በአፍሪማክስ ዘገባ መሠረት ስድስት ጊዜ ሞቶ ስድስት ጊዜ ሕይወት የዘራው ታንዛኒያዊው እስማኤል አዚዚ በማህበረሰቡ መገለል እንደደረሰበት ተናግሯል፡፡
አዚዚ እነዚህ ስድስት አደጋዎች የደረሱበት በሥራ ላይ፣ በጽኑ ወባ፣ በመኪና አደጋ፣ በእባብ ንክሻ፣ ጉድጓድ ውስጥ በመውደቅ እና በቤት ቃጠሎ ሳቢያ መሆኑን ይናገራል። ከእነዚህ ውስጥ በአንዱ አደጋ ሞቷል ተብሎ አስክሬን ማቆያ (ሬሳ ቤት) ውስጥ እንደነቃም ገልጿል።
ይሁን እንጂ በተደጋጋሚ ከሞት መነሳቱ በማህበረሰቡ ዘንድ ፍርሃት ፈጥሮባቸው ነበር፤ አንዳንዶች መናፍስት ወይም አስማተኛ ነው ብለው በማሰባቸውም ተገልሏል። ይህ አስገራሚ ታሪክ በአብዛኛው በእስማኤል አዚዚ እና በአካባቢው ሰዎች ንግግር ላይ የተመሠረተ ሲሆን፣ ስድስቱንም የሞት ማረጋገጫዎች የሚያሳዩ ይፋዊ የሕክምና መዝገቦች ግን እስካሁን አልተገኙም።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…

