ጠንከር ያለ አለንጋ መግዛት (በደንብ ሾጥ የሚያደርግ)
ጋላቢዎቹን መቀየር (ፈረሱን ሳይሆን)
የሞተውን ፈረስ በግምገማ ማጣደፍ
የፈረሱን ጀርባ የሚያጠና የግምገማ ኮሚቴ
ማቁዋቁዋም
ቻይናን የመሳሰሉ ወዳጅ አገራት በሞተ ፈረስ
ላይ እንዴት እንደሚጋልቡ ልምድ ለመቅሰም
የስራ ጉብኝት ማመቻቸት
የሞተ ፈረስ በህይወት ካሉት ጋር እኩልነቱ
ተጠብቆ እንዲታቀፍ ማድረግ
የሞተ ፈረስ ሙት ሳይሆን “የህይወት ጉዳተኛ”
ተብሎ እንዲጠራ መወሰን
የሞተውን ፈረስ እንዲጋልቡ የቻይና
ኮንትራክተሮች መቅጠር
የሞቱ ፈረሶችን በ1ለ5 በማደራጀት አቅማቸውን
ማጎልበት
የሞተውን ፈረስ ለማብቃት የአቅም ግንባታ
ስልጠና እና/ወይም የበጀት ድጎማ መስጠት
የሞተ ፈረስ ጫና ቢቃለልለት አቅሙን ያሻሽል
እንደሆነ የምርታማነት ጥናት መስራት
የሞተ ፈረስ ቀለብ አለመፈለጉ › ወጪ ቆጣቢ
መሆኑ ለኢኮኖሚው ከሌሎች በህይወት ካሉ
ፈረሶች የላቀ ፋይዳ እንዳለው በይፋ ማወጅ
የአቅም መስፈርቶችን በተመለከተ ለሁሉም
ፈረሶች ተጨባጭ ሁኔታውን ከግንዛቤ ውስጥ
ያስገባ ክለሳ ማከናወን
የሞተውን ፈረስ ወደ ቁጥጥርና ግምገማ ክፍል
ማሳደግ
እንደ መጨረሻ አማራጭ በኢንተርኔት (Ebay)
መሸጥ