በካናዳ ዓለም አቀፍ የቦክስ አሠልጣኝ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ ምርጥ ተጫዋች የሆነው መምህር ካሣሁን በቀለ፣ ከራሱ የሕይወት ልምዶች በመነሳት "ጽናት" የተሰኘውን አዲስ መጽሐፉን ሊያስመርቅ ነው። የፊታችን ቅዳሜ ጠዋት 3 ሰዓት ላይ በአራት ኪሎ ስፖርት ትምህርትና ሥልጠና ማዕከል (ወወክማ) አዳራሽ በሚካሄደው በዚህ ታላቅ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ከኤምባሲዎች እና ከስፖርቱ ዓለም የተጋበዙ የክብር እንግዶች እንደሚገኙ ይጠበቃል።
ይህ መጽሐፍ የቦክስ ስፖርትን ብቻ የሚያስተምር ሳይሆን፣ አንባቢያን ትዕግሥትን፣ ጥንካሬን፣ ተግሣጽን፣ የጊዜን አጠቃቀም እና በራስ መተማመንን የሚማሩበት የሕይወት መምህር ነው። የቦክሰኛ ጡጫ ሰውነትን እንደሚፈትን ሁሉ፣ በመጽሐፉ ውስጥ ያሉት የሕይወት ትምህርቶችም መንፈስን የሚያጠነክሩ እና ለስኬት የሚመሩ በመሆናቸው ለሁሉም አንባቢያን የማይታለፍ ልዩ እውቀት ይሰጣል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdma
Published in
ስፖርት አድማስ

