Saturday, 02 June 2012 08:58

ኦማር ኻያም አሁን OMAR KHAYAM The Now

Written by  ከበደ ደበሌ ሮቢ
Rate this item
(0 votes)

አንጋፋው ኢራናዊ ባለቅኔ ሊቀ ሊቃውንትና የሥነ ክዋክብት ሳይንቲስት ኦማር ኻያም ከጠዘኝ መቶ ሃምሣ ዓመታት በፊት እ.ኤ.አ በ1048 (በእኛ በ1040 ዓ.ም) ተወለደ፡፡ በዚህች ምድር ላይ ለሰባ አራት ዓመታት የኖረውና በ1122 (በእኛ በ1114 ዓ.ም) ያረፈውና ያለፈው ይህ የጥንታዊት ፋርስ ወይ ፐርሺያ አንጋፋ ባለቅኔ የፃፋቸውን ግጥሞችና ቅኔዎች ሁሉ በፃፈበት ሥፍራ ነው ትቶ የሚሄደው፡፡ ኡመር ኻያም ባለቅኔ ብቻ ሳይሆን ሳይንቲስትና ሊቀ ሊቃውንት መሆኑን፤ አሜሪካዊው ተመራማሪና የዩኒቨርሲቲ ሌክቸረር ዶክተር ዋይኒ ደብሊው ዳየር ከፃፋቸው ሃያ የመርምር መፃሕፍት አንዱ በሆነው “wisdom of the ages sixty days to Enlightenment”  ላይ ሲጽፍ፤ “Omar khayam was a scholar & Astronomer who lived in Iran. His poetry reflects his thoughts about the deity, good & evil, spirit matter, & destiny” ብሎአል፡፡

የስምንት ልጆች አባትና የሶስት የትምህርት መፃሕፍት ጭምር የፃፈው ዋይኒ ዳየር፤ በዚህ ስለ ታላላቅ ሰዎች ሰብዕና በተፃፈ መጽሐፉ ስለ ኦማር ኻያም ማውሣት የሚጀምረው፤ The Now አሁን ወይም አሁኑኑ በሚል ምዕራፍ ሥር ነው፡፡ አሁን እና እዚህ (Now & here) የሚለው አስተሳሰብ (ንድፈ ሃሳብ) Existentialism በተሰኘው የመላው ዓለም ሥነ ጽሑፍ የዕድገት እርከን ውስጥ ብቅ ካለ ሁለት መቶና ሶስት መቶ ዓመት እንኳ አይሞላውም፡፡ የዚህ ንድፈ ሃሳብ ባለቤቶች ሁለቱ ፈረንሣውያን ከፍተኛውን ዓለምአቀፍ የሥነጽሑፍ ሽልማት ያገኙት - Literary & Philosophical Essays የሚለውን ዝነኛ መጽሐፍ የፀፈው ዣን ፖል ሳርትርና የThe stranger ደራሲ አልበርት ካሙ (ሥ) ናቸው፡፡ በፈረንሳይኛ አልበርት ካሙ፤ በእንግሊዝኛና በሌሎች ቋንቋዎች አልበርት ካሙስ - ልክ የአምስት መቶ ልጆች አባት የሆነው The count of Monthechristie (የሞንቴክሪስቴ ደሴት መሥፍን) የተሰኘውን ድንቅ መጽሐፍ የፃፈው አሌክሳንደር ዱማ ፔሬ ከፈረንሣይ ውጪ አሌክሳንደር ዱማስ ፔሬ እንደሚባለው ሁሉ፡፡ በዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ፈረንሳይ የተባለችዋን አገር በክብር ምዕራፍ የፃፈው ዚነዲን ዚዳን፤ የወላጆቹ ሥረ መሠረት (Roots) ሰሜን አፍሪቃ አልጄሪያ ነው፡፡ አልበርት ካሙ በቅኝ ግዛት ዘመን አልጄሪያ ውስጥ ሆኖ ፈረንሳዮች አልጄሪያን ቅኝ መግዛታቸውን ሊቃወም አድናቂ ወዳጆቹ ጠሩትና የገንዘብ ቦርሣህን አሳየን አሉት፤ አሳያቸው፤ ቦርሳውን በገንዘብ ሞሉለትና ወደ ፈረንሣይ ሂድ፤ እዚህ ከቆየህ ይገድሉሃል…

ኦማር ኻያም ኢግዚንሴሺያሊስት ነው፤ አሁንና እዚህ ይኖራል፤ አሁንና እዚህን ይጽፋል (Now & here) Existentialism የሚለው ንድፈ ሃሳብ በሥነ ጽሑፍ ጥበብ ደምቆ የታየው ባለፈው መቶ ዓመት ቢሆንም ከ2000 ዓመታት በፊት ኢየሱስ ክርስቶስ ለነገ ክፋቱ ይበቃዋል ብሏል፡፡ ከ1400 ዓመታት በፊት ነቢዩ መሐመድ ሲተኙ ሁል ጊዜ የመጨረሻውን ሌሊት ነው የሚተኙት ስለ ነገ እርሱ ያውቃል…እዚሁ በአገራችን በኮሜዲ ጥበብ የተካነችው እንግዳዘር ነጋ ሁልጊዜ ምሽት ማረፊያ ማደሪያዋ ላይ ጋደም ስትል፤ ነገን በህልውና (በህይወት) ስለመዝለቄ እርግጠኛ አይደለሁም ብላ ነው፡፡ ትንሽ ትህትናና ቁጥብነት በተሸረፈለት አቀራረብ ዛሬ ሌሊት ሞታ እንደምታድር ነው የምታስበው፡፡ ኦማር ኻያም በፋርስ ቋንቋ ጽፏቸው፣ በፃፈባቸው ሥፍራዎች ትቶአቸው የሄደው ግጥሞችና ቅኔያዎች ተሰባስበው በእንግሊዝኛ ቋንቋ እንዲታተሙ በማድረግ የመጀመሪያ የሆነው ሰው ፊትዤራልድ ሲሆን The Rubaiyat of Omar Khayam የሚል ርዕስ ተጠቅሟል፡፡ በመላው ዓለም ከሚገኙ ስድስት ሺህ ቋንቋዎች ጥቂቶቹ የራሳቸው ፊደል ያላቸው ናቸው፤ ከነዚህ ውስጥ የኢንዶ ዩሮፕያን ዝርያ ሥረ መሠረት ያላቸው ፐርሷያን (ፋርሶች) የፋርስ ቋንቋ ነው፤ የፋርስ ቋንቋ የራሳቸው ፊደል (ሆሄያት) ካላቸው ጥቂት የዓለም ቋንቋዎች አንዱ ብቻ ሳይሆን ከቀኝ ወደ ግራ ከሚፃፉ ሶስት ቋንቋዎች አንዱ ነው፤ ሁለቱ አረብኛና ሂብሩ ወይ እብራይስጥ ናቸው፡፡

የኦማር ኻያምን በፋርስ ቋንቋ የተፃፉ ግጥሞችና ቅኔዎች ፊት ዤራልድ ወደ እንግሊዝኛ ተርጉሞ ሲያሳትም፤ ከአሥራ ዘጠኝ ዓመታት በፊት የኦማር ካያም ሩብ አያቶች ብሎ በአማርኛ የተረጐመውና በመድብል መጽሐፍ ያሳተመው ኢትዮጵያዊ የዩኒቨርሲቲ መምህር፣ በቲያትር ጥበብና በሥነ ጽሑፍ የተካነው አዛውንት ጠቢብ ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሠሠ ነው፡፡ ጋሽ ተስፋዬ ተርጉሞ በመድብል ያሳተመውን በብሔራዊ ቲያትር መድረክ በቃሉ በቃለ ትረካ በዜማ አስደምጦን አስደመሞናል፡፡

The Moving Finger Writes, having writ moves on nor all thy piety nor wit shall lure it back to cancel half a line

Nor all thy tears Wash out a word of it

የሚሉት ስንኞች ዶክተር ዋይኒ ዳየር ከኦማር ኻያም ሩብአያት የግጥምኔ ቅኔ የእንግሊዝኛ መድብል ቆንጥሮ ለአንጋፋው ፋርሣዊ ባለቅኔ ሳይንቲስትና ሊቁ ፈላስፋ ሰብዕና መገለጥ እንደ መግቢያ የተጠቀመበት ነው፡፡ ጋሼ ተስፋዬ በአማርኛ ተርጉሞ ያሳተመውን መድብል መግቢያ የፃፈው የእኛው ታላቅ ደራሲና ጋዜጠኛ፤ ተርጓሚና ኤዲተር (ህፃን ነፍስ) ጋሼ ስብሃት ለአብ ገብረአግዚአብሔር ነው፡፡ ከአሥራ ዘጠኝ ዓመታት በፊት በ1985 ዓ.ም ያነበብኩትን ይሄን መግቢያ አስታውሰው እንደኹ፤ መሬት ጠብ የማይል ፍሬ ነገር አለውና እነሆ፡-

ኦማር ኻያም አዛውንቱ ፈላስፋ ሳይንቲስትና ባለቅኔ ለመጨረሻ ጊዜ ለወዳጆቹ የታየው በኢራን ርዕሰ ከተማ በቴህራን ዩኒቨርሲቲ አጠገብ ሲያልፍ በሰባ አራት ዓመት የሽምግልና ዕድሜው ነው፡፡ የሚገርመው የጋሼ ስብሃትን ሠባ ስድስተኛ ዓመት ልደት ያከበርነው ባለፈው ሚያዝያ ነው፤ ጋሼ ተስፋዬ ገሠሠ ሊቀ ጠቢቡ ሠሎሞን ደሬሣ፤ ደራሲና ተርጓሚው ሳህለ ሥላሴ ብርሃነ ማርያም፡፡

በዚህ የዕድሜ ግድም የሚገኙ ናቸው፡፡ ኦማር ኻያም በቴህራን ዩኒቨርሢቲ አጠገብ ሲያልፍ ዩኒቨርሢቲው እየታደሠ ነበር፡፡ ለዕድሣት ግንባታው አንድ ድንጋይ የተጫነ አህያ ወደ ዩኒቨርሢቲው ግቢ እንዲገባ ባለአህያው እየቀጠቀጠ ሊነዳው ይሞክራል፤ አህያው ከቆመበት ንቅንቅ አልል አለ፡፡ ይሄን የተመለከተው ኡማር ኻያም፤ አህያ ነጂውን፡- ቆይ አለው፤ ቆይ አትቀጥቅጠው፡፡ አህያ ነጂው ከድብደባው ተግ ጋብ ብሎ ፈንጠር ብሎ ቆመ፡፡ ኦማር ኻያም ወደ አህያው ሄደና በጆሮው አንሾካሾከ፤ በዚህን ጊዜ ድንጎይ የተጫነው አህያ በፍጥነት ወደ ዩኒቨርሢቲው ግቢ መግባት ጀመረ፡፡ አህያ ነጂው ተገርሞ ኦመር ኻያምን፡- ምን ብለህ ብትናገረው ነው፤ እንደዚህ መሾሩ ሽር ቱር ማለቱ … በሚል መጠየቃዊ መንፈሥ ቢያይ፡- አየህ አለ ኦማርኻያም ይሄ አህያ፡- አህያ ሆኖ ከመጠፈሩ በፊት የዚህ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሠር ነበር፤ ፕሮፌሰር ሆኜ ባስተማርኩበት ዩኒቨርሲቲ እንዴት ድንጋይ ተጭኜ እገባለሁ ብሎ ነው፤ በጅ አልል ያለህ፡፡ እኔ፡- ቀስ ብዬ በጆሮው ዛሬ አህያ ሆነህ ብትፈጠርም በሚቀጥለው የነፍሥ ዑደት (ሪንካርኔሽን) አገረ ገዢ ሆነን ትመጣለህ (ትፈጠራለህ) ብለው ይኸው እንደምታየው ሳይደበደብ ሳይቀጠቀጥ ሰተት ብሎ ወደሚታደሠው ዩኒቨርሢቲ ግቢ ገባልህ…

ኦኦማርኻያም ከተወለደ አንድ ሺህ ዓመት ግድም ሆነው ይለናል፡- The moving Finger (ለመፃፍ የምትንቀሣቀሠው ጣት) የሚለውን የአንጋፋውን ኢራናዊ ጠቢብና ሊቅ ግጥም ለመባቻነት የተጠቀመው ዶክተር ዋይኒ ዳየር፡- Almost a thousand years have passed Since the Birth of Omar, The World’s most Famous tent-maker, Poet, & Astronomer all rolled into one brilliant Philosophical Storyteller…

The Now በሚል ንዑሥ ርዕሥ ሥር እንደሰፈረው የዶክተር ዋይኒ ደብሊው ዳየር አስተሣሰብ፡- በህይወታችን ውስጥ ካሉ የተሣሣቱና የተዛቡ ግንዛቤዎች (ቅዠቶች) አንዱ ስለ አሁኑ ህይወታችን ያለፈውን ጊዜ ተጠያቂ አድርገን ማመናችን ነው፡፡ One of Life’s greatest illusions us the belief that the past is responsible for the current Conditions of our lives … ይሁንና ይለል ይሄ ፅሁፍ (የዚህ ፅሁፍ አቅራቢ)፡- ይሁንና ማናቸውም ክስተትና ኑባሬም ሆነ የሠው ልጅ አሁንና እዚህ ባለበት የህልውና ሁናቴ ውስጥ በኋላ ትዝታውና በፊት ለፊት ባለተስፋው መሀከል ሆኖ ነው የሚታየው፡፡ የኋለኛ ህይወቱ በወደፊት ህልውናው ላይ በጐም ሆነ መጥፎ ምልክቶች ሊኖሩት ይችላሉ፤ የምንም ነገር ተፈጥሮና አኗኗር መሠረታዊ ባህሪውን መነሻና መድረሻ ያደርጋል፡፡፡ ይሄንን መሠረታዊ ባህሪ ጠንቅቆ ለመረዳትና ለማንፀር ደግሞ ሥረ ሥራ መሠረትን (Roots) ማየት አንዱ ዋነኛው ነገር ነው፡፡ የምንም ነገር ሥረ መሠረት ወይም ሥርወ አመጣጥ ወይም ሥርወ አፈጣጠር ለመጠናት ለመንፀርና ለማንፀር የሚመቸው ከኋላ ወይም ከነባራዊው ህልውና ሊጀምሩት ነው፡፡

ለመፃፍ የምታንቀሣቅሰው ጣት በቀጥታ ከልብህ ጋር ህያው ግንኙነት አለው ይላል ዋይኒ ዳየርኦማርኻያምን መሠረት አድርጐ፡፡ እናም የፈለግከውን ምርጫህ የሆነውን (የመረጥከውን) ለመፃፍ ይቻልሃል፡፡ The essential lessons of this quatrain include ይልና ዋይኒ ዳየር የተወሰኑ ፍሬ ነገሮችን ያክላል፡፡ አንዱ ፍሬ ነገር ዛሬ ኑር (ዛሬን ኑር) የሚል ነው፡- Live today

ዛሬ ኑር፡- አንተ አሁን በዛህ ሠዓት በምርጫህ እያደረግክ (እየከወንክ) ያለኻቸው ክንዋኔዎች ውጤት ነህ፡፡ እናም ዛሬን እክል ያለበት የክንዋኔ ሂደት ሊያደርግብህ የሚቻለው አንዳች የለም፡፡ ይሄ ሀሜት ደግሞ እንዲሰማህ ያስፈልጋል፡፡ የቀድሞውን ማማረር፡- የሚለውን ቃልና ሀሣብ ከአእምሮህ መዝገበ ቃላት ውስጥ አስወግድ፡፡ ሀሣብህ የዛሬውን ውድቀትህን ወይም ያለመሣካት መነሾ ካለፈ ታሪክህ ምክንያታዊነት ውስጥ ለመንቀስ ሲፈልግ ይሄን ጊዜ አእምሮህን ያዘው፡፡ እናም የባለፈውን በማማረር ምትክ ለራስህ እንደዚህ በል፡- I am free now to detach myself from what used to be

አሁን፤ ያለፈውን የምታስብ ከሆነ፡- ያለፈው አለ፡፡ ነገር ግን አሁን (Now) የለም፡፡ በሌላ አቀራረብ፡- የባለፈውን እንዲያስብ ለአእምሮህ ዕድል በሠጠህበት አሁን ውስጥ፤ የባለፈው እንጂ አሁን የሚባለው የለም፤ የባለፈውን በማውጠንጠን መጠመድ አሁንን እንዳትኖረው (አሁንን እንድታጣው) ያደርግሃል፡፡ የባለፈውን በማሠብና በማውጠንጠን አእምሮህ በተጋበት በዚህ አሁን በምንለው ጊዜ፡- የባለፈው አለ፤ የወደፊት መጪው ጊዜም አለ፤ አሁን የምንለው ይሄ ቅፅበት ይሄ ሂደት ግን የለም፡፡ እናም ዛሬ ኑር፤ በዚህ ከአንድ ሺህ ዓመት በፊት በተገለጠ ቀላል (ቀለል ያለ) እውነት የዛሬው ዘመን ህይወታችንም የተፃፈ ሊሆን የተገባ ነው፡- From a thousand years ago grasp this Simple Truth & write your life with it.

ሠላምዎ ይብዛ! በፍቅር!

Soli.Deo.Gloria!

 

 

Read 2603 times Last modified on Saturday, 02 June 2012 09:02