Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 23 June 2012 07:42

‘ኔትወርክ ፌይለር’…

Written by 
Rate this item
(0 votes)

እኔ የምለው…እንግዲህ ጨዋታም አይደል…ስለ ሙቀት መለዋወጥ ሳነሳ የሆነ ነገር ትዝ አለኝማ፡፡ እንትናዬዎች…ኽረ ይሄ ቅጥነት ማብዛት ነገራችሁን ተዉን! በእኛ በቀጫጭኖቹ ሀበሾች ሰውነት ሆን ተብሎ የመጣ ቅጥነት ተጨምሮ…(ብቻ…ላልታሰበ ትርጉም የሚያች ነገር አታናግሩና! ቂ…ቂ…ቂ…. ለነገሩ እኮ ዘንድሮ ልክ “ውበት እንደ ተመልካቹ ነው…”

እንዴት ሰነበታችሁሳ!

ሰኔ 30 ደረሰ አይደል! የምር ግን ምን ይመስለኛል መሰላችሁ…ዘንድሮ የሳምንት ቀጠሮ እንኳን ማስታወስ ያቃተን ሰዎች፣ ድርጅቶች ምናምን ከ‘ሰኔ ሠላሳ ቀጠሮ’ ብንማር አሪፍ ይመስለኛል፡፡ ልክ ነዋ…የአሥር ሰዓት ቀጠሮ ከተያዘ በኋላ  “ምን መሰለህ፣ ሥራ ይዤ ረሳሁት…”  ለምንል የአሥር ወር ቀጠሮ መስጠት ማክበር የሚቻልበት ዘመን እንደነበር ማወቁ አሪፍ ነው፡፡

ለምንም ይሁን ለምን የ“ሰኔ 30 ጠብቀኝ/ጠብቂኝ…” ቀጠሮ አይዛነፍም ነበር፡፡ “ወንዝ ወርደን ይዋጣልናል…” ለመባባል፣ ዓመቱን ሙሉ “አንቺ ላይማ ኪሶሎጂ ሳላጦፍ! ቆይ ብቻ ሰኔ ሠላሳ ጠብቂኝ…”  ምናምን ብሎ ተፎክሮ በተግባር የሚውልበት…ሰኔ ሠላሳ አሪፍ ነበር፡፡

ምን ይመስለኛል በቃ ትልቅ የ‘ኔትወርክ ፌይለር’ ያለ ይመስለኛል፡፡ ልክ ነዋ…ድምጻችን አልሰማ ሲልስ! ነገሬ የሚለን ‘የህዝብ አገልጋይ ምናምን እየጠፋ ሲሄድስ! የቦሶች ቋንቋ እየተለወጠ እንደ ሁለተኛ ክፍል ተማሪ “ዋ! ሱሪህን ዝቅ አድርጌ በሳማ እንዳልጠበጥብህ!” መባል ሲበዛብንስ!

እናላችሁ…ኔትወርክ ፌይለር እግር ተወርች አስሮናል፡፡ ምንም አያቅታቸው የተባሉ ጥንዶች በሆነ የቤርሙዳ ትሪያንግል አይነት እንቆቅልሽ በሆነ ነገር “ዓይንህ/ዓይንሽ ለአፈር…” ምናምን ሲባባሉ የምር የሆነ የ‘ኔትወርክ ፌይለር’ እንዳለ ይገባችኋል፡፡

እናላችሁ… እንግዲህ ጨዋታን ጨዋታ ያነሳው የለ… መተማመን፣ መከባበር፣ መተሳሰብ የመሳሰሉ መልካም እሴቶች  የጠፉት በ‘ኔትወርክ ፌይለር’ ይመስለኛል፡ ብቻ ምን አለፋችሁ…የሆነ የማናውቀው ‘ሉሲፈር’ ምናምን ነገር ተደጋግፈን እንዳንኖር፣ ተነጋግርን ሀሳብ እንዳንለዋወጥ፣ ተቃቅፈን ሙቀት እንዳንለዋወጥ… የኔትወርካችንን ‘ፓስወርድ’ የወሰደብን ነው የሚመስለው፡ በአጭር ጊዜ ድፍን አገር ነገረ ሥራው ሁሉ ግራ የሚያጋባ የሚሆነው…አለ አይደል…‘ፓስወርዳችን ተሰብሮ’ ኑግና ተልባው ድብልቅልቁ ወጥቶ መሆን አለበት፡፡

እኔ የምለው…እንግዲህ ጨዋታም አይደል…ስለ ሙቀት መለዋወጥ ሳነሳ የሆነ ነገር ትዝ አለኝማ፡፡ እንትናዬዎች…ኽረ ይሄ ቅጥነት ማብዛት ነገራችሁን ተዉን! በእኛ በቀጫጭኖቹ ሀበሾች ሰውነት ሆን ተብሎ የመጣ ቅጥነት ተጨምሮ…(ብቻ…ላልታሰበ ትርጉም የሚያች ነገር አታናግሩና! ቂ…ቂ…ቂ…. ለነገሩ እኮ ዘንድሮ ልክ “ውበት እንደ ተመልካቹ ነው…” ምናምን አንደሚባለው ትርጉምም እንደ ተርጓሚው ሆኗላችኋል፡፡ እንዲሁ ለጥቆማ ነው… ቴብልና ቼይር…አለ አይደል… ጠረጴዛና ወንበር መሆናቸው የሚወሰነው በዌብሰተርና ሉዶልፍ ምናምን መዝገበ ቃላቶች ሳይሆን በእያንዳንዱ ሰው ሆኗል፡፡ አሀ…አገሯ የእኛዋ ጦቢያችን ነቻ! )

እናላችሁ…የገጠመን የ‘ኔትወርክ ፌይለር’ በአይ.ቲ. ምናምን ዕውቀት የሚፈታ አይደለም፡ ሊቀጠል ነው ሲሉት ይብሱን የሚቆረጥ ነገር በበዛበት ጊዜ ኔትወርካችንን መልሶ በመልክ በመልኩ የሚጠግንልን ያስፈልገናል፡፡

ስሙኝማ… እንግዲህ ጨዋታም አይደል… ችግሩ ምን መሰላችሁ፣ ያው እንደለመደብን… ከዌስት ኢንዲስ ወይ ከኦኪናዋ ደሴት ‘ቃል በቃል የምንኮርጀው’ ነገር አልሆን ብሎን ይኸው ውሉ ጠፍቶናል፡፡ ኮራጆች ትከሻንን ሰፋ አድርገን “ከእነእንትና ነው እኮ ልቅም አድርጌ የኮረጅኩት…” እያልን በሚጨበጨብልን አገር… መፍትሄው በኩረጃ የማይመጣ የ‘ኔትወርክ ፌይለር’ ሲገጥመን…የግራ ይሁን የቀኙ ፍሬቻ መብራት ያለበት ግራ ይገባናል፡፡

እኔ የምለው…አንዳንዴ ጊዜ “ኸረ በጭራሽ እንዲህ አልነበርንም…” እኮ ማለትም አሪፍ ነው፡፡ መስታወትና አርማታ የማይተኳቸው መአት ሰብአዊና አገራዊ ስሜቶች ሲጠፉና የ‘ኔትወርክ ፌይለር’ በማህበራዊ ኑሯችን ‘ካብ ለካብ’ ሲያስተያየን …“ቢሆንም፣ ባይሆንም እኔ የድርሻዬን ወርወር ላድርግ…” አይነት ብሎ የሚረባረብ ህብረተሰብ ያስፈልገናል፡፡ ህጻናቱ ከወላጆች ጋር በተፈጠረው የ‘ኔትወርክ ፌይለር’ የራሳቸውን የ‘ያልተገደበ የጋራ ንብረት አጠቃቀም’ ቂ…ቂ…ቂ… ስርአት ነገር ሲፈጥሩ ከተቋጠረው ግንባር ጀርባ “እንዲህ ሲሆንማ ዝም ብዬ አላይም…” የሚል ዕልህ ያስፈልገናል፡፡

ሀሳብ አለን…“ኔትወርክሽ ፌይል አድርጎ፣ ሳላገኝሽ ብቀር…” ምናምን የሚል ክሊፕ ይሠራልንማ፡፡ ስሙኝማ…እንግዲህ ጨዋታም አይደል… የክሊፕ ነገር ካነሳን አይቀር፣ የ‘ጥቁር ሰው’ ክሊፕ መመቸት ብቻ አይደለም፣ “ለካንስ እንዲህ መስራት የሚችሉ ልጆች አሉ!” አስብሎኛል፡፡ በክሊፑ የተሳተፉት ሁሉ ይመቻቸውማ!

እናላችሁ….የ‘ኔትወርክ ፌይለር’ የእነኚህ ዓይን፣ አፍና ጆሯቸውን የደፈኑትን ጦጣዎች ነገር ነው የሚያስታውሷችሁ፡፡ ልክ ነዋ…የ‘ኔትወርክ ፌይለር’ በአብዛኛው የመጣው ሆነ ተብሎ ነዋ! ኔትወርኩ ሲጠብቅና ላላላተ የሚያስቸግር ሲሆን የማይመቸን መአት ነና! ‘ኔትወርክ’ ጥሩ በሆነበት ሁሉ ‘የአትክልት መከርከሚያ መቀስ ይዘን አደን የምንወጣ መአት ነና! የሆዳችንን የምናማከራቸውና የላይኛው ቤታችን ድልድይ የሆኑን የነፍስ አባቶች ምናምን ቁጥራቸው እየቀነሰብን ነዋ! (እዛ አካባቢስ ቢሆን…ዘንድሮ ቀላል ‘ኔትወርክ’ ቆረጣ ነው እንዴ ያለው!)

ታዲያማ…ሪሃና ትዘፍናለች፣ እኛ ‘ኔትወርካችን’ ይበጣጠሳል… ሜሲ ጎል ያገባል፣ እኛ ‘ኔትወርካችን’ ይበጣጠሳል… ቴሪ የጓደኛውን ገርልዬ “እነሆ በረከት” ይላል፣ እኛ ‘ኔትወርካችን’  ይበጣጠሳል…ፊፍቲ ሴንት ጣጥ ብሎ ሲያሽከረክር ይያዛል፣ እኛ ‘ኔትወርካችን’  ይበጣጠሳል…እና ቅድሚያ የምንሰጣቸው ነገሮች በደህናው ዘመን ቢሆን ኖሮ… “የራሷ አሮባት የሰው ታማስልላች…” አይነት ነገር የሚያስተርትብን ነበር፡፡ አሁን መፈክርና ተረቱ በአንድ ተሰፋና የምንተረትው እንኳን ጠፋንማ!

የመፈክር ምናምን ነገር ካነሳን አይቀር…በዚሀ በከተማችን ምሥራቅ ክፍል አንዲት ‘ሱቅ’፡ አለችላችሁ፡፡ እናማ… ‘ሱቋ’ የሆነች ግድግዳዋ በአስፈሪ ሁነታ ከመፈራረሱ የተነሳ መጀመሪያ ስትሠራ ስንት ግድግዳ እንደነበራት ለማወቅ ‘አርኪዮሎጂስቶች’ ምናምን ያስፈልጋሉ፡፡ የቤቷ ስፋትና የሱቋ ባለቤት የጎን ስፋት ጥቂት ቢበላለጡ ነው፡፡ እናላችሁ በሯ ላይ ምን ተብሎ ተለጥፏል መሰላችሁ… “ዱቤና ጦርነት አስከፊ ገጽታ ነው…” አሪፍ አይደል!

ለነገሩ ከዚች ሱቅ ዱቤ የሚጠይቅ ማንኛውም ሰው ‘ክብረ ነክ’ ምናምን የሚል አንቀጽ ተጠቅሶበት ሊከሰስ ይገባል፡፡

እናላችሁ….ነገርዬዋ ምን መሰለቻችሁ… ድፍን አገር ፈካሪ፣ ፈላስፋ ምናምን በሆነበት ዘመን ሚጢጢዋ ኪዮስክ ትከሻዋን የማትነሰንስሳ!

እናማ… በባዶ ሜዳ፣ ምንም በሌለበት “…አስከፊ ገጽታ ነው…” ምናምን የምንል እየበዛን ነው… (እንትናዬ… ክራይቴሪያዎችሽ ውስጥ ቁመትን ቀዳሚ የማድረግሽን ‘አስከፊ ገጽታ’ ልገልጽልሽ እገደዳለሁ፡፡)

ስሙኝማ…ከዓመታት በፊት አንድ “አቤቱታ ለክቡራን ኢትዮጵያውያን…” ምናምን ነገር የሚል ዜማ ነበር አይደል! ያኔ፣ በፅሁፍ ቢያቅት እንኳን በዘፈን ፊት ለፊት አቤቱታ ማቅረብ ይቻል ነበር፡፡ አሁን አቤቱታ አቅርቦ ለመደመጥም፣ ምላሽ ለማግኘትም ‘ኔትወርክ ፌይለር’ ነገሩን ሁሉ አበላሽቶት አቤቱታችንን ለጂንና ብራንዲ ለመንገር ተገደናል፡፡እናማ…በየቦታው ‘ኔትወርክ ፌይለር’ ምልክቶች በሽ በሽ ናቸው፡፡ አንዴ የግቢውን አጥር ካለፋችሁ በኋላ ጥበቃ ሊያደርግላችሁ የሚገባ መሥሪያ ቤት ግድግዳው ላይ በትልቁ… ‘ኪሳችሁን ጠብቁ’ ብሎ ማስታወቂያ ሲለጥፍ የ‘ኔትወርክ ፌይለር’ ችግር አለ ማለት ነው፡፡ ለነገሩ ኪስ የሚጠበቀው… አለ አይደል…ከኪስ አውላቂ ነው ወይስ በተዘዋዋሪ የሚተላለፍልን መልእክት አለ! ልክ ነዋ…“ጠበል ቅመሺ…” ብሎ የጠራ ጋባዥ “ቦርሳሽን ከአጠገብሽ አታርቂ…” ሲል የሆነ ቦታ ላይ ውሉ የተበጠሰ ነገር አለ ማለት ነው፡፡

ታዲያላችሁ…‘ኔትወርክ ፌይለር’ ነገራችን ወደዛ አካባቢ ሳይበረዝ፣ ሳይከለስ እንዳይሄድ የእዛም አካባቢ ነገር ወደ እኛ እንዳይመጣ ይኸው ወጥሮ ይዞናል፡፡ (እነ እንትና… መልእክቴን አስተላልፉልን ብለናችሁ ምነው ሳይደርስ ቀረሳ!… ነው የእኛም ቁም ነገር ሆነችና ‘ጃም’ አደረጋችኋት! ቂ…ቂ…ቂ

እናላችሁ…‘ኔትወርክ ፌይለር’ ትልቁ ችግራችን ሆኗል፡፡ አንድዬ… የተዘጉ ጆሮዎችን፣ የተለጎሙ ዓይኖችን፣ የተደፈኑ ጆሮዎችን በሙሉ ይክፈትልንማ!

ደህና ሰንብቱልኝማ!

 

 

 

 

Read 3255 times Last modified on Saturday, 23 June 2012 10:39