Saturday, 01 October 2011 13:17

.. እንደሀገር... እጅና ጉዋንት ... ..

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

ሕጻናት ከኤችአይቪ ቫይረስ ነጻ ሆነው እንዲወለዱ ለማስቻል በስራራ ላይ ያለው የ PMTCT ፕሮጀክት የስራራ ውጤትን ለመለካት የሚቻለው ምን ያህል ሕጸናት ከቫይረሱ ነጻ ሆነው ተወለዱ የሚለው ሲታወቅ ነው፡፡ ይህንን በሚመለከት ያለው የቅብብሎሽ አሰራራር የተሟላ መረጃን አይሰጥም በሚል የጀመርነውን ርእስ ለመቋጨት ከኢፊድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስር ሁለት እንግዶች ማብራራሪያቸውን እንዲያካፍሉን ጋብዘናል፡፡

እንግዶቹ አቶ አበባው ደሶ በኢትዮጵያ ፌደራራላዊ ዲሞክራራሲያዊ ሪፐብሊክ ጤና ጥበቃ ሚኒስር የሜዲካል ሰርቪስ ረዳት ዳይሪክተር እና ዶ/ር ታደሰ ከተማ በኢፊድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስር የእናቶች ጤና አማካሪ ሲሆኑ በኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር የ PMTCT ፕሮጀክት የክትትልና ምዘና ባለሙያዎች አቶ አቢይ መርጊያና መቅደስ ይልማ የመፍትሔ ሀሳብ ያሉትን እናe’wv‹G<ªK”፡፡
ከኤችአይቪ ቫይረስ ነጻ የሆነ ተውልድን ለማፍራራት በተናጠል ከመስራራት ተቀናጅቶ መስራራት ያስፈልጋል ያሉት አቶ አበባው ደሶ በኢትዮጵያ ፌደራራላዊ ዲሞክራራሲያዊ ሪፐብሊክ ጤና ጥበቃ ሚኒስር የሜዲካል ሰርቪስ ረዳት ዳይሪክተር ናቸው፡፡ በመቀጠልም አቶ አበባው እንደገለጹት ..ታካሚዎች ለተሻለ የህክምና ክትትል ወይንም አካባቢን መሰረት ባደረገ መልኩ ከአንዱ የጤና ተቋም ወደሌላው የህክምና ተቋም መላክ በጤና ጥበቃ ሚኒስር ትኩረት የተደረገበትና የታወቀ አሰራራር ነው፡፡ እንደጤና ጥበቃ ሚኒስር የቅብብሎሽ ዘዴው ተግባራራዊ ሊሆን የሚችልበትን መመሪያ ማዘጋጀት ትልቁ ጅማሮ ሲሆን ይህም ተጠናቆ ለህክምና ተቋማቱ የማስተዋወቅ ስራራው ተካሂዶ በአሁኑ ሰአት ከስራራ ላይ ውሎአል፡፡
አንድ ጤና ተቋም ወደሌላ ተቋም የተላከ ታካማን ከምን ደረጃ ላይ እንዳለ በምላሹ ታካሚውን ለላከው የህክምና ተቋም ግብረ መልስ መላክ እንዳለበት ይታመናል፡፡ ይህም ከፌደራራል ደረጃ በክልል ጤና ቢሮዎችም አሰራራሩ ምን እንደሚመስልና እንዲሁም ግድፈትን በሚመለከት ተጠያቂነትን በሚያሳይ ደረጃ በዝርዝር የተገለጸበት ነው፡፡ ስለዚህ ይህ በአገር አቀፍ ደረጃ ተግባር ላይ የዋለ አሰራራር ነው፡፡ በእርግጥ ስራራው በትክክል እየተካሄደ አይደለም ለሚለው ችግሩ መኖሩን የሚያሳዩ አሰራራሮች አልፎ አልፎ መታየታቸው አልቀረም፡፡ ነገር ግን ምን ያህል የጎላ ነው የሚለውንም አብሮ መመልከት ተገቢ ነው ብለዋል አቶ አበባው ደሶ፡፡
አቶ አበባው በመቀጠልም ማንኛውም የጤና ባለሙያ በትምህርቱ ወቅት አንዱ የሚያገኘው እውቀት በምን መልክ ታካሚን እንደT>Áe}“ÓÉ“ ከአቅም በላይ ሲሆን በምን መልክ ወደሌላ የህክምና ተቋም እንደሚልከው ሲሆን ከሌላ የህክምና ተቋም ለተላከ ሕመምተኛም ግብረ መልሱን በተገቢው መንገድ መመዝገብ ይጠበቅበታል ፡፡ ነገር ግን ይህ አሰራራር አልፎ አልፎ ክፍተት ስለሚታይበት በኢትዮጵያ ፌደራራላዊ ዲሞክራራሲያዊ ሪፐብሊክ ጤና ጥበቃ ሚኒስር ሁኔታውን ለማረም መመሪያ ከመውጣቱ በተጨማሪ ስልጠና ለባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን ይህንን የሚከታተሉ ላይዘን ኦፊሰሮች በየጤና ተቋማቱ እንዲቀመጡ ተደርጎአል፡፡ በእርግጥ በግል የህክምና ተቋማት ደረጃ ስራራው እንደሚሰራራ እምነቱ ቢኖረንም በእኛም በኩል እገዛ የማድረጉ ሁኔታ ዘልቀን የገባንበት አይደለም፡፡
አንድ ታካሚ  ከኤችአይቪ ጋር በተያያዘም ብቻ ሳይሆን በማንኛውም የጤና ጉዳይ ወደሌላ የህክምና ተቋም ሲላክ ለምን እንደተላከ ፣ምን ሕክምና እንደተደረገለት ፣ወደፊትስ ምን እንደT>ÁeðMÓ መጠየቅና ማወቅ እንዲሁም ሂደቱን መከታተል እንደሚገባው አስቀድሞ ግንዛቤው ቢኖረው ጥሩ ነው፡፡ ታካሚው ይህንን ካወቀ በመካከል የሚጎድል ነገር እንኩዋን ቢኖር በማስታወስ በጤናው ዙሪያ ተገቢው አሰራራር እንዲኖር ያግዛል፡፡
ከኤችአይቪ ነጻ የሆነ ትውልድ ለማፍራራት ተቀናጅቶ መስራራት ተገቢ ነው ያሉት አቶ አበባው ለአንድ አይነት አላማ በመቆም ባጠቃላይ የሚመለከተው ሁሉ እንደሀገር እጅና ጉዋንት ሆነን መስራራት ይጠበቅብናል፡፡ በእርግጥ በተናጠል መሄዱ ከሚፈለገው ውጤት አያደርስም ብለዋል አቶ አበባው ደሶ በኢፊድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስር የሚዴካል ሰርቪስ ረዳት ዳይሬክተር፡፡ ..
ቀጣዩ ተናጋሪ ዶ/ር ታደሰ ከተማ በኢፊድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስር የእናቶች ጤና አማካሪ ናቸው፡፡ እንደ ዶ/ር ታደሰ ማብራራሪያ ..የህጻናቱ ከኤችአይቪ ነጻ ሆነው የመወለድና ከተወለዱም በሁዋላ ለቫይረሱ እንዳይጋለጡ ለማድረግ ከተወለደ ጀምሮ ከሚወስደው መድሀኒት በተጨማሪ በየወሩ ክትትል ሊደረግላቸው ይገባል፡፡ በመቀጠልም ከኤችአይቪ ቫይረስ ነጻ ናቸው አይደሉም የሚለውን በተለየ ምርመራራ ይረጋገጣል፡፡ በእርግጥ የሕጻናቱ አጠቃላይ ምርመራራ መጀመሪያ ሕክምናውን ባደረጉበት ቦታ የሚጠናቀቅ ሳይሆን ወደሌላ የህክምና ተቋም ወይንም ላቦራራቶሪ በመላክ ጭምር የሚሰራራ ነው፡፡ ስለዚህ የደም ናሙናው ወደሌላ የህክምና ተቋም ወይንም ላቦራራቶሪ ተልኮ ምርመራራው ሲካሄድ በተቀናጀ መልክ መልሱንም እየተቀባበሉ ውጤቱን ለባለሙያ የማቅረብ አሰራራር ተዘርግቶአል፡፡
የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር የክትትልና ምዘና ባለሙያዎች እንደጠቆሙት በቅብብሎሽ ስርአት ውስጥ የሚጎድለው ነገር ታካሚው ለተላከበት የህክምና ተቋም ምላሽ በትክክል አይላክም የሚል ሲሆን እንደ ኢፊድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስር የሚጠበቅብን የአሰራራር ሂደቶችን መዘርጋት ሲሆን ያ መስመር በምን መልክ ተግባር ላይ እንደዋለ መከታተልና ስህተት ካለ ወደትክክለኛው መስመር የሚገባበትን መንገድ ማሳየት ነው፡፡ ከዚህ አንጻር የተዘጋጀው የቅብብሎሽ ፎርም ከስሩ ምላሽ የመስጫ ቦታ ያለው ስለሆነ ማንኛውም ታካሚ የተላከበት የህክምና ተቋም ቅጹን በትክክል ሞልቶ መረጃው የተሟላ እንዲሆን ማስቻል ይጠበቅበታል ብለዋል ዶ/ር ታደሰ ከተማ ፡፡     
የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር የ PMTCT  ኤችአይቪ ከእናት ወደልጅ እንዳይተላለፍ የሚሰራራ ፕሮጀክት የክትትልና ምዘና ባለሙያዎች የሆኑት መቅደስ ይልማእና አቶ አቢይ መርጊያ በተለይም በግል የህክምና ተቋማት ከቫይረሱ ጋር ከሚኖሩ እናቶች የሚወለዱ ሕጻናት ከቫይረሱ ነጻ መሆን ያለመሆናቸውን የሚያሳየው መረጃ በትክክል እየተመዘገበ አይደለም ፡፡ ስለዚህም የህክምና ተቋማቱ ወደሌላ የህክምና ተቋም ሲልኩም ይሁን ከሌላ የህክምና ተቋም ሲቀበሉ ታካሚው የነበረውን ታሪክ የመመዝገብና የመላላክ ዘዴያቸው የተጠናከረ እንዲሆንም የመፍትሔ ሐሳቦችን ጠቁመዋል፡፡
ከኤችአይቪ ቫይረስ ነጻ የሆነ ትውልድ ለማፍራራት የሚያግዝ የመፍትሔ ሀሳብ ፡-
1.    ከመፍትሔዎች ሁሉ ቀዳሚ የሚሆነው ስለኤችአይቪ ቫይረስም ሆነ ሌላ የጤና ሁኔታቸው ሕጻናት የጤና አገልግሎት የሚያገኙት በአንድ ሆስፒታል ቢሆን የተሻለ መፍትሔ ነው፡፡ ይህ የማይቻል ሆኖ ወደሌላ የጤና ድርጅት ሲላኩ ደግሞ በትክክለኛው መንገድ ምላሽ መስጠት ተገቢ ነው፡፡
2.    ከቫይረሱ ጋር የምትኖር እናት በእርግዝናዋ ጊዜ ለክትትል ወደሐኪም ዘንድ ስትቀርብ ጥራራቱን የጠበቀና ተከታታይነት ያለው የምክርና የክብካቤ አገልግሎት ሊሰጣት ይገባል፡፡ አንዲት እናት ከእርግዝና ጊዜዋ ጀምሮ ይህንን አገልግሎት ብታገኝ ግንዛቤዋን በማሳደግ ስለልጅዋም ቀጣይ ሁኔታ ልትከታተል ትቸላለች፡፡
3.    ኤችአይቪ ቤተሰብን ያማከለ ችግር በመሆኑ የህብረተሰቡ ግንዛቤው እንዲያድግ በተለያየ መንገድ የጠነከረ ስራራ መሰራራት አለበት፡፡ በመገናኛ ብዙሀንና በጤና ተቋማቱ የጋራራ የጤና ትምህርት በመስጠት ወይንም የጤና ኤክስንሽን ሰራራተኞች በሚዘዋወሩባቸወ ቤቶች ሁሉ ግንዛቤውን ቢያስጨብጡ ህብረተሰቡ በቅድሚያ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ያስችለዋል፡፡
4.    ተከታታይነት ያለው የጤና ባለሙያዎች ትምህርት መስጠት አሁን የሚታየውን ችግር ለማቃለል ይረዳል፡፡ ብዙ ጊዜ የጤና ባለሙያዎቹ በተለያየ ምክንያት ከስራራ ስራራ የመዘዋወር ወይንም ስራራ የመልቀቅና የመቀጠር ሁኔታ ስለሚታይባቸው ስልጠናው በስፋት እና በተከታታይነት ቢሰጥ ግን የሰው ኃይል እጥረትን እና የስራራ ተጠናቅቆ ያለመሰራራትን ችግር ለማቃለል ያስችላል፡፡
5.    የጤና አገልግሎት ስርአቱ ረዘም ላለ ጊዜ ክትትልና ክብካቤ ለመስጠት እንዲያስችል  ከተዛመጅ አገልግሎቶተቸ ጋር ማቀናጀት ጠቀሜታ አለው ፡፡ ከቫይረሱ ጋር ከሚኖሩ እናቶች የተወለዱ ሕጻናት ከተወለዱበት ጊዜ ጀምሮ  ለአስራራ ስምንት ወራራት ያህል ተከታታይ የሆነ የህክምና አገልግሎት ካላገኙ በኤችአይቪ ይያዙ አይያዙ ማወቅ አይቻልም፡፡ ነገር ግን ለክትባትና ለሌላም ወቅታዊ ለሆነ ምርመራራ ወፈሕክምና ተቋሙ በሚመጡበት ጊዜ በዚያውም የኤችአይቪን መኖር ያለመኖር ለማወቅ የሚያስችለውን ክትትል መስራራት ሂደቶቹን የተቀላጠፈ ከማድረጉም ባሻገር ልጁ ያለበት የጤና ደረጃም በቀላሉ እንዲታወቅ ይረዳዋል፡፡ በእርግጥ በኢትዮጵያ ከአሰራራር አንጻር ፕሮግራራሙ በዚህ መንገድ ቢነደፍም ብዙ ጊዜ ተግባራራዊ አይደለም፡፡
6.    የጤና ባለሙያው በቀላሉ ለኤችአይቪ የተጋለጡ ሕጻናት ልጆችን የሚለይባቸውን መሳሪያዎች እንደ ካርድ የመሳሰሉትን ቢጠቀም ለክትትሉ ግልጽነት ይረዳል፡፡ ለምሳሌ.. አንዳንድ የጤና ተቋማት ውስጥ እንደታየው ሕጻናቱ ለሌላ ሕክምና ወደህክምና ተቋሙ ሲመጡ ለኤችአይቪ የተጋለጡ መሆኑ ተረስቶ  ክትትሉ ሳይደረግ ይቀራራል፡፡
7.    ብዙ ህጻናት መሰረታዊ የሆኑ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ለማስቻል የ PMTCT  አገልግሎትን በፍጥነትና በተሟላ መልኩ ማስፋፋት ይገባል፡፡በዚህU ኤችአይቪ  ከእናት ወደልጅ የመተላለፍ እድሉን ለማጥበብ ይረዳል፡፡
8.    የጤና አገልግሎት ስርአቱን ማሻሻል ሕጻናቱ ከኤችአይቪ ነጻ ሆነው እንዲወለዱ ከሚረዳው መንገድ አንዱ ነው፡፡ የጤና ባለሙያዎች ታካሚን ከየት ወደየት መላክ እንዳለባቸው የሚያሳየውን የአገልግሎት መዳረሻ በትክክል ወጥነት ባለው መልኩ መጠቀም ተገቢ ነው፡፡ ምክንያቱም አንድ ልጅ በቫይረሱ መያዝ አለመያዙን ለማወቅ በሚፈጀው የአስራራ ስምንት ወር ጊዜ ውስጥ ወደየትኛው የጤና ተቋም እንደተላከ ለማወቅ ሲፈለግ መረጃውን በቀላሉ ለማግኘት ስለሚያስችል ነው ፡፡

 

Read 2719 times Last modified on Saturday, 01 October 2011 13:21