የሞሮኮው ንጉስ 6ኛ መሐመድ በሳውዲ አረቢያ ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን አጥብቀው በማውገዝ፣ በሳውዲ ግዛት ላይ የሚፈጸም ማንኛውም ጥቃት በሞሮኮ ላይ እንደተፈጸመ እንደሚቆጠር ገለጹ።
ንጉሱ የሳውዲና የባህረሰላጤ አገራት ደህንነት አንድ መሆኑን በመጥቀስ፣ መካ እና መዲና ላይ የሚደረጉ ጥቃቶች ከ1.8 ቢሊዮን በላይ ሙስሊሞችን እንደሚነኩ አሳስበዋል። በተጨማሪም ቀይ ባህርና ባብ አል-መንደብ አካባቢ የሚፈጠር አለመረጋጋት ዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮችን እና የመርከብ ንግድ ወጪን ከፍ እንደሚያደርግ አስጠንቅቀዋል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas
Tuesday, 29 September 2026 08:23
«በሳውዲ ላይ የሚሰነዘር ጥቃት በኛ ላይ እንደተፈጸመ ይቆጠራል» የሞሮኮው ንጉስ
Written by Administrator
Published in
ዜና

