጠር በ2000 ዓ/ም በኢትዮጵያ ከ 100000 አንድ መቶ ሺህ 871 ስምንት መቶ ሰባ አንድ ያህል እናቶች ይሞቱ የነበረ ሲሆን በ2005 በተደረገው ጥናት ደግሞ ከአንድ መቶ ሺህ እናቶች ወደ 673 ስድስት መቶ ሰባ ሶስት ያህሉ በአንድ አመት ጊዜ ይሞቱ እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በሚሊኒየሙ የልማት ግብ እቅድ መሰረት የእናቶች ሞት እንደውጭው አቆጣጠር ከ1990-2015 ድረስ ከነበረበት በ3/4ኛ እንዲቀንስ ይጠበቃል፡፡ በዚህም መሰረት በአሁኑ ወቅት በመካሄድ ላይ ያለው የእናቶች ሞት ምክንያት በዳሰሳው ከተለየና አንኩዋር የሆኑ ችግሮችን መቅረፍ ከተቻለ ከታቀደው ለመድረስ ምቹ መንገድ ይፈጥራል ...እንደባለሙያዎቹ እምነት፡፡

 

 

 

Read 2223 times Last modified on Saturday, 12 May 2012 11:04