ከ35 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን የቀድሞ (የኢ.ሕ.ድ.ሪ) ፕሬዝዳንት የኢትዮጵያ ህዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑሊክ፣ (የኢ.ሠ.ፓ) የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ ዋና ፀሐፊ የነበሩት ጓድ መንግስቱ ሃይለማርያም (ሌ/ኮ) ከአገር ወጥተው ወደ ሃገረ ዙምባቡዌ የሄዱበት ዕለት ነው።
ግንቦት 10 ቀን 1983 ዓ.ም ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማሪያም በመኖሪያ ቤታቸው ለከፍተኛ ባለስልጣኖቻቸው የእራት ግብዣ አደረጉ ፤ ግብዣው ሲጠናቀቅ ፕሬዘዳንቱ ከዚህ በፊት ባልተለመደ መልኩ ሁሉንም ተጋባዥ እንግዶች እበራፋቸው ላይ በመሆን አንድ ባንድ እየጨበጡ ሸኙዋቸው።
ግንቦት 12 ቀን 1983 ዓ.ም ፤ ፕሬዝዳንት መንግስቱ መሉውን ቀን የተለያዩ ወረቀቶችን እቢሯቸው ውስጥ ሲቀዳድዱ ዋሉ ፤ ማምሻው ላይ ግን ወደ ዘመቻ መምሪያ በማምራት ለከፍተኛ የጦር አዛዦቻቸው ንግግር አደረጉ።
ማክሰኛ ግንቦት 13 የፕሬዝዳንቱ ልዩ ረዳት ሻምበል መንግስቱ ፤ ብላቴ ማሰልጠኛ ጣቢያ ደርሶ ከዚያም ወደ አስመራ ደርሶ መልስ የሚበቃ ነዳጅ የሞላ አንድ ዳሽ 5 አውሮፕላን እንዲዘጋጅ ትእዛዝ አስተላለፉ።
በዛሬው እለት ከጠዋቱ ወደ 2:00 ገደማ ፕሬዝዳንቱ ከተመረጡ አጃቢዋች እንደዚሁም ከ3ኛው ክፍለጦር የመጣና የቅርብ አጃቢያቸው ከነበረው ከሻንበል ደመቀ ባንጃው ጋር በመሆን በኮሎኔል ተስፋዬ መሪነት ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በመድረስ ተዘጋጅታ ትጠብቅ ከነበረችው አውሮፕላን ተሳፈሩ።
ታሪክን_ወደኋላ
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…

