ጃኪ ቻን በዓለም ዙሪያ በሚያስደንቁ የአክሽን ፊልሞቹ የሚታወቅ ቢሆንም፣ ጥቂት የማይባሉ ሰዎች ግን አንጋፋ ድምፃዊ መሆኑን አያውቁም! ጃኪ የሙዚቃ ሥራዎችን በይፋ መቅረጽ የጀመረው በ1980ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ ለራሱ ፊልሞች መግቢያና መውጫ የሚሆኑ ዜማዎችን በማንጎራጎር ነበር።
በሂደትም የሙዚቃ ጉዞውን በማስፋት እስከ 20 የሚደርሱ የሙዚቃ አልበሞችን ለገበያ ያበቃ ሲሆን፣ ካንቶኒዝ፣ ማንዳሪን፣ ጃፓንኛ፣ ታይዋንኛና እንግሊዝኛን ጨምሮ በአምስት የተለያዩ ቋንቋዎች አቀንቅኗል። ሌላው ቀርቶ በ1984 ዓ.ም በጃፓን ሀገር የ"ምርጥ የውጭ ሀገር ድምፃዊ" ሽልማትን ጭምር መጎናጸፍ ችሏል።
የጃኪ ቻን የሙዚቃ እና የፊልም ሕይወት አንዱ ከአንዱ ሳይቀድም ጎን ለጎን አብረው የዘለቁ ስኬቶቹ ናቸው። በእርግጥም እሱ ተዋናይ፣ ስታንትማን (አደገኛ ትዕይንቶችን የሚሠራ)፣ ዳይሬክተር እና የፖፕ ኮከብን በአንድ አካል የያዘ አስደናቂ የተሰጥኦ ማዕከል ነው!
Eastlyn Hub-

