Tuesday, 01 September 2026 13:24

አዲሱ የዓለም ሥርዓት፡ ደራሲው ዓለም በአንድ ንጉሥ እንድትመራ ጥሪ አቀረቡ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በደራሲ ንጉሥ ታደለ ድሪባ የተዘጋጀው እና 340 ገጾችን የያዘው “አዲሱ የዓለም ሥርዓት” (New World Order) የተሰኘ መጽሐፍ በቡራዩ ኩሪፍቱ ሪዞርት በይፋ ተመረቀ። መጽሐፉ ዓለም በአንድ የገንዘብ ሥርዓት፣ በአንድ ንጉሥ እና በአንድ የአመራር እዝ ስር ስትመራ የበለጠ ፍትሃዊነትና እኩልነት ይሰፍናል የሚል አከራካሪ እናለየት ያለ ሃሳብ ያነሳ ሲሆን፣ ደራሲው ለዚህ አዲስ ሥርዓት ራሳቸውን እንደ ዋነኛ እጩ አቅርበዋል።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የሀገራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰርፀፍሬ ስብሀት እና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጡት ዶክተር ገዛኸኝ ፀጋው፣ መጽሐፉ የምርምር አስተሳሰብን ለማሳደግ እና በአለም አቀፍ ደረጃ ሊወያዩበት የሚችሉ አዳዲስ ሀሳቦችን ለማፍራት ትልቅ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

ይህ በአማርኛ፣ በኦሮምኛ እና በእንግሊዝኛ ተዘጋጅቶ ከሀገር አልፎ ለዓለም አቀፍ አንባቢያን እንዲደርስ ወደ 13 ተጨማሪ ቋንቋዎች የተተረጎመው መጽሐፍ የምረቃ መርሐ-ግብር ታዋቂ አርቲስቶች፣ ምሁራን እና የፈጠራ ባለሙያዎች በተገኙበት በድምቀት ተካሂዷል።

የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas

Read 5293 times