Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 01 September 2012 10:52

“ባዶነትና ትልቅ ሃይል ተሰማኝ” አቶ በረከት ስምዖን

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ሕይወቱ ከማለፉ ከአምስት ቀናት በፊት በስልክ አግኝቼ ስለ ጤንነቱ ጠይቄው ነበር፡፡ አስከፊውን ዜና የሰማሁት ሕይወቱ ባለፈ ጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ነው፡፡ በአጋጣሚ አጠገቡ አልነበርኩም፡፡ ተደወለልን፡፡ ከእንቅልፋችን ተቀስቅሰን ተሽሎታል የሚለውን ወሬ ሰምተን ስለነበር ተዝናንተን መተኛት ጀምረን ነበር፡፡ እና የመጨረሻዎቹ ቀናት ላይ ነው ችግር ያጋጠመው፡፡ ሲቀሰቅሱኝ ባልተለመደ ሰዓት ነበር፡፡ 5፡40 ላይ ሕይወቱ አልፎ 6፡10 ላይ ተቀሰቀስኩ፡፡ በዚህ ሰዓት ላይ የሚቀሰቅሰኝ ሰው ስላልነበረ “አቶ መለስ አርፏል” ማለት ነው የሚል ነገር ተሰማኝ፡፡ ያኔ በአንድ በኩል ባዶነት ተሰማኝ፤ በአንድ በኩል ደግሞ ትልቅ ኃይል ተሰማኝ፡፡ የዚህን ሰውዬ ራዕይ እንደ ኢሕአዴግ በቡድን ማሳካት አለብን የሚል ብርታት ሰጠኝ፡፡ እኔ አቶ መለስን እስከመጨረሻዋ ሰዓት ድረስ እየሠራ ነው የማውቀው፤ እየታገለ እየደከመ ራዕዩን እውን ለማድረግ ሲሠራ ነው የማውቀው፡፡ ሳጣው ባዶነት ብቻ አይደለም የተሰማኝ፤ ከፊቴ ሆኖ ሁሌም ወደፊት የሚጎትተኝ እንድሠራ የሚገፋፋኝ አሁንም ከጎኔ እንዳለ ነው የተሰማኝ፡፡

 

 

 

 

Read 2118 times Last modified on Saturday, 01 September 2012 10:54