የዓለም አትሌቲክስ 18ኛውን የ2027 የዋንዳ ዳይመንድ ሊግ የውድድር መርኃ ግብር ይፋ ያደረገ ሲሆን፣ ውድድሩ እ.አ.አ ግንቦት 7 ቀን 2027 በኳታር ዶሃ ተጀምሮ በአራት አህጉራትና በ15 ከተሞች ተካሂዶ በነሐሴ 25 እና 26 በስዊዘርላንድ ዙሪክ ከተማ ለሁለት ቀናት በሚደረግ የፋይናል ውድድር የሚጠናቀቅ ይሆናል። አትሌቶች በ32 የውድድር ዓይነቶች ነጥብ በመሰብሰብ ለዳይመንድ ዋንጫና ለገንዘብ ሽልማት የሚፎካከሩበት ይህ ውድድር፣ በቀጣዩ መስከረም ወር በቤጂንግ ለሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ትልቅ የአቋም መፈተሻ እንደሚሆን ተገልጻል።

