Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 09 June 2012 07:19

“አልሙእሚኑ ሰይኑን ለይን”…

Written by 
Rate this item
(0 votes)

“አማኝ ሰው ለስላሳ ነው”

ዘመድ ነኝ/ ከልደታ/
በሁሉም ቤተ - ሃይማኖት በዚህ ዘመን “…እያንዳንዱ ጐረቤቱን፤ እያንዳንዱም ወንድሙን ጌታን
(አላህን) እወቅ ብሎ አያስተምርም፤ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያውቁኛልና” (ዕብ 8÷11) ምክንያቱም ሰው ሁሉ በተማረበትና በሠለጠነበት ዘመን አንብቦ፣ አስቦ፣ አገናዝቦ፣ መርምሮ፣ ጠይቆና አውቆ በገዛ ህሊናው “አምላክ” አለኝ! ብሎ ማመኑ እንደማይቀር፣ (ባያምንም እንኳ ማወቁ እንደማይቀር) የሚገልጽ ቃል ነው፡፡ በመሆኑም በኃይልና በክርክር ስሜት እኔ ያልኩት ካልሆነ! የኔ ካልበለጠ! በሚል መገፋፋትና ጫና መፍጠር ለአምላክ ቀንቶ እንደማገልገል ከታሰበ ውጤቱ መንፈሳዊ (ሃይማኖታዊ) ሳይሆን ጠባሳው ከሥጋዊ (ፖለቲካዊ) ግጭትና ጥፋት ስለማይዘል በህግም ወንጀለኛ፣ በአምላክም ኩነኔ አለበትና ንፁህ ሰው በጥፋትና ግጭት በመተባበር የገዛ ራሱን ሃይማኖት አያስነቅፍም፡፡ የቀደሙት ቅዱሳንና ነቢያት የሃይማኖትን ዋጋ አውቀው በእምነታቸው ፀንተው የሚደርስባቸውን ግፍና በደል ታግሰው አስተማሩ፣ መሰከሩ፣ መልካም የሆነውን ለሰው ልጅ ሠሩ፡፡
እኛም ሁላችንም በታሪክ ብቻ ልናውቃቸው፣ በአፍ ብቻ ልናወራቸው ሳይሆን “ሃይማኖታችንን በጥሩ ሥነ - ምግባር” ጠብቀን ልንከተላቸው ምሳሌ ልናደርጋቸው እንጂ ለዝና፣ ለክብር፣ ለጥቅም፣ ለፖለቲካ ጉዳይ ሃይማኖትን መሸሸጊያ ማድረግ ለሚፈልጉ ሁሉ መመሳሰሉን ትተን የማናየውን “አምላክ”
የሚያስረዳንን ሃይማኖት በተስፋና በእውነት እንጠብቅ፡፡ በተለይም “እውነትን ለሰዎች እንዳይደርስ የሚያግዱትን አማኞችን የሚወጉትን!”ዟሊም” በደለኞች ጋር የሚወግኑትን ሁሉ ኢስላም ያስጠነቅቃልበ2ኛ ጴጥ 3÷16 “ያልተማሩትንና የማይፀኑትን ሰዎች ለማታለል ሌሎችን መጻሐፍት እንደሚያጣምሙ ቅዱስ መጽሐፍን ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ” ይላል፡፡ አል - ሙምተሒናህ፡፡ ክፍል 28÷ 7-9 “ኢስላም ቤቱን የሚወጉበትን፣ አምነው የሚክዱትን ባይወዳጅም “አላህ ጥበበኛ ነው” በማለት ሰላም ፈላጊ የሆኑትን መልካምና ፍትህ ያለው እንጂ በሃይማኖት ልዩነት የሰው ዘርን ለማጥፋት፣ ሀገርን ለማሸበር ራሱን ቢያጠፋ እንደሚፀድቅ በቅዱስ ቁርዓን አልተፃፈም፡፡የእምነቱን መርህ (ሥርዓት) ጠንቅቆ በተረዱት ውስጥ እንዲህ ያለ ትርጉም የለም፡፡  በሚወጉት፣ እምነቱን በመንቀፍ ግፍና በደል ሲፈፀም በትዕግስት መክሮ ካልተሳካለትና በወረሩት ጊዜ ሊመክት ሊነሳ ይችል ቢሆንም፤ አብይት በሚኖር ወንድሙ፣ ሚስትና ልጁ፣ ጐረቤትና ሃገሩ አመጽን፣ ስደትን፣ ጦርነትን የሚቀሰቅስ ህዝብም፣ ሃይማኖትም አይደለም፡፡ ህን ጽሑፍ ለመፃፍ መነሻ የሆነኝ በገጠር እንዲህ ተፈፀመ፣ አዲስ አበባ ተከፋፍለው ተጣሉ፣ መንግስትንም ጣልቃ ገባብን የሚሉ እንዳሉ በሰማንበት ወቅት “እኛ የሴት ወገን ሽማግሎች ክርስቲያን፣ የወንድ ወገን ሽማግሎች ሙስሊም” ሆነን ስንደራደር ከዚህ ታሪክ ፀሐፊ በቀር ሁሉም በሳል አዛውንቶችና ጐልማሶች ነበሩ፡፡ እያንዳንዳቸው በንግግራቸው ውስጥ “እኛ እንደሆን መቼም አንድ ነን” ሙሽሪትና ሙሽራውን አላህ (እግዚአብሔር) ይባርክልን በማለት ሁሉም እንደ ባህሉ (ብሔሩ ወግና ቋንቋ) እንደ እምነቱ ፀሎትና ምርቃት አወረቀ፡፡ ቡፌውም አንድ ዓይነትና እኩል ለሙስሊሙም ሙስሊም ሴት አስተናጋጆች፤ ለክርስቲያኑም የክርስቲያን ሴቶች ሲያስተናግዱ በማየት የነበረውን የኢትዮጵያዊነትና ትክክለኛ ሰውነት ገምቼ ስለተመሰጥሁ “ከፍቅር በላይ ምን አለ?” አልኩና ይህን ለመፃፍ ተነሳሳሁ፡፡ እናም አማኝ ሰው የእምነቱን ዶግማ (አይለወጤ - መርህ)፣ ቀኖና (ሥርዓት) ጠንቅቆ ማወቅ አልያም መማር ይኖርበታል፤ እንጂ ባለማወቅ በስሜቱ ብቻ ለእምነቱ የቀና እየመሰለው ባንድ እምነት ውስጥ ያሉትን በመከፋፈል ወይም ያንዱን እምነት ከሌላው እያጋጩ፤ ህዝብን በህዝብ፣ ብሔርን ከብሔር ማቃቃር ከፖለቲካ አንፃር የሚታይ እንጂ ከሃይማኖት የመጣ ነው ሊባል አይችልም፡፡ ይህም በመሆኑ ደግሞ ሁላችንም በጋራ ሃገራችንና በህዝብ ሰላም ዝም ልንልና በምን አገባኝ ስሜት የምንታዘብበት ሳይሆን ጉዳያችን ነው!!በጥሩ ሥነ-ምግባሩ የጠነከረ፣ የታፈረና የተከበረ የኢትዮጵያ ህዝብ ትዕግስቱም ሆነ ጀግንነቱ መሠረቱ እምነቱ እንጂ ጠብ አጫሪነቱ አይደለም “ወማ አርሰፍናከ ኢለ ራህመተን ሊልአለሚን” ቅ.ቁርዓን 21÷ 107 ሙሐመድ ሆይ ለዓለማት እዝነት አድርገን እንጂ አልላክንህም፤ ይህን የመሰሉ ተነግረው የማይጠገቡትን፣ ተጠቅሰው የማያልቁትን የመጽሐፍ ቃል እየተውን በከንቱ እየተቀናናን ያልታዘዝነውን ሰይፍ እየመዘዝን ጥፋትና ወንጀል፣ ግፍና በደል እርስ በርሳችን ስንፈጽም እውነት የሃይማኖት ፍቅር፣ የእግዚአብሔር ክብር አስጨንቆን ይሆን?አምላክ እኮ ለሰው ልጅ ነፍስ ብቻም ሳይሆን ለትንሿ ትልም ህይወት ይጨነቃል፤ ያለአግባብ ከሱ ፈቃድ ውጭ እንድትጠፋበት አይፈቅድም፡፡ ፈጥሯታልና!ህዝቦች ሆይ! ጥሩውን ጥሩ፣ መጥፎውንም፤ መጥፎ! እንበል፡፡ “መልካም ምክር ከሌለ ህዝብ ይወድቃል፤ በመካር ብዛት ሰላም ይሆናል” ምሳ 11÷4 ይህ ቃል ከስሜት የፀዳ፣ ከፖለቲካ የራቀ፣ ሁሉን የሚታደግና የሚያድን ነው፡፡ የሠለጠነ ህዝብ ለሥርዓት፣ ለህግ፣ ለምክርና ለፍቅር ይገዛል፡፡ ከዚህም በላይ የአንድ ፈጣሪ፣ የአንድ አባት ልጆች ነን፡፡ ያውም የነቢዩ (የፃድቁ) የአብርሃም (የኢብራሂም) ልጆች!
ይህ ማለት ለውርስ እንደሚጣሉ ልጆች፣ ለሥጋ፣ እንደሚከሉ ውሾች ባለመሆናችን እኛ ሐበሾች ለኢትዮጵያ “ልዩ ፀጋ” ምልክቶች ነን፡፡ ህብር ሆነን አንድ ላይ በመኖር ዓለምን የምናስደንቅ የቃል - ኪዳን ልጆች ነን፡፡ “ኢስላም ሰለምሀ፣ ክርስቶስ ፍቅር” ነው፡፡ በምግባርም አብረን በመኖር በምሳሌነት የምንጠቀስ አንድ ህዝብ እንጂ የምንጠላላ ሁለት ህዝብ አይደለንም፡፡ “አስተዋይ አገልጋይ በንጉስ ዘንድ ይወደዳል” ምሳሌ 15÷1 ከዚህ ቃል የምንረዳው ያለፉት አባቶች በነገርም ሁሉ ለእግዚአብሔር ሰማያዊው ንጉስ በምድርም ለመሪዎቻቸው ታምነው አስተምረዋል!፣ ሠርተዋል!፣ ሞተዋልም፡፡
አሁን ግን በነሱ ታሪክ መኮፈስም፣ መካሰስም ብልህ አያሰኝም፡፡ ይልቅስ ከጉርብትና እስከ ጋብቻ፣ ከዜግነት እስከ ሰውነት ያለንን የደም አንድነት እያሰብን “እርስ በርሳችን እንዋደድ”እኛ ግሪክም፣ ሮማዊም፣ አይሁዳዊም፣ አረባዊም አይደለንም!፡፡የእስራኤል፣ የአሜሪካም፣ የኢራቅና ኢራን፣ የቻይናና ኮሪያ፣ የጀርመንና የእንግሊዝ ጉዳይ (አልሻባብም ሆነ አልቃይዳ) ከፖለቲካ ፋይዳና ጥቅም የሚነሱ እንጂ ለእኛም ለአላህ (ለእግዚአብሔርም) የሚመቹ አይደሉም፡፡ ስለዚህም ወገኔ ቀዳዳ ልንፈጥር አይገባም፡፡ ዘመኑን እየተረዳን (እየዋጀን) በጥበብ እንኑር፣ እንመካከር ቆላ 4÷5 ለማደግ ስንጥር በማይረባ ነገር እየተነቃቀፍን ተጠላልፈን ሳንወድቅ እንደሰው በተረዳንበት፣ በተሰለፍንበት፣ ሁሉ ለእምነታችንም፣ ለሀገራችንም ጥሩ ታሪክ በመሥራት እንለፍ፣ የጥልን ግድግዳ በማፍለስ፡፡ “ፍቅር የህግ ፍፃሜ ነው” ሮሜ 13÷10፣ ገላ 5÷13

 

 

Read 2689 times Last modified on Saturday, 09 June 2012 07:40