የቤተ ክርስቲያን ሚዲያዎች 'ይሻሻላሉ፣ ገና ጅምር ላይ ናቸው፣ ብዬ በተስፈኝነት ጠበቅሁ። እኔን ብሎ ተስፈኛ! እነርሱ ግን እያደር የጳጳሳት_ዲያሪ ሆነው ቁጭ!
"ብፁዕነታቸው መሠረት ጣሉ፣ ጎበኙ፣ ከፈቱ፣ ተጓዙ...።" non sense! የሚዲያ ይዘት እንዲህም ይሞታል እንዴ?! ኃፍረት ወዝንጓጔ ማለት ለእናንተ! እያደር ማዘቅዘቅ! እንደ ተዘዋዋሪ ሰባኪ በየንግሡ ለአበል ሩጫ ብቻ! ያሳዝናል! ሚዲያችን contentwise ክፉኛ፣ ያውም ፀዋግ ሞት እየሞተ ነው።
ኅሡ ርእሰክሙ አኃው።
ቤተ ክህነቱን እንደ መደብ ጀርባው እንደሚቆጥር ደብተራ ባላችሁ ይዘትም ሆነ አቀራረብ ኃዘንም ኃፍረትም ይሰማኛል።
የላዕላይ መዋቅሩ የዕለት ተዕለት ውሎ ዘጋቢ ሆናችሁ እየቀራችሁ ነው። ሁሌ "የሙከራ ስርጭት" ላይ ያላችሁ መስላችሁ መታየት ደስ አይልም። አዘጋገባችሁ ቤተ ክርሰቲያን ማለት "ጳጳሳት/መምሪያዎች ብቻ" ያስመስላል።
ባካችሁ ይዘት ላይ ሥሩ፣ የካህኑና የምዕመኑ እንዲሁም የአጥቢያዎች ድምፅ ለመሆንም ሞክሩ። የይዘት ሳይሆን የአደባባይ ተርእዮ መድረክ እየሆናችሁ ነው።
በአማን ነጸረ
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…

