በኢትዮጵያ ስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ ብቻ የሚገኘውና የዩኔስኮ የዓለም ቅርስ መለያ የሆነው ብርቅዬው ዋልያ፣ በቅርብ ዓመታት በነበረው ግጭትና የሕግ መላላት ምክንያት ቁጥሩ ከ638 ወደ 306 ዝቅ ብሏል። በዚህም ሳቢያ አካባቢው ለሕገ-ወጥ አደን በመጋለጡ፣ ዓለም አቀፍ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ኅብረት (IUCN) ዋልያን «ከፍተኛ የመጥፋት አደጋ የተደቀነበት» ሲል በአደጋ መዝገቡ ውስጥ አካትቶታል። ሆኖም ይህ ምዝገባ ለእንስሳው ዓለም አቀፍ ትኩረት፣ ምርምርና የገንዘብ ድጋፍ ለማሰባሰብ ትልቅ ዕድል የሚፈጥር በመሆኑ እንደ መልካም አጋጣሚ ተወስዷል።
ችግሩን ዘላቂ በሆነ መንገድ ለመፍታት የኢትዮጵያ የዱር እንሰሳት ጥበቃ ባለሥልጣንና የፓርኩ ጽሕፈት ቤት የ10 ዓመት ስትራቴጂ በማዘጋጀት ወደ ሥራ ገብተዋል። በዚሁ መሠረት «የዋልያ አምባሳደሮች» የተሰኙ 12 ባለሙያዎችን በማሰማራት፣ ከኅብረተሰቡ ጋር በመተባበር ሌት ተቀን ቅኝት በማድረግ ሕገ-ወጥ አደንን ሙሉ በሙሉ ማስቆም ተችሏል። ቀደም ሲልም በ1983 ዓ.ም በተደረገ ጥበቃ እንስሳቱን ከአደጋ ቀጠና ማውጣት የተቻለ ሲሆን፣ አሁንም በአንዳንድ አካባቢዎች እስከ 15 የሚደርሱ አዳዲስ ግልገሎች መታየታቸው የዋልያ ቁጥር በፍጥነት እንደሚያገግም ትልቅ ተስፋ ፈጥሯል።
AMECO-
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…

