Wednesday, 05 August 2026 09:22
በካናዳ ቫንኩቨር የሚኖረው ኢትዮጵያዊ-ካናዳዊ አርቲስት ያሬድ ንጉሱ፤ የካናዳ የስፖርት አፈ ታሪክ የሆነውን ሃሪ ጄሮምን የሚዘክር "Mighty Jerome" የተሰኘ ግዙፍ የሥነ-ጥበብ ሥራ በሰሜን ቫንኩቨር አዲሱ የህብረተሰብ ማዕከል መግቢያ ላይ በቋሚነት አስመረቀ።
ከዚህ ቀደም የቫንኩቨር የሆኪ ቡድን ማልያን በግዕዝ ቁጥሮች በማስዋብ ታዋቂነትን ያተረፈው ያሬድ፣ ይህ አዲስ የህዝብ ጥበብ ፕሮጀክት መመረጡ በካናዳ ያለውን ከፍተኛ ሙያዊ ክብር እና ተዓማኒነት በድጋሚ አሳይቷል።
በ1964 የቶኪዮ ኦሎምፒክ የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊውንና ከከባድ ጉዳት በጽናት ተመልሶ ለወጣቶች ልማት የሠራውን ሃሪ ጄሮምን የሚዘክረው ይህ ሥራ፤ ለኢትዮጵያውያን ካናዳውያን ትልቅ የኩራት ምንጭ ነው። በሺዎች የሚቆጠሩ ጎብኚዎች በሚጎበኙበት ማዕከል ላይ የሚቀመጠው ይህ ሥራ፣ በካናዳ የብዝሃነት፣ የእኩልነት እና የባህል ተሳትፎ ዋጋን በግልጽ የሚያሳይ ታላቅ ምልክት ሆኗል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ዜና

