Monday, 12 October 2026 15:27

“ለገዛ ሴት ልጆቼና የልጅ ልጆቼ የምመኘውን ሁሉ ለሁሉም ሴት ልጆች እመኛለሁ” — ዶ/ር ቴዎድሮስ

Written by 
Rate this item
(3 votes)

የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ዓለም አቀፉን የሴት ልጆች ቀን በማስመልከት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣ የዓለም ማህበረሰብ ለሴት ልጆች ጤና፣ ደህንነትና መብት መከበር ቁርጠኝነቱን እንዲያድስ ጥሪ አቀረቡ።

ዶክተር ቴዎድሮስ ባስተላለፉት መልዕክት፡

“እንደ አባትና እንደ አያት፣ ለገዛ ሴት ልጆቼ እና የልጅ ልጆቼ የምመኘውን መልካም ነገር ሁሉ ለእያንዳንዷ ሴት ልጅ እመኛለሁ፤ ይኸውም በጤና፣ በደህንነትና ህልሞቻቸውን በነጻነት የመከተል መብታቸው ተከብሮ እንዲያድጉ ነው።

ነገር ግን የብዙ ሚሊዮን ሴት ልጆች እውነታ ከዚህ እጅግ የተለየ ነው።

በየዓመቱ ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት ውስጥ የሚገኙ ወደ 21 ሚሊዮን የሚጠጉ ታዳጊ ሴት ልጆች ለእርግዝና ይጋለጣሉ። የፍቅር አጋር ካላቸው አራት ሴት ልጆች መካከል አንዷ የአካል ወይም የፆታዊ ጥቃት ይደርስባታል። በተጨማሪም በርካታ ሴት ልጆች በኋለኛ ዕድሜአቸው ከማህፀን በር ካንሰር ሊጠብቃቸው የሚችለውን ክትባት አሁንም አያገኙም።

እነዚህ ቁጥሮች ብቻ አይደሉም። ከእያንዳንዱ ቁጥር ጀርባ ጤናዋ፣ ምርጫዋና የወደፊት ዕጣ ፈንታዋ አደጋ ላይ የወደቀ ሴት ልጅ አለች።

የሴቶች ልጆች ቀንን ስናከብር፣ እያንዳንዷ ሴት ልጅ ጤናማ ህይወት እንድትኖርና አቅሟን ሙሉ በሙሉ እንድታወጣ እድል ለመስጠት ቃል እንግባ። ምንም አይነት ልዩነት ሳይደረግ!”

Read 7270 times