የረጅም ርቀት ሯጭ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ፣ መስከረም 17 ቀን 2019 በሚካሄደው የ2026 የበርሊን ማራቶን ላይ እንደሚሳተፍ የውድድሩ አዘጋጆች ይፋ አድርገዋል።
የ44 ዓመቱ አትሌት በ2026 የሚያደርገው የመጀመሪያ ይፋዊ ውድድሩ ይህ ሲሆን፤ ቀደም ሲል በ2016 እና በ2019 የበርሊን ማራቶንን አሸንፎ ማጠናቀቁ የሚታወስ ነው። በተለይም በ2019 ያስመዘገበው የ2 ሰዓት ከ01 ደቂቃ ከ41 ሰከንድ የሩጫ ሰዓት፣ የዓለምን ክብረ ወሰን በሁለት ሰከንዶች ብቻ ያጣበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነበር።
በዘንድሮው የበርሊን ማራቶን በወንዶች በኩል ከቀነኒሳ በተጨማሪ እንደ ጌታነህ ሞላ፣ ጉዬ አዶላ፣ ሹራ ቂጣታ፣ ሰለሞን ባረጋ እና ታደሰ ቶሎሳ ያሉ ጠንካራ አትሌቶች የሚወዳደሩ ይሆናል። በሴቶች ዘርፍ ደግሞ በበርሊን ጎዳናዎች ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ የምትታወቀው ትዕግስት አሰፋን ጨምሮ ህዳቱ ሂርጳ፣ ደራ ዲዳ፣ ዘይነባ ይመር እና ኬንያዊቷ ሮዝማሪ ዋንጂሩ በታላቁ ውድድር ላይ እንደሚሳተፉ ተረጋግጧል።

