Friday, 28 August 2026 17:08

በእስራኤል የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጥገኝነት ጠያቂዎች ላይ የመባረር ስጋት ተደቅኖባቸዋል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ለሁለት አሥርት ዓመታት ያህል በእስራኤል ያለ ቋሚ ሕጋዊ ፈቃድ ሲኖሩ የቆዩ ኢትዮጵያውያን ጥገኝነት ጠያቂዎች፣ ሀገሪቱ በምትወስደው አዲስ የሕግ እርምጃ ምክንያት ከባድ የመባረር ስጋት ገጥሟቸዋል። እንደ አቶ እንዳልካቸው የማኔ እና ዮርዳኖስ ያሉ ስደተኞች ከባድ በደሎችን አልፈው እስራኤል ገብተው ሕይወት መስርተው  ልጆቻችውን  እያስተማሩ ቢሆንም፣ ባለፈው ታኅሣሥ ወር የእስራኤል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቡድን ከለላ ፈቃድ እንዲሰረዝ መወሰኑ ሕልማቸውን አደጋ ላይ ጥሎታል።
 
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው፣ እስራኤል የጥገኝነት ማጽደቅ ምጣኔዋ 0.1 በመቶ ብቻ መሆኑ ስጋቱን  አባብሶታል። ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት የወሰደው 'HIAS Israel' የተሰኘው ድርጅት፣ እስራኤል ዓለም አቀፍ የከለላ ስምምነቶችን አክብራ ስደተኞችን  አደጋ ወደ ሚጠብቃቸው ሀገር እንዳትመልስ  በቴል አቪቭ የዞን ፍርድ ቤት ክስ መመስረቱን ሃራምቤ ሬዲዮ ዘግቧል፡፡

Read 5473 times