"ትናንት ከሸገር ተነስቼ ፍራንክፈርት እንዳረፍኩ የጀርመን ድንበር ጠባቂ የት እየሄድኩ አንደሆነ ጠየቀኝ፤ አገሩን ትቸለት ወደ ስፔን ባርሴሎና እያቀናሁ እንደሆነ ነገርኩት፤ ምክንያቱን ሲጠይቀኝ የግጥም ፌስቲቫል ላይ ልሳተፍ እንደሆነ አ(ስ)ረዳሁት፤
ለፌስቲቫሉ መግቢያ የቆረጥከውን ትኬት አሳየኝ ብሎ ገገመ፤
ካቅራቢዎች አንዱ ነኝ አልሁና የተጋበዝኩበትን ደብዳቤውን አሳየሁት፤
ያኔ ፖሊሱ ፊት ላይ የተሳለውን ስሜት ፤ የመገረም ይሁን የመናደድ የመጠራጠር ይሁን የማፈር ለመለየት ጊዜ አልነበረኝም፤ ያው ብዙ ፈረንጆች፣ ችግር እንደሚያጋጥመን እንጂ ስለችግር አንደምንገጥም አያውቁም
ለማንኛውም እንደሰማችሁት ሆነ እንዳልሰማችሁት በዘንድሮው ፌስቲቫል ላይ ስራቸውን እንዲያቀርቡ ከተጋበዙ ከተለያዩ አለም ክፍሎች ከተጋበዙ ሰባት ገጣሚያን አንዱ አኔ ወንድማችሁ ነኝ፤
ትውልደ ኢትዮጵያዊ ባርሳዎች በነገው ዝግጀት ላይ መታደም ከወደዳችሁ ኮመንት መስጫ ላይ አድራሻውንና ጊዜውን አስቀምጥላችሁዋለሁ፤"
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…

