Wednesday, 16 September 2026 09:58

ሲንጋፖር ዜጎቿ እንዲያነቡ ክፍያ መፈፀም ጀመረች

Written by 
Rate this item
(1 Vote)
ሲንጋፖር የንባብ ባህልን ለማሳደግ እና በስልክ አጫጭር ቪዲዮዎች ምክንያት የሚመጣን የአእምሮ ድካም ለመከላከል አዲስ የአምስት ዓመት ፕሮግራም ጀምራለች። "ReadSG" በተባለው በዚህ መርሃ-ግብር ዜጎች በቀን ለ15 ደቂቃ ያነበቡትን ጊዜ በስልክ መተግበሪያ በመመዝገብ ሽልማት ያገኛሉ።
የብሔራዊ ቤተ-መጻሕፍት ቦርድኃላፊ ሜሊሳ ታም እንደተናገሩት፤ አጫጭር ጽሁፎች ፈጣን መረጃ ቢሰጡም፣ ረዘም ያሉ መጻሕፍትን ማነብ ግን የማሰብ እና የማስተዋል አቅምን ያሳድጋል። የፕሮግራሙ ዋና አላማም በጥበብ የሚያስቡ እና አስተዋይ የሆኑ ዜጎችን ማፍራት ነው።
ይህ አሰራር ንባብን እንደ ጨዋታ ለማቅረብ የተዘጋጀ ሲሆን፣ በቀን ለ15 ደቂቃ ያነበበ ሰው 20 ነጥብ ያገኛል። እነዚህ ነጥቦች ተከማችተው 1,000 ሲሞሉ ከአንድ የሲንጋፖር ዶላር ጋር እኩል ዋጋ ይኖራቸዋል።
የንባብ ተመራማሪዋ ሎህ ቺን ኢ እንደሚሉት፤ አሁን ባለው ጊዜ ብዙ ሰዎች በስልክ ስክሪን ላይ ያነባሉ፤ ነገር ግን ትኩረት ሰጥቶ በጥልቀት የማንበብ ልማድ እየቀነሰ መጥቷል። ስለዚህ በቀን 15 ደቂቃ መመደብ ጥሩ የንባብ ልማድ ለማዳበር በጣም ጥሩ መንገድ ነው።
Read 5519 times Last modified on Wednesday, 16 September 2026 10:12