Print this page
Saturday, 09 June 2012 07:38

የአህጉራችን አስከፊው ትራጄዲ ድራማ

Written by  አልአዛር ኬ.
Rate this item
(0 votes)

ለአፍሪካ ሙስና ተጠያቂዎቹ መሪዎቿ ናቸው!

ምንም አይነት የፖለቲካ የኢኮኖሚም ሆነ የማህበራዊ ጉዳይ ቢነሳ የአፍሪካ መሪዎች ለስንፍናቸው ማመካኛ የሚሆን ነገር ምንጊዜም አጥተው አያውቁም፡፡

በቅርቡ ሀገራችን በተሳካ ሁኔታ ባዘጋጀችው ሃያ ሁለተኛው የአለም የኢኮኖሚ ፎረም ስብሰባ ላይ ተካፋዮቹ ካደረጓቸው የተለያዩ ውይይቶች በአንዱ፣ የአፍሪካ የሙስና ሁኔታ ተነስቶ በውይይቱ ተሳታፊ የነበሩ የአፍሪካ መሪዎች በአፍሪካ ለተንሰራፋው ከፍተኛ የሙስና ችግር የውጭ ኩባንያዎች ግንባር ቀደም ተጠያቂ እንደሆኑ ገልፀው ነበር፡፡ ድሮ ድሮ ለአፍሪካ የኋልዮሽ እድገትና የኢኮኖሚ ድቀት ለእነዚህ መሪዎች ዋነኛ ማመካኛቸው የአውሮፓ የቅኝ ግዛት ነበር፡፡ አብዛኞቹ የአፍሪካ መሪዎች ይህንን ማመካኛ ዛሬም ድረስ አልተውትም፡፡

ርዕዮተ አለምን በተመለከተ ደግሞ አሁን አሁን ቅኝ ግዛት በኒዮሊበራሊዝም የተተካ ይመስላል፡፡ ይህ ሁሉ ማመካኛ ግን የጠቅላላው ታሪክ አንድ ክፍል ብቻ ነው፡፡ እንዲህም ሆኖና የተቻለውን ያህል የቅስቀሳና ፕሮፖጋንዳ ድግስ ቢደገስለትም የታሪኩን ሌላኛውን ክፍል ሸፍኖ ወይም አድበስብሶ የማስቀረት አቅም የለውም፡፡ በሌላ አነጋገር ማመካኛዎቹ የቱንም ያህል ቢቀያየሩና የህዝብ ግንኙነት ከበሮ ቢደለቅላቸውም የራስን ስህተት በመደበቅ፣ “በእኔ የለሁበትም፤ ከደሙ ንፁህ ነኝ” አይነት እንደ ጲላጦስ እጅን ለመታጠብ አያስችሉም፡፡ በቅርቡ የአለም የኢኮኖሚ ፎረም ስብሰባ ላይ የተነሳውን የአፍሪካን የሙስና ሁኔታ እንመልከት፡፡ የእኛን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ጨምሮ በውይይቱ የተሳተፉት የአፍሪካ መሪዎች፤ ለችግሩ ምንጭነት በዋናነነት እጃቸውን በውጭ ኩባንያዎች ላይ ቀስረዋል፡፡ ወቀሳውም ሆነ ሰበቡ ምንም ስህተት የለበትም፡፡ ምክንያቱም ነገርየው እውነት ስለሆነ ነው፡፡ በርካታ የአሜሪካና የአውሮፓ ታላላቅ ኩባንያዎች፤ በአፍሪካ ውስጥ ባሉ አትራፊ የንግድ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ማናቸውንም ነገር ለማግኘት የተሳትፎ ቁልፍን ለያዘው አካል እጅ መንሻም በሉት ጉቦ ወይም ማትጊያ ገንዘብ እንደሚከፍሏቸው ወይም በውጭ ሀገራት በከፈቱት የባንክ ደብተሮቻቸው እንደሚያስቀምጡላቸው የታወቀ ጉዳይ ነው፡፡  የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ስትራቴጂክ ምርቶች የሚሏቸውን እንደ ነዳጅ ዘይት፣ ወርቅ፣ አልማዝና ሌሎች የከበሩ ማዕድናትን በሚያመርቱ የአፍሪካ ሀገራት የዚህ አይነቱ የሙስና ጉዳይ አይነቱም ሆነ ደረጃው እጅግ ከፍ ያለ ነው፡፡ ነዳጅ አምራች በሆኑ ሀገራት ነዳጅን በማልማት ስራ ላይ የተሠማሩ ግዙፍ የምዕራብ የነዳጅ ኩባንያዎች፤  የነዳጅ ማልማቱ ስራ በየአካባቢው ባሉ ህዝቦችና ስነምህዳራቸው ላይ የሚፈጥረውን ከፍተኛ የጐንዮሽ ጉዳት ለመከላከል የሚሞክሩና የተቃውሞ ድምፃቸውን የሚያሰሙ የህብረተሰብ መሪዎችንና የመብት ተሟጋች ድርጅት ተወካዮችን በግልጽም ሆነ በስውር ከማሳፈን እስከ ማስገደል የሚደርስ ከፍተኛ ተጽእኖ በመሪዎቹ ላይ እስከመፍጠር የሚያስችል ሀይልና ጉልበት ገንብተዋል፡፡ ሟቹ የቀድሞው የናይጀሪያ አምባገነን መሪ ጀነራል ሳኒ አባቻ፤ በናይጀሪያ ነዳጅ አምራች ክልሎች ውስጥ በአንዱ ነዋሪ የሆኑት የኦጐኒ ጐሳ መሪና የመብታቸው ተሟጋች የነበሩትን ባለቅኔውንና ፀሐፌ ተውኔቱን ኬንሳሮዊዋን በግፍ በስቅላት የቀጡበትን መዝገብ መመርመር ለቻለ ልባም፣ የታላቁን የሼል የነዳጅ ኩባንያ ደም የነኩ እጆች አሻራ የሚያገኘው በቀላሉ ነው፡፡የአሜሪካና የአውሮፓ የተለያዩ ባንኮች የደንበኞቻቸውን የአካውንት ዝውውር ሰነድ በግልጽ የሚያሳዩ ቢሆኑ ኖሮ፣ ከናይጀሪያ ወደ ምዕራብ አፍሪካ ተሻግራችሁ የኢኳቶሪያል ጊኒ የእድሜ ልክ ፕሬዚዳንት የሆኑትን የቴወዶሮ ንጉየማምሻሶጐ እና የልጃቸው የቴወዶሪን በባንኮቹ የታጨቀው በብዙ መቶ ሚሊዮን ዶላር የሚቆጠረው ከፍተኛ ገንዘብ፣ ቀላል የማይባለውን መጠን የትኛው የአሜሪካና የአውሮፓ የቢዝነስ ኩባንያ በየትኛው ቀን በሰዎቹ ስም እንዳስገባ በቀላሉ ማወቅ ይቻል ነበር፡፡ ልክ በዚህ አይነት ከሰሜን አፍሪካ ከሊቢያ ጀምረን፣ በምዕራብ በጋቦን አድርገን፣ በምስራቅ በደቡብ ሱዳን አቆራርጠን፣ ወደ ደቡብ አፍሪካ በመዝለቅ፣ ወደ አንጐላ ስንገባ የመጠን ልዩነት ካልሆነ በቀር የምናገኘው ታሪክ ከላይ ከጠቀስነው ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ይህ ግን የታሪኩ ግማሽ ክፍል ብቻ ነው፡፡ ከዚህ በላይ የተዘረዘሩት እውነታዎች የሚያሳዩን የአፍሪካን ከፍተኛ የሙስና ድራማ የመጀመሪያ ክፍል ብቻ ነው፡፡ ድራማው ደግሞ የሚሊዮኖችን የአፍሪካ ህዝቦች ልብና ቅስም የሰበረ ትራጀዲ ድራማ ነው፡፡ የዚህን ትራጀዲ ድራማ ቀጣይ ክፍል ደግሞ ማንም የአፍሪካ ፕሬዚዳንትም ሆነ ሌላ ባለስልጣን አድበስብሶ ሊያልፈው ወይም ሃጢያቱን በሌሎች ላይ በመጫንና የራስን አቧራ በጭብጨባ አራግፎ ዞር የሚባልበት ተራና ቀላል ጉዳይ አይደለም፡፡ በሃያ ሁለተኛው የአለም የኢኮኖሚ ፎረም ስብሰባ ከተካፈሉትና ሙስናን በተመለከተው ስብሰባ ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ጋር የውጭ ኩባንያዎችን ዋና ተጠያቂ አድርገው ከፈረጁት መሪዎች አንዱ የናይጀሪያው ፕሬዚዳንት ጉድላክ ጆናታን ናቸው፡፡ በአፍሪካ ስለተንሰራፋው ከፍተኛ ሙስናም ሆነ ባጠቃላይ ሙስናን በተመለከተ የችግሩን መጠንና ስፋትም ሆነ በሀገርና በዜጐች ላይ ስለሚያደርሰው ጉዳት ምስክርነት ለመስጠት የሚችል ሰው ቢፈለግ ከፕሬዚዳንት ጉድላክ ጆናታን የሚበልጥ ሁነኛ ሰው ፈልጐ ማግኘት በእርግጥም ከባድ ፈተና ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም በፕሬዚዳንትነት የሚመሯት ሀገራቸው ናይጀሪያ ሙስናንና የሀገር ሀብትን በመዝረፍ በኩል ደረጃዋ ወይም ምድቧ ከባለ ከባድ ሚዛኖቹ የሻምፒዮን ሊግ ውስጥ ነው፡፡ ናይጀሪያ ከአመታዊ ብሔራዊ ገቢዋ ምን ያህሉን ከላይ እስከታች በየደረጃው ያሉ መሪዎቿ እንደሚዘርፉትና ይሄው ከፍተኛ የሀገር ሀብት ዝርፊያ ሀብታሟንና ለሌሎች የመትረፍ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ አቅም የነበራትን ሀገርና ህዝቦቿን ለእንዴት ያለ ከፍተኛ የህይወት ፈተና እንደዳረጋቸው በእርግጥም ከፕሬዚዳንት ጉድላክ ጆናታን በበለጠ በእማኝነት ቀርቦ የዚህን አስከፊ ትራጀዲ ድራማ የመጀመሪያ ክፍል ማስረዳት ወይም መተረክ የሚችል ሰው አይገኝም፡፡እንደሌላው የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ኑሮ ጉዳዮች ሁሉ የሙስናንም ጉዳይ በተመለከተ የአፍሪካ መሪዎች የማይነግሩን ወይም እዚህ ግባ የማይባል ምክንያት እየደረደሩ አደባብሰው ለማለፍ የሚሞክሩት የጠቅላላው ታሪክ ሁለተኛው ክፍል ለሁኔታው መፈጠር የሚጫወቱትን ግንባር ቀደም አሉታዊ ሚናና የየራሳቸውን ስህተቶች ነው፡፡ በሌላ አነጋገር የአፍሪካ መሪዎች በሌሎች ላይ ጣታቸውን በመቀሰር ወይም በሌሎች ላይ በማላከክ ሽወዳውን ሊያልፉ የሚሞክሩት ስውርና ግልጽ የሙስና ሁኔታ፣ በየሀገሮቻቸው የፖለቲካና የኢኮኖሚ ስርአት ውስጥ ተዘርቶ እስኪበቅልና ግንድ እስኪያወጣ ድረስ የሚጫወቱት ግንባር ቀደም ሚናና የየግል ሌብነታቸውን ታሪክ ነው፡፡ ማንም እንደሚያውቀው ናይጀሪያ በታሪኳ ከተፈራረቀባት አምባገነን መሪዎቿ ውስጥ በሀገር ሀብት ዝርፊያ ላይ ያልተሠማራና እጁ ያልተልከሰከሰ አንድ መሪ ለሞት መድሀኒት እንኳ ፈለጐ ማግኘት አይቻልም፡፡ የአሁኑ ፕሬዚዳንት ጉድላክ ጆናታንም ቢሆኑ ወደ ፕሬዚዳንትነት ስልጣን ምን ያህል ሀብት ይዘው መጥተው አሁን የባንክ አካውንት ደብተራቸው ምን ያህል መቶ ሚሊዮን ዶላር እንደያዘ፤ የፕሬዚዳንትነት ስልጣናቸው ሲጠናቀቅም ምን ያህል ይዘው እንደሚወጡ አይታወቅም፡፡ ይህ እንግዲህ የአፍሪካን መሪዎች በከፍተኛ ሁኔታ የሚያስሞስኑት የውጭ ኩባንያዎች በባንክ አካውንታቸው ከሚያስገቡላቸው ሌላ በራሳቸው የግል ተነሳሽነት ከብሔራዊው ካዝና በሰበብ አስባቡ የሚቦጭቁት ተደምሮ ነው፡፡ ጉዳዩን ዘርዘር አድርገን እንየው፡፡ በአንድ ወቅት የናይጀሪያ ፕሬዚዳንት የነበሩት ሸሁ ሻጋሪ፤ ፕሬዚዳንት ከመሆናቸው በፊት ናይጀሪያ በሚሊየነርነት ጨርሶ አታውቃቸውም ነበር፡፡ ከፕሬዚዳንትነት ስልጣናቸው ከተነሱ በኋላ ግን ዘመድ ጥየቃ ብለው ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀሱባቸው በስማቸው የተመዘገቡ ሁለት ጀት አውሮፕላኖች ነበሯቸው፡፡ የኒዠር ዴልታ ግዛት አገረ ገዥ የነበረውና አሁን እንግሊዝ ለንደን ውስጥ በሙስናና በሀገር ሀብት ዝርፊያ ተከሶ በእስር ላይ የሚገኘው ግለሰብ፤ በሶስት አመታት የአገረ ገዥነት ዘመን ብቻ የሁለት መቶ ሃምሳ ሚሊዮን ዶላር ባለቤት መሆን ችሎ ነበር፡፡ ቪያግራ የተባለ ወሲብ ቀስቃሽ ክኒን ውጠው ከስሪላንካና ከህንድ አገራት በግል ጀታቸው ካስመጧቸው ሴተኛ አዳሪዎች ጋር አለመጠን ሲዳሩ ልባቸው ቆሞ እንደሞቱ የሚታሙት አምባገነኑ ፕሬዚዳንት ጀነራል ሳኒ አባቻ፤ በስልጣን ላይ በቆዩበት የአራት አመት ከስምንት ወር ጊዜ ውስጥ ወደ አምስት ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ሀብት ከናይጀሪያ ብሔራዊ ካዝና ዘርፈው ወደ ውጭ አሽሽተዋል፡፡ ከዚህ ከፍተኛ ገንዘብ ውስጥ አብዛኛውን የዘረፉት በራስ ተነሳሽነትና ናይጀሪያን የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ቋሚ አባል እንድትሆን ለማድረግ ነው የሚል ኮሚክ ምክንያት በማቅረብ ነበር፡፡ በአንጐላ በየአመቱ ከአስር እስከ አስራ አምስት ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ሃብት ከብሔራዊ ገቢው የገባበት ይጠፋል እያሉ ራሳቸው አንጐላውያን በይፋ ይናገራሉ፡፡ ለረጅም አመታት በብቸኝነት እየገዟት ያሉት ፕሬዚዳንት ዶስ ሳንቶስ ዝም ብለው ፕሬዚዳንት ሳይሆኑ በአለማችን ካሉት ሚሊየነር (አንዳንዶች ቢሊየነር ናቸው ይሏቸዋል) ፕሬዚዳንቶች ግንባር ቀደሙ እንደሆኑ በሰፊው ይነገርላቸዋል፡፡ የአባታቸውን ስልጣን ወርሰው ጋቦንን በፕሬዚዳንትነት የሚገዙት አሊ ቦንጐ ከአባታቸው ስንት መቶ ሚሊዮን ዶላር እንደወረሱ፤ እሳቸውም በግላቸው ስንት እንዳላቸው ለጊዜው አይታወቅ ይሆናል፡፡ ሚሊየነር ፕሬዚዳንት እንደሆኑ ግን ለአፍታም አያጠራጥርም፡፡ በኢኳቶሪያል ጊኒ እንኳን የውጭ ሀገር ዜጋ የሆነ ቀርቶ የራሷ ዜጐች በትክክል መናገር የማይችሉት አንድ ጉዳይ አለ፡፡ ማንም የኢኳቶሪያል ጊኒ ዜጋ፤ የመንግስቱንና የፕሬዚዳንቱን የግል የቢዝነስ ድርጅቶች ለይቶ መናገር አይችልም፡፡ እጅግ ዝቅ ካለው የጨውና የስኳር የጉልት አይነት የችርቻሮ ንግድ እስከ ከፍተኛው የነዳጅ ዘይትና የጣውላ ንግድ ድረስ አሉ የተባሉት የንግድ ድርጅቶች ከዳር እስከ ዳር የተያዙት በፕሬዚዳንቱና በቤተሰቦቻቸው አባላት ነው፡፡ በተለይ በነዳጅ ዘይት ቢዝነስ ውስጥ ያላቸው ድርሻና ተሳትፎ በርካታና ትልቅ በመሆኑ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒያውያን በነዳጅ ዘይት ሀብት የታደሉት ፕሬዚዳንቱና ቤተሰቦቻቸው እንጂ ሀገራችን አይደለችም እያሉ የደህንነት ጥበቃ አባሎች በሌሉበት ጊዜና ቦታ በግልጽ፣ ያለበለዚያ ግን በሹክሹክታ ይናገሩታል፡፡ የቀድሞው የሊቢያ ፈላጭ ቆራጭ መሪ ኮሎኔል ሙአመር ጋዳፊ በሰይፍ እንደመጡ በሰይፍ ሄደዋል፡፡ በስልጣን ላይ በቆዩበት አርባ አንድ አመታት ሲያደርጉት የነበረውን አስገራሚ ድርጊትና የሊቢያን ከፍተኛ የነዳጅ ዘይት ሽያጭ ገቢ እንዴት ይጠቀሙበት እንደነበር በማስታወስ፣ የሊቢያ የነዳጅ ዘይት ሽያጭ ገቢ የሊቢያ ህዝብና መንግስት ነው ወይስ የሙአር ጋዳፊ ተብሎ የተጠየቀ አንድ ሰው፤ ትክክለኛውን መልስ የጋዳፊ ነው ብሎ ለመመለስ ለአፍታም እንኳ የማሰቢያ ጊዜ ያስፈልገዋል ብሎ የሚከራከር መኖሩ ያጠራጥራል፡፡ አፍሪካ በከፍተኛ የነዳጅ ዘይት ሀብት የታደሉ ከፍተኛ የነዳጅ አምራች ሀገራት አሏት፡፡ ከእነዚህ ሀገሮች መሀል የጥቂቶቹን ስም ዝርዝር ተናገሩ ብንባልና ናይጀሪያ፣ አንጐላ ፕሬዚዳንት ቴወዶሮ ንጉዌማ ሞባሶጐ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ፕሬዚዳንት ኣማር ቦንጐ፣ ጋና፣ ፕሬዚዳንት ሙአመር ጋዳፊ፣ ሱዳን፣ አልጀሪያ ወዘተ…ብለን ዝርዝሩን ብናቀርብ አንድ ማስተካከያ ይቀርብብናል እንጂ ሌላ ስህተት ጨርሶ አይገኝብንም፡፡ ማስተካከያው ኦማር ቦንጐና ሙአመር ጋዳፊ ሟች የቀድሞ ፕሬዚዳንቶች በሚል ይቅረብ የሚል ብቻ ነው፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ ምናልባት በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ የነዳጅ ዘይት ሀብት እንዳላት ሊበሰርላት ይችል ይሆናል የሚል ተስፋ እንጂ ገና ነዳጅማምረት አልጀመረችም፡፡ ይህን እኛም መላው አለምም እናውቀዋለን፡፡ ስለዚህ እንደ ሼል ያሉ አለምአቀፍ ግዙፍ የነዳጅ አምራች ኩባንያዎች በናይጀሪያና በኢኳቶሪያ ጊኒ የሚያደርጉትን አይነት እጅ ጥምዘዛና ሌሎች ተጽእኖዎች ቢያንስ ነዳጅ አግኝተን ማምረት እስከምንጀምር ድረስ እዚህ አይኖርብንም፡፡ ለውጭም ሆነ ለሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ከተዘጋጀው በሚሊወን የሚቆጠር ሄክታር የእርሻ መሬት ለውጭ ሀገር አልሚዎች የተላለፈው በጣም ዝቅተኛው መጠን ስለሆነና ቀሪው የአልሚ ያለህ እየተባለ እየተጮኸለት በመሆኑ፣ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ሊከሰት የሚችለው የውጭ ሀገር ኩባንያዎች የአስሞሳኝነት ሚና ከቁጥር የሚገባ ነው ብዬ በግሌ አልገምትም፡፡ ከእኔ የተሻለ ለጉዳዩ ቅርበትና መረጃው ያላችሁ ምስክራችሁን ስጡበት፡፡ልክ እንደ ናይጀሪያው ፕሬዚዳንት ጉድላክ ጆናታን ሁሉ የእኛው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊም የውጭ ሀገር ኩባንያዎችን ለአፍሪካ የሙስና ችግር በዋና ምንጭነት ተጠያቂ አድርገዋቸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ይህንን ሲናገሩ፣ ጉዳዩ እርስዎ እንደሚሉት ከሆነ በሀገራችን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ውስጥ ለመሳተፍ ወደ ግል ይዞታ ከተዛወሩት የተለያዩ የመንግስት የኢኮኖሚ ተቋማት ውስጥ ዋና ዋና የሚባሉትን የገዙት የውጭ ሀገር ኩባንያዎች ምን ያህል ሚሊዮን ወይም መቶ ሺዎች ዶላር ለመንግስት ባለስልጣናት በምስጋና መልክ አቀረቡላቸው ተብለው ቢጠየቁ ኖሮ፣ ያለ አንዳች ማመንታት የሚሰጡት መልስ “ይህ በእኛ ሀገር ያልተደረገ አንዳች አይነት ለፍርድ ቤት መቅረብ የሚችል ማስረጃ ያልተገኘበት መሠረተ ቢስ ወሬ ወይም ውንጀላ ነው” የሚል እንደሚሆን ቢያንስ ዘጠና አምስት በመቶ እርግጠኛ ሆኖ መናገር ይቻላል፡፡ ስለዚህ በሀገራችን ውስጥ ከሙጃ ሳርነት ወደ ግራር ዛፍነት ቀስ በቀስ እየተቀየረና ስርና ቅርንጫፉን እያንሰራፋ የመጣው ሙስና፤ የሀገር ውስጥ ስሪት ነው ብለን በሙሉ ልብ መናገር እንችላለን፡፡ ቀደም ብለን በተደጋጋሚ እንደጠቀስነው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ያነሱት የታሪኩን የመጀመሪያ ክፍል ብቻ ነው፡፡ የታሪኩ ክፍል ሁለት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ የሚመሩት ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግም ሆነ ካቢኔአቸው፤ ከፖለቲካው መድረክ በፍጥነት ሊያስወግዳቸው የሚፈልጋቸውን “እድለ ቢሶች” ካልሆነ በቀር የተንሰራፋውን ከፍተኛ ችግር የምር ማስወገድ ባይችል እንኳ ለመቀነስ የሚያስችል የፖለቲካም ሆነ የተግባር ቁርጠኝነት አንዴም እንኳን አሳይቶን አለማወቁ ነው፡፡ የታሪኩ ቀጣይ ክፍል የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ኢህአዴግም ሆነ መንግስታቸው ለበርካታ አመታት በታላቅ ትጋት እያከናወነ ያሳየን በሙሰኝነታቸውና በህገወጥ ስራቸው የተነሳ ህዝብ ያዘነባቸውና የተከፋባቸውን የፓርቲና የመንግስት ሹመኞቹን በህገወጥና በመጥፎ ስራቸው በህግ እንዲጠየቁ ሲያደርግ ሳይሆን በተቃራኒው ከተከፋው ህዝብ አይን ለጊዜው ዞር እንዲሉ ብቻ ወደ ሌላ አካባቢና የመንግስት መስሪያ ቤት አንዳንዴ ይግረማችሁ በሚል እልህ አይነት ተጨማሪ ስልጣን በመስጠት ሲያዛውራቸው ነው፡፡ በታሪኩ የመጀመሪያ ክፍል በከፍተኛ ስሜት በሌሎች ላይ ጣታቸውን የቀሰሩት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ፤ በቀጣዩ ክፍል ያልነገሩን ወይም የተለያዩ ውሃ የማያነሱ ምክንያቶችን በመደርደር አድበስብሰው ለማለፍ የሞከሩት፣ ለመዝረፍና ለማስዘረፍ ከማንኛውም ዜጋ የበለጠ እድልና ስልጣን ያላቸው ዋና ዋና ሌቦች ወይም ሙሰኞች የመንግስት ሌቦችና ሙሰኞች የመሆናቸውን ታሪክ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ያልነገሩን የግሎቹ ሌቦች የተፈጠሩትና ዝምባቸው እሽ እንዳይባል ስልችት እስኪለን ድረስ መረጃ እንጂ ፍርድ ቤት ማቅረብ የሚያስችል ማስረጃ ልናቀርብባቸው አልቻልንም እየተባለላቸው እንደፈለጉ እየሆኑ ያሉት መለኮታዊ ስልጣን ከላይ ቤት ተሰጥቷቸው ሳይሆን የበላይ አካል ከለላና ጥበቃ ስላላቸው የመሆኑን ታሪክ ነው፡፡ እንግዲህ ከዚህ በላይ የተዘረዘሩት ጉዳዮች ግልጽ የሚያደርጉልን አንድ ዋና ቁም ነገርን ነው፡፡ የአፍሪካ መሪዎች ዛሬም ቢሆን የመረጡት ለችግሮቻቸው መፈጠርና መንሠራፋት የራሳቸውን ሚና መደበቅና ሌሎቹን መውቀስና ማውገዝን ነው፡፡ ይህ ደግሞ ትርፉ ከንቱ ድካም ብቻ ነው፡፡ ለምን ቢባል መሪዎቹ የቻሉትን ያህል ቢያድበሰብሱትና በሌላ ላይ ቢያላክኩት የታሪኩን ቀጣይ ክፍል ህዝቡ ብጥርጥር አድርጐ ስለሚያውቀው ነው፡፡ እንዲህ ያለ ነገር ሲያጋጥማቸው የማሊ ዜጐች “አንዱ በር ሲዘጋ ሌላኛው ይከፈታል” በማለት ይተርታሉ፡፡ እውነታቸውን ነው፡፡ የአፍሪካ መሪዎች የገመናቸውን አንዱን በር ተረባርበው ሲዘጉት፣ ህዝቡ ደግሞ ሌላኛውን የገመና በር በቀላሉ ይከፍተዋል፡፡ መጨረሻ ላይ ለህዝቡና ለመሪዎች የሚቀረው መተዛዘብ ብቻ ነው፡፡ ልክ ፕሬዚዳንት ጉድላክ ጆናታንና ጠቅላይ ሚኒስትር መለስን በአለም የኢኮኖሚ ፎረም ስለሙስና በተደረገው ስብሰባ ላይ እንደታዘብናቸው፡፡     ለአፍሪካ ሙስና ተጠያቂዎቹ መሪዎቿ ናቸው! ምንም አይነት የፖለቲካ የኢኮኖሚም ሆነ የማህበራዊ ጉዳይ ቢነሳ የአፍሪካ መሪዎች ለስንፍናቸው ማመካኛ የሚሆን ነገር ምንጊዜም አጥተው አያውቁም፡፡ በቅርቡ ሀገራችን በተሳካ ሁኔታ ባዘጋጀችው ሃያ ሁለተኛው የአለም የኢኮኖሚ ፎረም ስብሰባ ላይ ተካፋዮቹ ካደረጓቸው የተለያዩ ውይይቶች በአንዱ፣ የአፍሪካ የሙስና ሁኔታ ተነስቶ በውይይቱ ተሳታፊ የነበሩ የአፍሪካ መሪዎች በአፍሪካ ለተንሰራፋው ከፍተኛ የሙስና ችግር የውጭ ኩባንያዎች ግንባር ቀደም ተጠያቂ እንደሆኑ ገልፀው ነበር፡፡ ድሮ ድሮ ለአፍሪካ የኋልዮሽ እድገትና የኢኮኖሚ ድቀት ለእነዚህ መሪዎች ዋነኛ ማመካኛቸው የአውሮፓ የቅኝ ግዛት ነበር፡፡ አብዛኞቹ የአፍሪካ መሪዎች ይህንን ማመካኛ ዛሬም ድረስ አልተውትም፡፡

 

 

ርዕዮተ አለምን በተመለከተ ደግሞ አሁን አሁን ቅኝ ግዛት በኒዮሊበራሊዝም የተተካ ይመስላል፡፡ ይህ ሁሉ ማመካኛ ግን የጠቅላላው ታሪክ አንድ ክፍል ብቻ ነው፡፡ እንዲህም ሆኖና የተቻለውን ያህል የቅስቀሳና ፕሮፖጋንዳ ድግስ ቢደገስለትም የታሪኩን ሌላኛውን ክፍል ሸፍኖ ወይም አድበስብሶ የማስቀረት አቅም የለውም፡፡  በሌላ አነጋገር ማመካኛዎቹ የቱንም ያህል ቢቀያየሩና የህዝብ ግንኙነት ከበሮ ቢደለቅላቸውም የራስን ስህተት በመደበቅ፣ “በእኔ የለሁበትም፤ ከደሙ ንፁህ ነኝ” አይነት እንደ ጲላጦስ እጅን ለመታጠብ አያስችሉም፡፡ በቅርቡ የአለም የኢኮኖሚ ፎረም ስብሰባ ላይ የተነሳውን የአፍሪካን የሙስና ሁኔታ እንመልከት፡፡ የእኛን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ጨምሮ በውይይቱ የተሳተፉት የአፍሪካ መሪዎች፤ ለችግሩ ምንጭነት በዋናነነት እጃቸውን በውጭ ኩባንያዎች ላይ ቀስረዋል፡፡ ወቀሳውም ሆነ ሰበቡ ምንም ስህተት የለበትም፡፡ ምክንያቱም ነገርየው እውነት ስለሆነ ነው፡፡ በርካታ የአሜሪካና የአውሮፓ ታላላቅ ኩባንያዎች፤ በአፍሪካ ውስጥ ባሉ አትራፊ የንግድ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ማናቸውንም ነገር ለማግኘት የተሳትፎ ቁልፍን ለያዘው አካል እጅ መንሻም በሉት ጉቦ ወይም ማትጊያ ገንዘብ እንደሚከፍሏቸው ወይም በውጭ ሀገራት በከፈቱት የባንክ ደብተሮቻቸው እንደሚያስቀምጡላቸው የታወቀ ጉዳይ ነው፡፡  የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ስትራቴጂክ ምርቶች የሚሏቸውን እንደ ነዳጅ ዘይት፣ ወርቅ፣ አልማዝና ሌሎች የከበሩ ማዕድናትን በሚያመርቱ የአፍሪካ ሀገራት የዚህ አይነቱ የሙስና ጉዳይ አይነቱም ሆነ ደረጃው እጅግ ከፍ ያለ ነው፡፡ ነዳጅ አምራች በሆኑ ሀገራት ነዳጅን በማልማት ስራ ላይ የተሠማሩ ግዙፍ የምዕራብ የነዳጅ ኩባንያዎች፤  የነዳጅ ማልማቱ ስራ በየአካባቢው ባሉ ህዝቦችና ስነምህዳራቸው ላይ የሚፈጥረውን ከፍተኛ የጐንዮሽ ጉዳት ለመከላከል የሚሞክሩና የተቃውሞ ድምፃቸውን የሚያሰሙ የህብረተሰብ መሪዎችንና የመብት ተሟጋች ድርጅት ተወካዮችን በግልጽም ሆነ በስውር ከማሳፈን እስከ ማስገደል የሚደርስ ከፍተኛ ተጽእኖ በመሪዎቹ ላይ እስከመፍጠር የሚያስችል ሀይልና ጉልበት ገንብተዋል፡፡ ሟቹ የቀድሞው የናይጀሪያ አምባገነን መሪ ጀነራል ሳኒ አባቻ፤ በናይጀሪያ ነዳጅ አምራች ክልሎች ውስጥ በአንዱ ነዋሪ የሆኑት የኦጐኒ ጐሳ መሪና የመብታቸው ተሟጋች የነበሩትን ባለቅኔውንና ፀሐፌ ተውኔቱን ኬንሳሮዊዋን በግፍ በስቅላት የቀጡበትን መዝገብ መመርመር ለቻለ ልባም፣ የታላቁን የሼል የነዳጅ ኩባንያ ደም የነኩ እጆች አሻራ የሚያገኘው በቀላሉ ነው፡፡የአሜሪካና የአውሮፓ የተለያዩ ባንኮች የደንበኞቻቸውን የአካውንት ዝውውር ሰነድ በግልጽ የሚያሳዩ ቢሆኑ ኖሮ፣ ከናይጀሪያ ወደ ምዕራብ አፍሪካ ተሻግራችሁ የኢኳቶሪያል ጊኒ የእድሜ ልክ ፕሬዚዳንት የሆኑትን የቴወዶሮ ንጉየማምሻሶጐ እና የልጃቸው የቴወዶሪን በባንኮቹ የታጨቀው በብዙ መቶ ሚሊዮን ዶላር የሚቆጠረው ከፍተኛ ገንዘብ፣ ቀላል የማይባለውን መጠን የትኛው የአሜሪካና የአውሮፓ የቢዝነስ ኩባንያ በየትኛው ቀን በሰዎቹ ስም እንዳስገባ በቀላሉ ማወቅ ይቻል ነበር፡፡ ልክ በዚህ አይነት ከሰሜን አፍሪካ ከሊቢያ ጀምረን፣ በምዕራብ በጋቦን አድርገን፣ በምስራቅ በደቡብ ሱዳን አቆራርጠን፣ ወደ ደቡብ አፍሪካ በመዝለቅ፣ ወደ አንጐላ ስንገባ የመጠን ልዩነት ካልሆነ በቀር የምናገኘው ታሪክ ከላይ ከጠቀስነው ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ይህ ግን የታሪኩ ግማሽ ክፍል ብቻ ነው፡፡ ከዚህ በላይ የተዘረዘሩት እውነታዎች የሚያሳዩን የአፍሪካን ከፍተኛ የሙስና ድራማ የመጀመሪያ ክፍል ብቻ ነው፡፡ ድራማው ደግሞ የሚሊዮኖችን የአፍሪካ ህዝቦች ልብና ቅስም የሰበረ ትራጀዲ ድራማ ነው፡፡ የዚህን ትራጀዲ ድራማ ቀጣይ ክፍል ደግሞ ማንም የአፍሪካ ፕሬዚዳንትም ሆነ ሌላ ባለስልጣን አድበስብሶ ሊያልፈው ወይም ሃጢያቱን በሌሎች ላይ በመጫንና የራስን አቧራ በጭብጨባ አራግፎ ዞር የሚባልበት ተራና ቀላል ጉዳይ አይደለም፡፡ በሃያ ሁለተኛው የአለም የኢኮኖሚ ፎረም ስብሰባ ከተካፈሉትና ሙስናን በተመለከተው ስብሰባ ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ጋር የውጭ ኩባንያዎችን ዋና ተጠያቂ አድርገው ከፈረጁት መሪዎች አንዱ የናይጀሪያው ፕሬዚዳንት ጉድላክ ጆናታን ናቸው፡፡ በአፍሪካ ስለተንሰራፋው ከፍተኛ ሙስናም ሆነ ባጠቃላይ ሙስናን በተመለከተ የችግሩን መጠንና ስፋትም ሆነ በሀገርና በዜጐች ላይ ስለሚያደርሰው ጉዳት ምስክርነት ለመስጠት የሚችል ሰው ቢፈለግ ከፕሬዚዳንት ጉድላክ ጆናታን የሚበልጥ ሁነኛ ሰው ፈልጐ ማግኘት በእርግጥም ከባድ ፈተና ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም በፕሬዚዳንትነት የሚመሯት ሀገራቸው ናይጀሪያ ሙስናንና የሀገር ሀብትን በመዝረፍ በኩል ደረጃዋ ወይም ምድቧ ከባለ ከባድ ሚዛኖቹ የሻምፒዮን ሊግ ውስጥ ነው፡፡ ናይጀሪያ ከአመታዊ ብሔራዊ ገቢዋ ምን ያህሉን ከላይ እስከታች በየደረጃው ያሉ መሪዎቿ እንደሚዘርፉትና ይሄው ከፍተኛ የሀገር ሀብት ዝርፊያ ሀብታሟንና ለሌሎች የመትረፍ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ አቅም የነበራትን ሀገርና ህዝቦቿን ለእንዴት ያለ ከፍተኛ የህይወት ፈተና እንደዳረጋቸው በእርግጥም ከፕሬዚዳንት ጉድላክ ጆናታን በበለጠ በእማኝነት ቀርቦ የዚህን አስከፊ ትራጀዲ ድራማ የመጀመሪያ ክፍል ማስረዳት ወይም መተረክ የሚችል ሰው አይገኝም፡፡እንደሌላው የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ኑሮ ጉዳዮች ሁሉ የሙስናንም ጉዳይ በተመለከተ የአፍሪካ መሪዎች የማይነግሩን ወይም እዚህ ግባ የማይባል ምክንያት እየደረደሩ አደባብሰው ለማለፍ የሚሞክሩት የጠቅላላው ታሪክ ሁለተኛው ክፍል ለሁኔታው መፈጠር የሚጫወቱትን ግንባር ቀደም አሉታዊ ሚናና የየራሳቸውን ስህተቶች ነው፡፡ በሌላ አነጋገር የአፍሪካ መሪዎች በሌሎች ላይ ጣታቸውን በመቀሰር ወይም በሌሎች ላይ በማላከክ ሽወዳውን ሊያልፉ የሚሞክሩት ስውርና ግልጽ የሙስና ሁኔታ፣ በየሀገሮቻቸው የፖለቲካና የኢኮኖሚ ስርአት ውስጥ ተዘርቶ እስኪበቅልና ግንድ እስኪያወጣ ድረስ የሚጫወቱት ግንባር ቀደም ሚናና የየግል ሌብነታቸውን ታሪክ ነው፡፡ ማንም እንደሚያውቀው ናይጀሪያ በታሪኳ ከተፈራረቀባት አምባገነን መሪዎቿ ውስጥ በሀገር ሀብት ዝርፊያ ላይ ያልተሠማራና እጁ ያልተልከሰከሰ አንድ መሪ ለሞት መድሀኒት እንኳ ፈለጐ ማግኘት አይቻልም፡፡ የአሁኑ ፕሬዚዳንት ጉድላክ ጆናታንም ቢሆኑ ወደ ፕሬዚዳንትነት ስልጣን ምን ያህል ሀብት ይዘው መጥተው አሁን የባንክ አካውንት ደብተራቸው ምን ያህል መቶ ሚሊዮን ዶላር እንደያዘ፤ የፕሬዚዳንትነት ስልጣናቸው ሲጠናቀቅም ምን ያህል ይዘው እንደሚወጡ አይታወቅም፡፡ ይህ እንግዲህ የአፍሪካን መሪዎች በከፍተኛ ሁኔታ የሚያስሞስኑት የውጭ ኩባንያዎች በባንክ አካውንታቸው ከሚያስገቡላቸው ሌላ በራሳቸው የግል ተነሳሽነት ከብሔራዊው ካዝና በሰበብ አስባቡ የሚቦጭቁት ተደምሮ ነው፡፡ ጉዳዩን ዘርዘር አድርገን እንየው፡፡ በአንድ ወቅት የናይጀሪያ ፕሬዚዳንት የነበሩት ሸሁ ሻጋሪ፤ ፕሬዚዳንት ከመሆናቸው በፊት ናይጀሪያ በሚሊየነርነትጨርሶአታውቃቸውም ነበር፡፡ ከፕሬዚዳንትነት ስልጣናቸው ከተነሱ በኋላ ግን ዘመድ ጥየቃ ብለው ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀሱባቸው በስማቸው የተመዘገቡ ሁለት ጀት አውሮፕላኖች ነበሯቸው፡፡ የኒዠር ዴልታ ግዛት አገረ ገዥ የነበረውና አሁን እንግሊዝ ለንደን ውስጥ በሙስናና በሀገር ሀብት ዝርፊያ ተከሶ በእስር ላይ የሚገኘው ግለሰብ፤ በሶስት አመታት የአገረ ገዥነት ዘመን ብቻ የሁለት መቶ ሃምሳ ሚሊዮን ዶላር ባለቤት መሆን ችሎ ነበር፡፡ ቪያግራ የተባለ ወሲብ ቀስቃሽ ክኒን ውጠው ከስሪላንካና ከህንድ አገራት በግል ጀታቸው ካስመጧቸው ሴተኛ አዳሪዎች ጋር አለመጠን ሲዳሩ ልባቸው ቆሞ እንደሞቱ የሚታሙት አምባገነኑ ፕሬዚዳንት ጀነራል ሳኒ አባቻ፤ በስልጣን ላይ በቆዩበት የአራት አመት ከስምንት ወር ጊዜ ውስጥ ወደ አምስት ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ሀብት ከናይጀሪያ ብሔራዊ ካዝና ዘርፈው ወደ ውጭ አሽሽተዋል፡፡ ከዚህ ከፍተኛ ገንዘብ ውስጥ አብዛኛውን የዘረፉት በራስ ተነሳሽነትና ናይጀሪያን የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ቋሚ አባል እንድትሆን ለማድረግ ነው የሚል ኮሚክ ምክንያት በማቅረብ ነበር፡፡ በአንጐላ በየአመቱ ከአስር እስከ አስራ አምስት ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ሃብት ከብሔራዊ ገቢው የገባበት ይጠፋል እያሉ ራሳቸው አንጐላውያን በይፋ ይናገራሉ፡፡ ለረጅም አመታት በብቸኝነት እየገዟት ያሉት ፕሬዚዳንት ዶስ ሳንቶስ ዝም ብለው ፕሬዚዳንት ሳይሆኑ በአለማችን ካሉት ሚሊየነር (አንዳንዶች ቢሊየነር ናቸው ይሏቸዋል) ፕሬዚዳንቶች ግንባር ቀደሙ እንደሆኑ በሰፊው ይነገርላቸዋል፡፡ የአባታቸውን ስልጣን ወርሰው ጋቦንን በፕሬዚዳንትነት የሚገዙት አሊ ቦንጐ ከአባታቸው ስንት መቶ ሚሊዮን ዶላር እንደወረሱ፤ እሳቸውም በግላቸው ስንት እንዳላቸው ለጊዜው አይታወቅ ይሆናል፡፡ ሚሊየነር ፕሬዚዳንት እንደሆኑ ግን ለአፍታም አያጠራጥርም፡፡ በኢኳቶሪያል ጊኒ እንኳን የውጭ ሀገር ዜጋ የሆነ ቀርቶ የራሷ ዜጐች በትክክል መናገር የማይችሉት አንድ ጉዳይ አለ፡፡ ማንም የኢኳቶሪያል ጊኒ ዜጋ፤ የመንግስቱንና የፕሬዚዳንቱን የግል የቢዝነስ ድርጅቶች ለይቶ መናገር አይችልም፡፡ እጅግ ዝቅ ካለው የጨውና የስኳር የጉልት አይነት የችርቻሮ ንግድ እስከ ከፍተኛው የነዳጅ ዘይትና የጣውላ ንግድ ድረስ አሉ የተባሉት የንግድ ድርጅቶች ከዳር እስከ ዳር የተያዙት በፕሬዚዳንቱና በቤተሰቦቻቸው አባላት ነው፡፡ በተለይ በነዳጅ ዘይት ቢዝነስ ውስጥ ያላቸው ድርሻና ተሳትፎ በርካታና ትልቅ በመሆኑ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒያውያን በነዳጅ ዘይት ሀብት የታደሉት ፕሬዚዳንቱና ቤተሰቦቻቸው እንጂ ሀገራችን አይደለችም እያሉ የደህንነት ጥበቃ አባሎች በሌሉበት ጊዜና ቦታ በግልጽ፣ ያለበለዚያ ግን በሹክሹክታ ይናገሩታል፡፡ የቀድሞው የሊቢያ ፈላጭ ቆራጭ መሪ ኮሎኔል ሙአመር ጋዳፊ በሰይፍ እንደመጡ በሰይፍ ሄደዋል፡፡ በስልጣን ላይ በቆዩበት አርባ አንድ አመታት ሲያደርጉት የነበረውን አስገራሚ ድርጊትና የሊቢያን ከፍተኛ የነዳጅ ዘይት ሽያጭ ገቢ እንዴት ይጠቀሙበት እንደነበር በማስታወስ፣ የሊቢያ የነዳጅ ዘይት ሽያጭ ገቢ የሊቢያ ህዝብና መንግስት ነው ወይስ የሙአር ጋዳፊ ተብሎ የተጠየቀ አንድ ሰው፤ ትክክለኛውን መልስ የጋዳፊ ነው ብሎ ለመመለስ ለአፍታም እንኳ የማሰቢያ ጊዜ ያስፈልገዋል ብሎ የሚከራከር መኖሩ ያጠራጥራል፡፡ አፍሪካ በከፍተኛ የነዳጅ ዘይት ሀብት የታደሉ ከፍተኛ የነዳጅ አምራች ሀገራት አሏት፡፡ ከእነዚህ ሀገሮች መሀል የጥቂቶቹን ስም ዝርዝር ተናገሩ ብንባልና ናይጀሪያ፣ አንጐላ ፕሬዚዳንት ቴወዶሮ ንጉዌማ ሞባሶጐ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ፕሬዚዳንት ኣማር ቦንጐ፣ ጋና፣ ፕሬዚዳንት ሙአመር ጋዳፊ፣ ሱዳን፣ አልጀሪያ ወዘተ…ብለን ዝርዝሩን ብናቀርብ አንድ ማስተካከያ ይቀርብብናል እንጂ ሌላ ስህተት ጨርሶ አይገኝብንም፡፡ ማስተካከያው ኦማር ቦንጐና ሙአመር ጋዳፊ ሟች የቀድሞ ፕሬዚዳንቶች በሚል ይቅረብ የሚል ብቻ ነው፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ ምናልባት በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ የነዳጅ ዘይት ሀብት እንዳላት ሊበሰርላት ይችል ይሆናል የሚል ተስፋ እንጂ ገና ነዳጅ ማምረት አልጀመረችም፡፡ ይህን እኛም መላው አለምም እናውቀዋለን፡፡ ስለዚህ እንደ ሼል ያሉ አለምአቀፍ ግዙፍ የነዳጅ አምራች ኩባንያዎች በናይጀሪያና በኢኳቶሪያ ጊኒ የሚያደርጉትን አይነት እጅ ጥምዘዛና ሌሎች ተጽእኖዎች ቢያንስ ነዳጅ አግኝተን ማምረት እስከምንጀምር ድረስ እዚህ አይኖርብንም፡፡ ለውጭም ሆነ ለሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ከተዘጋጀው በሚሊወን የሚቆጠር ሄክታር የእርሻ መሬት ለውጭ ሀገር አልሚዎች የተላለፈው በጣም ዝቅተኛው መጠን ስለሆነና ቀሪው የአልሚ ያለህ እየተባለ እየተጮኸለት በመሆኑ፣ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ሊከሰት የሚችለው የውጭ ሀገር ኩባንያዎች የአስሞሳኝነት ሚና ከቁጥር የሚገባ ነው ብዬ በግሌ አልገምትም፡፡ከእኔ የተሻለ ለጉዳዩ ቅርበትና መረጃው ያላችሁ ምስክራችሁን ስጡበት፡፡ልክ እንደ ናይጀሪያው ፕሬዚዳንት ጉድላክ ጆናታን ሁሉ የእኛው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊም የውጭ ሀገር ኩባንያዎችን ለአፍሪካ የሙስና ችግር በዋና ምንጭነት ተጠያቂ አድርገዋቸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ይህንን ሲናገሩ፣ ጉዳዩ እርስዎ እንደሚሉት ከሆነ በሀገራችን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ውስጥ ለመሳተፍ ወደ ግል ይዞታ ከተዛወሩት የተለያዩ የመንግስት የኢኮኖሚ ተቋማት ውስጥ ዋና ዋና የሚባሉትን የገዙት የውጭ ሀገር ኩባንያዎች ምን ያህል ሚሊዮን ወይም መቶ ሺዎች ዶላር ለመንግስት ባለስልጣናት በምስጋና መልክ አቀረቡላቸው ተብለው ቢጠየቁ ኖሮ፣ ያለ አንዳች ማመንታት የሚሰጡት መልስ “ይህ በእኛ ሀገር ያልተደረገ አንዳች አይነት ለፍርድ ቤት መቅረብ የሚችል ማስረጃ ያልተገኘበት መሠረተ ቢስ ወሬ ወይም ውንጀላ ነው” የሚል እንደሚሆን ቢያንስ ዘጠና አምስት በመቶ እርግጠኛ ሆኖ መናገር ይቻላል፡፡ ስለዚህ በሀገራችን ውስጥ ከሙጃ ሳርነት ወደ ግራር ዛፍነት ቀስ በቀስ እየተቀየረና ስርና ቅርንጫፉን እያንሰራፋ የመጣው ሙስና፤ የሀገር ውስጥ ስሪት ነው ብለን በሙሉ ልብ መናገር እንችላለን፡፡ ቀደም ብለን በተደጋጋሚ እንደጠቀስነው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ያነሱት የታሪኩን የመጀመሪያ ክፍል ብቻ ነው፡፡ የታሪኩ ክፍል ሁለት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ የሚመሩት ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግም ሆነ ካቢኔአቸው፤ ከፖለቲካው መድረክ በፍጥነት ሊያስወግዳቸው የሚፈልጋቸውን “እድለ ቢሶች” ካልሆነ በቀር የተንሰራፋውን ከፍተኛ ችግር የምር ማስወገድ ባይችል እንኳ ለመቀነስ የሚያስችል የፖለቲካም ሆነ የተግባር ቁርጠኝነት አንዴም እንኳን አሳይቶን አለማወቁ ነው፡፡ የታሪኩ ቀጣይ ክፍል የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ኢህአዴግም ሆነ መንግስታቸው ለበርካታ አመታት በታላቅ ትጋት እያከናወነ ያሳየን በሙሰኝነታቸውና በህገወጥ ስራቸው የተነሳ ህዝብ ያዘነባቸውና የተከፋባቸውን የፓርቲና የመንግስት ሹመኞቹን በህገወጥና በመጥፎ ስራቸው በህግ እንዲጠየቁ ሲያደርግ ሳይሆን በተቃራኒው ከተከፋው ህዝብ አይን ለጊዜው ዞር እንዲሉ ብቻ ወደ ሌላ አካባቢና የመንግስት መስሪያ ቤት አንዳንዴ ይግረማችሁ በሚል እልህ አይነት ተጨማሪ ስልጣን በመስጠት ሲያዛውራቸው ነው፡፡ በታሪኩ የመጀመሪያ ክፍል በከፍተኛ ስሜት በሌሎች ላይ ጣታቸውን የቀሰሩት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ፤ በቀጣዩ ክፍል ያልነገሩን ወይም የተለያዩ ውሃ የማያነሱ ምክንያቶችን በመደርደር አድበስብሰው ለማለፍ የሞከሩት፣ ለመዝረፍና ለማስዘረፍ ከማንኛውም ዜጋ የበለጠ እድልና ስልጣን ያላቸው ዋና ዋና ሌቦች ወይም ሙሰኞች የመንግስት ሌቦችና ሙሰኞች የመሆናቸውን ታሪክ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ያልነገሩን የግሎቹ ሌቦች የተፈጠሩትና ዝምባቸው እሽ እንዳይባል ስልችት እስኪለን ድረስ መረጃ እንጂ ፍርድ ቤት ማቅረብ የሚያስችል ማስረጃ ልናቀርብባቸው አልቻልንም እየተባለላቸው እንደፈለጉ እየሆኑ ያሉት መለኮታዊ ስልጣን ከላይ ቤት ተሰጥቷቸው ሳይሆን የበላይ አካል ከለላና ጥበቃ ስላላቸው የመሆኑን ታሪክ ነው፡፡ እንግዲህ ከዚህ በላይ የተዘረዘሩት ጉዳዮች ግልጽ የሚያደርጉልን አንድ ዋና ቁም ነገርን ነው፡፡ የአፍሪካ መሪዎች ዛሬም ቢሆን የመረጡት ለችግሮቻቸው መፈጠርና መንሠራፋት የራሳቸውን ሚና መደበቅና ሌሎቹን መውቀስና ማውገዝን ነው፡፡ ይህ ደግሞ ትርፉ ከንቱ ድካም ብቻ ነው፡፡ ለምን ቢባል መሪዎቹ የቻሉትን ያህል ቢያድበሰብሱትና በሌላ ላይ ቢያላክኩት የታሪኩን ቀጣይ ክፍል ህዝቡ ብጥርጥር አድርጐ ስለሚያውቀው ነው፡፡ እንዲህ ያለ ነገር ሲያጋጥማቸው የማሊ ዜጐች “አንዱ በር ሲዘጋ ሌላኛው ይከፈታል” በማለት ይተርታሉ፡፡ እውነታቸውን ነው፡፡ የአፍሪካ መሪዎች የገመናቸውን አንዱን በር ተረባርበው ሲዘጉት፣ ህዝቡ ደግሞ ሌላኛውን የገመና በር በቀላሉ ይከፍተዋል፡፡ መጨረሻ ላይ ለህዝቡና ለመሪዎች የሚቀረው መተዛዘብ ብቻ ነው፡፡ ክ ፕሬዚዳንት ጉድላክ ጆናታንና ጠቅላይ ሚኒስትር መለስን በአለም የኢኮኖሚ ፎረም ስለሙስና

በተደረገው ስብሰባ ላይ እንደታዘብናቸው፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Read 2867 times Last modified on Saturday, 09 June 2012 08:01