Tuesday, 15 September 2026 10:59

አንችም እንደ ሰው ሞትሽ?

Written by 
Rate this item
(0 votes)

አቶ ልደቱ አያሌው ያስተላለፉት የሃዘን መግለጫ

ለወ/ሮ ሶፊያ ይልማ ደሬሳ

ሶፊ—፥ አንች እናቴ፣ ጓደኛዬ፣ የትግል አጋሬ፣ ከምንም በላይ የህይዎት ቤተ-መጽሐፍቴ ነበርሽ። ከአማራጭ ኃይሎች ምስረታ ጀምሮ በትግል አጋርነት የተጀመረው ወዳጂነታችን ለ32 ዓመታት ሳይቋረጥ የዘለቀ ነው። አንች የሀገር ፍቅር፣ የስልጣኔ፣ የደግነት፣ የሀቀኝነት፣ የጽናትና የመርህ ሰውነት ዓርአዬ ነበርሽ።

ለ20 ዓመታትም የፓርቲያችን የኢዴፓ ምክትል ሊቀመንበር በመሆንና በተለያዩ ኃላፊነቶች በትጋትና በታማኝነት ለሀገርሽ የታገልሽ ጽኑ ሴት ነበርሽ።

ሶፊ—-፣ ከአንች ጋር በዓይን ሳንተያይ ሞት አንዳችንን እንዳይቀድም ለአለፉት ዓመታት ስመኝ ነበር። ግን እድለኛ አልሆንኩም። መላከ-ሞት አንችን ቀድሞ ወሰደ። ልቤም በሀዘን ተሰበረ። ምን ማለት እችላለሁ? አንች ልዩና በልዩ ሁኔታ መወሳት የሚገባሽ ሰው ብትሆኝም የተለመደውን ብዬ ልሰናበትሽ።

ሶፊ—፣ ነብስሽን ፈጣሪ ይማር። እራሴው ሀዘንተኛሽ ብሆንም ለልጆችሽ እና ለዘመድ አዝማዶችሽ በሙሉ መጽናናትን እመኛለሁ።

ልደቱ አያሌው።
መስከረም 4 ቀን 2019 ዓ.ም
ከሰሜን አሜሪካ

የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas

Read 8281 times