Thursday, 08 October 2026 07:00

በሀገራችን አሁን ሊቋቋም የሚገባው ቁልፍ ተቋም

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ልክ እንደ ጤና፣ ግብርና፣ ትምህርት እና ሰላም ሚኒስቴሮች ሁሉ የስፖርት ሚኒስቴር ራሱን ችሎ ሊቋቋም ይገባል! ስፖርት ለአንድ ሀገር ልክ እንደ ቱሪዝም ትልቅ ትኩረት እና ገጽታን የመገንባት ሃይል አለው።

ከዚህ ቀደም ስፖርት ኮሚሽን በመባል፣ በባህልና ቱሪዝም፣ እንዲሁም በወጣቶች ስር በአንድ ዘርፍ ተደራጅቶ ቆይቷል። ይሁን እንጂ በአዲሱ የመዋቅር እይታ ከቅንጦት ባለፈ ለሀገር የሚሰጠው ፋይዳ ከፍተኛ በመሆኑ የተለየ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።

እንደ ሀገር የምንወደውንና የምንታወቅበትን አትሌቲክስ ጨምሮ መላው ስፖርቱ በአስተዳደራዊ ተግዳሮቶች እና በንትርኮች እየተጎዳ ይገኛል። የስፖርት መሠረተ ልማቶችን ማሟላት የመንግሥት ዋነኛ ተግባር ሲሆን፣ በቁርጠኝነት የሚሰሩ ልበ ቀና ባለሙያዎችም በሀገራችን ሞልተዋል።

ስፖርት የሀገራችንን መልካም ስም ለመገንባት ቁልፍ መሣሪያ ነው። በመሆኑም በቢሊዮኖች የሚቆጠር አቅም ያለውን ይህንን ዘርፍ፣ ራሱን የቻለ ተቋም አድርጎ በዕቅድና በራእይ መምራት ጊዜ የማይሰጠው ብሔራዊ ጉዳይ ሊሆን ይገባል!

Read 366 times