Wednesday, 16 September 2026 13:00

“ታላቁ የቴክኖሎጂ ፈጠራችን ያለእኛ መፍጠር ሲጀምር ምን ይፈጠራል?”

Written by 
Rate this item
(0 votes)
በኤአይ፣ በስው ልጅና ነገን ማን ይቆጣጠራል በሚሉ ጉዳዮች ዙሪያ ደፋር ውይይት ለመፍጠር ያለመው “አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ“ የተሰኘው አዲስ መጽሐፍ የፊታችን ማክሰኞ፣ መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም ለንባብ እንደሚበቃ ተገለጸ፡፡
በኢቢኤስ ቴሌቪዥን የቴክኖሎጂ ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ በሆነው ሰሎሞን ካሳ የተዘጋጀው ይህ መጽሐፍ፤ ስለ ቴክኖሎጂ ዕድገትና የሰው ልጅ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ጥልቅ ውይይት ለመክፈት ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ጸሃፊው ጠቁሟል፡፡
ጸሃፊው ለለሞን ካሣ በ2010 ዓ.ም. “ግርምተ ሳይቴክ (The Wonder of SciTech)” የተሰኘ የሳይንስና ቴክኖሎጂ መጽሐፍ ለንባብ ማብቃቱ ይታወሳል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Read 5739 times