ታዋቂዋ ድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ በአዲስ አበባ ከተማ ትልቅ የሙዚቃ ኮንሰርት የማዘጋጀት ህልሟን ለማሳካት መኖሪያ ቤቷን በባንክ ማስያዟን በማህበራዊ ገጿ አስታወቀች። ላለፉት ሦስት ዓመታት በሀገር ውስጥ ኮንሰርቶችም ሆነ ክለቦች ውስጥ ሳትታይ የቆየችው ድምጻዊቷ፣ ከ20 በላይ ከሚሆኑ ፕሮሞተሮች ጋር ብታወራም የኮንሰርቱ ወጪ ከፍተኛ በመሆኑ አብረዋት ለመስራት ሳይችሉ መቅረታቸውን ገልጻለች።
በዚህም ምክንያት ህልሟን እውን ማድረግ የምትችለው ራሷ ብቻ መሆኑን በመረዳት «መጠሪያዬ ቱር» የተሰኘውን ታላቅ ኮንሰርት በራሷ ወጪ ለማዘጋጀት ወስና ቤቷን በባንክ አስይዛለች። ከአዲሱ አልበሟ ዝግጅት ጋር ተያይዞ ሀብቷ ሙሉ በሙሉ ስራ ላይ በመዋሉ ይህን ውሳኔ ማሳለፏን የገለጸች ሲሆን፣ ለዚህ ስኬትም ከቡድኗ ጋር በመሆን ከፍተኛ ዋጋ መክፈላቸውን አብራርታለች።
ይህ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚዘጋጀው ኮንሰርት ከአሜሪካና ከናይጄሪያ ከተወጣጡ ባለሙያዎች ጋር በመተባበር የሚከናወን ሲሆን፣ በህልሟ ላይ የተሳለቁትን አፍ የሚያስይዝ ስራ እንደምታቀርብም ተናግራለች። «ለህልም ዋጋ ቢከፈል አያግደውም» ያለችው ቬሮኒካ፣ ታላቁን የሙዚቃ ኮንሰርት በ2019 ዓ.ም እንደምታቀርብ ገልጻለች።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas
Tuesday, 15 September 2026 11:00
ድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ ለትልቁ ህልሟ ስትል መኖሪያ ቤቷን በባንክ ማስያዟን ገለጸች
Written by Administrator
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና

