በኢትዮጵያ የሕፃናት የአዕምሮ ጤና አገልግሎት እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተነገረ። ከጤና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፤ አጠቃላይ የአዕምሮ ጤና ባለሙያዎች ቁጥር ከ1,900 በላይ ቢሆንም፣ ውስብስብ የሕፃናት የአዕምሮ ሕመሞችን በስፔሻሊስት ደረጃ ማከም የሚችሉት ባለሙያዎች አራት ብቻ ናቸው። እነዚህም ባለሙያዎች የሚገኙት በአዲስ አበባ በሚገኙት ጥቁር አንበሳ እና ጳውሎስ ሆስፒታሎች ውስጥ ብቻ መሆኑ ችግሩን የባሰ የከፋ አድርጎታል።
በሌላ በኩል በሀገሪቱ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ከ2 ሺህ በላይ የሳይካትሪ ባለሙያዎች ቢኖሩም፣ በተለያዩ ምክንያቶች በሥራ ላይ እንዳልዋሉ ተመላክቷል። እነዚህን ባለሙያዎች ወደ ሥራ በማስገባት አገልግሎቱን ማስፋፋት እንደሚቻል ቢታመንም፣ አሁን ላይ ግን ከ15 ዓመት ጀምሮ የሚጀምሩ የአዕምሮ ጤና ችግሮች እና ከ15 እስከ 64 ዕድሜ ያሉ ዜጎች ከፍተኛ ጉዳት ላይ ይገኛሉ።
Dagu Journal-

