Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 29 September 2012 10:12

7ኛው የአይሮቤ አሜሪካ ፊልም አውደርእይ ሰኞ ይከፈታል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ሰባተኛው የአይሮቤ አሜሪካ ፊልም አውደርእይ ሰኞ ምሽት ሰሜን ሆቴል አካባቢ በሚገኘው የጣሊያን የባህል ተቋም እንደሚከፈት አዘጋጆቹ አስታወቁ፡፡ አዲስ አበባ የሚገኙ የስፓኞልና ፖርቱጋልኛ ተናጋሪ ሀገራት ኤምባሲዎች በየዓመቱ የሚያዘጋጁት አውደርእይ እስከ ዛሬ ሳምንት ለፊልም ተመልካቾች ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡ በዚሁ መሠረት ሰኞ Un Mundo Maravilloso የተሰኘ የሜክሲኮ ኮሜዲ፣ ማክሰኞ    Besouro የተሰኘ የብራዚል ድራማ፣ ረቡዕ ምሽት Habanastation የተሰኘ የኩባ ድራማ፣ ሐሙስ Oriena የተሰኘ የቬንዙዬላ ድራማ፣ አርብ Aesperanca estaonde menos se espera የተሰኘ የፖርቱጋል ድራማ እና ቅዳሜ Celda 211 የተሰኘ የስፔን ልብ አንጠልጣይ ድራማ ፊልሞች በእንግሊዝኛ ሰብታይትል ለእይታ ይቀርባሉ፡፡

 

 

Read 4198 times Last modified on Saturday, 29 September 2012 10:15