የአትላንቲክ የባርነት ንግድ ሰለባ የሆኑትን አፍሪካውያን አባቶችና እናቶች ለማስታወስ የተሰራው "የአንሴስተር ፕሮጀክት" በጋናዊው ቀራጭ ኳሜ አኮቶ-ባምፎ የተዘጋጀ ሕያው የጥበብ ሥራ ነው። "ንኪይንኪይም" የሚለው ስያሜ የተወሰደው "የሕይወት ጉዞ ጠማማ ነው" ከሚል ምሳሌ ሲሆን፣ ሰዎቹ የተገደዱበትን መራራና አስቸጋሪ የሕይወት ጎዳና ያንጸባርቃል።
እያንዳንዳቸው በእጅ የተቀረጹትና የተለያዩ ስሜቶችን የሚያሳዩት እነዚህ ቅርጻ ቅርጾች፣ ባርነት ከመፈጸሙ በፊት የነበረውን ቅጽበት ያስታውሳሉ።
ይህ ታላቅ መታሰቢያ በጋና በሚገኘው የንኪይንኪይም ሙዚየም እና በአሜሪካ አላባማ በሚገኘው የሰላም እና የፍትህ ብሔራዊ መታሰቢያ ውስጥ ይገኛል። ቅርጻ ቅርጾቹ ያለፈውን ታሪክ ከመዘከር ባለፈ፣ የጠፋውን ማንነታችንን መልሰን የማግኘት ተስፋን የሚሰጡ ትልቅ ታሪካዊ እሴት አላቸው።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ህብረተሰብ

