Print this page
Saturday, 27 August 2011 13:06

መዝናናት መዝናናት፣ አሁንም መዝናናት.. ጓድ ሌኒን

Written by  ስብሃት ገ/ እግዚያብሔር.
Rate this item
(0 votes)

FASUT
አሀዱ ርዕስ
Chemistry የሚባለው ሳይንስ Alchemy ከተባለ የጥንት ..ሳይንስ ብጤ.. ከሆነ የእውቀት ዘርፍ የተገኘ ነው፡፡
Doctor Faust በዘመናቸው የአልኬሚስቶች ቁንጮ ነበሩ፡፡ ቤታቸው ሁለት ክፍል ብቻ ነው፡፡ ላቦራቶሪያቸው ውስጥ በሥራ ተጠምደው ይውላሉ፣ መኝታ ቤታቸው ውስጥ ያድራሉ፡፡
በቀን አንድ ጊዜ ብቻ ከቤት ይወጣሉ፡፡ ወደ አመሻሽ ላይ በእግራቸው ለመዘዋወር፣ ደማቸውን ለማፍታታት እና ወዲያውም ፀሐይ ስትጠልቅ እያዩ በፈጣሪ ሥራ ለመደነቅ፡፡ ከወጣትነታቸው አንስቶ እስከ ሰማንያ ዓመታቸው እለታዊ ውሏቸው የተለያዩ Chemicals እያቀያየጡ፣ አንዳንድ ድግምትም እየጨመሩበት ሁለት ውጤቶች ለማግኘት መጣጣር ነበር፡፡

ውጤት አንድ ፈሳሽ ነው፡፡ እውስጡ ምንም ነገር ቢነክሩ (ለምሳሌ ሳር፣ ጠጠር፣ ጭራሮ ወይም አበባ) ወርቅ ሆኖ ይወጣል፡፡
ውጤት ሁለትም ፈሳሽ ነው፡፡ እሱን የጠጣ ሰው (ሽማግሌ እንኳ ቢሆን) ወጣት ይሆናል፣ በወጣትነት ለዘለዓለም ይኖራል፡፡ ዶክተር ፎስት በፍለጋቸው ቅድሚያ የሚሰጡት ይሄኛው ነበር፡፡
ለማንኛውም አንዱም ሳይሳካላቸው ሰማንያ ዓመት አለፋቸው፡፡ በከንቱ ባከነ ያ ሁሉ ጥረት፡፡ ጥቂት የሰው ልጅ ደስታ እንኳ ሳይቀምሱበት! ዋ!!
አንድ አመሻሽ ላይ ከሽርሽራቸው በሀሳብ እየተንሳፈፉ ሲመለሱ፣ አንድ ትንሽ ጥቁር ውሻ ፊታቸው ሱክ ሱክ እያለ ሲሄድ አዩ፡፡ ቀድሟቸው ወደ ላብራቶሪያቸው ገባ፡፡ ገብተው በሩን ዘግተው ወደ ውሻው ቢዞሩ፣ ውሻው የለም! በቦታው አንድ ቁመናውም መልኩም የዘለዓለም ወጣትነት የተገለለት አልኬሚስት የመሰለ ሰው ቆሟል፡፡
..እንደምን አመሹ ዶክተር.. አላቸው፣ ሙዚቃ ያለው በሚመስል ድምጽ “Mephistopheles እባላለሁ.. አላቸው ..በገሀነብ የሥልጣን ተዋረድ ከሳጥናኤል ቀጥሎ አራተኛው ሹም እኔ ነኝ፡፡ እዚህ የመጣሁት ለኔም ለርስዎም ስለሚበጅ ጉዳይ እንድንወያይ አስቤ ነው፡፡ ወምበርዎ ላይ ይቀመጡ.. (በድንጋጤ ፈዝዘው ቆመው ቆይተዋል)
..እቺን እዚህ ላቦራቶሪ ውስጥ ተኰራምተው ያባከኑዋትን ህይወት መልሼ ብሰጥዎትና የሃያ ዓመት ወጣት ሆነው እንደገና መኖር ቢችሉ ምን ይመስልዎታል?..
..ገነት የገባሁ ይመስለኛል..
..ገነት መግባት ይከፈልበታል..
..እከፍላለሁ..
..ሰማንያ ዓመት እስኪሞላዎት ድረስ እኔና እርስዎ አለማችንን እንቀጫለን፡፡ ከዚያ በኋላ፣ በሰማንያ ዓመትዎ ሲሞቱ ነብስዎትን ለኔ ይስጡኝና፣ ወስጄ ለሳጥናኤል ሳስረክባት የማእረግ እድገት ይሰጠኛል፡፡ የዶክተር ፎስት ነብስ ዋጋዋ ከመቶ ተራ ነብስ ይበልጣል፡፡ ይስማማሉ?..
..ሌላ የምትነግረኝ አለ?..
..በምናደርገው ሁሉ፣ ሃጢአት እንዲሠሩና እንዲኰነኑ ለማድረግ በትጋት እፈታተንዎታለሁ፡፡ ከቻልኩ እሰየው እላለሁ፡፡ ካቃተኝ ግን፣ ማለት እርስዎ ሃጢአቱን ካልሠሩ፣ አሸነፉኝ፣ ወደ መንግስተ ሰማያትዎ ገቡ ማለት ይሆናል፡፡ ይዋጣልን?..
..ይሁን..
..ነገር ግን (ይቅርታ ያድርጉልኝና) የሰው ዘር ሲባል ከሃዲ በመሆኑ፣ ስምምነታችንን በጽሑፍ እናስፍርና፣ እርስዎ በቀለም ሳይሆን በደምዎ ይፈርማሉ ውላችን ላይ..
ዶክተሩ ፈረሙ፡፡ እዚያው በዚያው የሃያ ዓመት ጎረምሳ ሆኑ!
ክልኤቱ
Gretchen እጅግ የተዋበች ጨዋ የአስራ ሰባት ዓመት ብላቴና ናት፡፡ ትምህርቷን ስትጨርስ መነኩሲት ለመሆን እቅድ አላት፡፡ ሰፈሩ በሙሉ ይወዳታል፡፡ ወላጆቿ ሞተዋል፡፡ አንደኛ ፎቅ ላይ የተከራየችውን አንድ ክፍል ታላቅ ወንድምዋ Christian ይከፍልላታል፡፡
ፎስትና ሜፊስቶፊሊስ ወደ ቤተ ክርስቲያን እየሄዱ ለግሬቸን እየታዩዋት፣ በአምስተኛው ጊዜ ተዋወቋትና ቤቷ ድረስ ሸኟት፡፡ የጊዜው fashion ስለሆነ ሁለቱም ሰይፍ ታጥቀው አምሮባቸዋል፡፡ ለሦስተኛ ጊዜ ቤቷ ሲያደርሷት ቤቷ ገብተው ጥቂት አጫውተዋት ተሰናበቷት፡፡
ይህን ሁሉ ጊዜ ሜፊስቶ ለሁለቱም ልዩ ልዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ይነግራቸው ነበር፡፡ ከሁሉ አሳምሮ የተረከላቸውና በኋላም በረዥሙ የተወያዩበት የንጉስ ዳዊትን፣ የታማኝ ጄኔራሉን የኦርዮንን እና የሚስቱ የቤርሳቤህን ግንኙነት ነበር፡፡
የጄኔራሉን መኖሪያና የዳዊትን ቤተ መንግሥት አንድ ካብ ይለያቸዋል፡፡ አንድ ቀን ቤርሳቤህ ቤቷ በር አጠገብ በፀሐዩ ገላዋን ስትታጠብ፣ እንዳጋጣሚ ንጉሡ ብቻውን ሰገነቱ ላይ ቆሞ ስለነበር ቁልቁል ታየችው፡፡ እንደሷ የተዋበች ሴት አይቶ አያውቅም፡፡ በምስጢር ልኮ አስመጣት፣ አብረው አደሩ፡፡ ..ሆን ብዬ ነው ሰገነትህ ብቻህን የምትሆንበትን ሰዓት ጠብቄ ገላዬን የታጠብኩት፡፡ ገና እረኛ እያለ ጐልያድን ያህል ጭራቅ የገደለ ጀግና እንዲያየኝ ፈልጌ.. አለችው፡፡
ባሏ ጦር ሜዳ ዘምቷል፡፡ ሁልጊዜ አብረው እያደሩ፣ የያዛቸው ፍቅር እየባሰበት ሄደ፡፡ አንድ ቀን ነብሰ ጡር ነኝ አለችው፡፡
ዳዊት ለሠራዊቱ ጠቅላይ አዛዥ ደብዳቤ ላከለት ..ስለ ጦር ግምባር ሁኔታ ጽፈህ በጄኔራል ኦርዮን እጅ ላክልኝ.. አለው፡፡
ኦርዮን ደብዳቤውን አምጥቶ ስለጦርነቱ በቂ ከተነጋገሩ በኋላ ዳዊት ..በል አላቆይህ፣ ባልተቤትህ ሳትናፍቅህ አትቀርም.. ሲለው
..ምንም ያህል ብትናፍቀኝ፣ ንጉሥ ሆይ፣ የጦር ጓዶቼ አደጋ ውስጥ እያደሩ እኔ ከሚስቴ ጋር አላድርም፡፡ ቤትም ብቅ አልልም..
ችግር ሆነ፡፡ ምን ማድረግ እንዳለበት ሲያወጣ ሲያወርድ፣ ንጉሡ የፍቅረኛው ናፍቆት እያንቆራጠጠው፣ ሰገነቱ ላይ እየቆመ ወይ እየተንጐራደደ፣ ሰዓታቱ እንደ ቀናት ረዘሙበት ሲጐተቱ፡፡ እሷ ስትታጠብ ወዳየበት ቦታ ረዥም ጊዜ አትኩሮ ተመለከተ፣ ሌሊቶቹን እያስታወሰ፡፡
በነጋታው ዳዊት ለሠራዊቱ ጠቅላይ አዛዥ ደብዳቤ ጻፈለት፡፡ እንዲህ የሚል ትእዛዝ አለበት ..ለውጊያ ስትሰለፉ ጄኔራል ኦርዮንን ግምባር ቀደም አድርገው፡፡ ውጊያው ጥቂት እንደተካሄደ፣ ኦርዮንን ትታችሁት አፈግፍጉ..
ኦርዮን ተሰናብቶ ደብዳቤውን ይዞ ሄደ፣ በጀግንነት ሲዋጋ ወደቀ፡፡
ቤርሳቤህ ለባሏ ሀዘን ላይ የምታሳልፈው ጊዜ ስርዓቱ እንደሚያዝዘው ካለፈ በኋላ የንጉሱ ህጋዊ ሚስት ሆነች፡፡ ወንድ ልጅ ወለደችለት፡፡
ገና ዓመት እንኳ ሳይሆነው ልጁ ታመመ፡፡ በሽታው ሲፀናበት ጊዜ አባት ማቅ ለበሰ፣ ሱባኤ ገባ ለልጁ ህይወት ሊፀልይ፡፡
ልጁ ግን ጥቂት ቀን ብቻ ቆይቶ ሞተ፡፡ ዳዊት በኔ ኃጢአት ነው ልጄ የሞተው ብሎ ከልቡ ተተ፡፡ እግዚአብሔር መሀሪ ነው፣ ጊዜውን ጠብቆ ..ለሁሉ ጊዜ አለው.. የሚለው ልጃቸው ተወለደ. . .
. . .ሜፊስቶ ከመጽሐፍ ቅዱስ እየቀነጨበ ታሪክ በነገራቸው ቁጥር፣ ማሳረጊያው ..እግዚአብሔር ከቁጣው ምህረቱ ሰባት እጥፍ ይበልጣል.. ነበር፡፡ ለአሁኑ ደግሞ ..ጠቢቡ ሰሎሞን ከተራው ወንድ ልጅ ሰባት ጊዜ ብቻ አይደለም፣ ሰባ ጊዜ ሰባት እጥፍ ይልቃል.. ሲል አከለበት ..ስለ ቁጣው በሃጢአት የተፀነሰ ልጃቸውን ገደለባቸው፣ ስለ ምህረቱ ሲክሳቸው ሰለሞንን ሰጣቸው..
ግሬቸንን ተሰናብተዋት ወደ ቤታቸው ሲሄዱ፣ እየሳቀ የራሱን ብልጠት ካደነቀ በኋላ ፎስትን ..ጊዜው ሲደርስ ሰሎሞናዊ እርምጃ ትወስድባት ዘንድ መንገዱን እያስተካከለኩልህ እንደሆነ አስተውለሃል? ዘዴው ረቂቅ ነው፡፡ መንፈሳዊ ነው ኧረ!..
እንደተባለው ጊዜው ሲደርስ አዲሱ ፎስት ድንግሉን ለድንግሊቱ ግሬቸን አስረከበ፡፡ ..እንኳን ደስ አለህ!.. አለ ሜፊስቶ ..እኔም እንኳን ደስ ያለኝ! የመጀመሪያውን ሀጢአት አሠራሁህ..
..እኔ ሀጢአት አልለውም፡፡ መኖር ነው..
..እኔም የሀጢአት እርምጃ አልለውም፡፡ ግን አሪፍ ዳዴ ነው! ሳይታወቅህ በሰፊው የሃጢአት ጐዳና አንድ እርምጃ አይተሃል፡፡ ሀጢአት ምን ያህል እንደሚጥም ቀምሰሃል፡፡ ጣመኝ ድገመኝ ደጋግመኝ ሲል ገና አሳይሃለሁ፡፡ ገና ስንዋዋል እንደነገርኩህ ነው፡፡ እያወቅህ ሀጢአት ማጥ ውስጥ ትዘፈቅ ዘንድ ነው ጥረቴ፣ አታልዬ ሀጢአት ባሠራህ አይቆጠርልኝም በኔ ቤት፡፡ ከዚህ የሚቀጥለው እርምጃችን በሰፊው ጐዳና ወንጀል መፈም ነው..
..ተወው አትልፋ፣ ወዳጄ፡፡ ፎስት ወንጀል ይፈጽማል ማለት ዘበት ነው!..
..እስቲ እናያለን..
ማንኛውም ሰፈር ቢያንስ አንድ አሳባቂ አያጣም፡፡ የግሬቸን ሰፈር አሳባቂ ሄዶ ለወንድሟ ነገረባት፡፡
ፎስትና ሜፊስቶ ግሬቸንን አድርሰዋት ቤቷ ሲገቡ፣ ሩብ ሰዓት ያህል ቆይቶ ክርስቲያን ገባ፡፡ ሰላም እንኳ ሳይላቸው ..እዚህ ምን ትሠራላችሁ?.. አምባረቀ
..ምን የምንሠራ ይመስልሃል?.. ጠየቀ ሜፊስቶ እየገላመጠው
..አንተ እነዚህን እያቃጠርካቸው ይመስለኛል..
..አንተ ደሞ ካቃጣሪም የባስክ ነህ፡፡ እንዳልነግርህ እቺ ንጽህት እህትህ ፊት ሆነብኝ እንጂ፡፡..
..ከአፈ ጮሌ አቃጣሪ ጋር አፍ አልካፈትም.. አለውና ወደ ፎስት ዞሮ ..አንተ አሳዳጊ የበደለህ ስድ! የተከበረ ቤተ-ሰብ ስም በማጉደልህ ሞት ተፈርዶብሃል፡፡ መክት!.. ብሎት ሰይፉን መዘዘ፡፡
ከአልኬሚ ቅመማ ሌላ ምንም የማያውቀው ፎስት፣ ግሬቸን ፊት ስለሆነበት ሰይፉን ለመምዘዝ ወኔው አስገደደው፡፡
ሜፊስቶም ተከትሎት ሰይፉን መዘዘ፡፡ ለራሱም ለፎስትም እየተከላከለ ክርስቲያንን አጋለጠለት፡፡ ፎስት ከፍርሃት በተገኘ የአልሞት ባይ ተጋዳይ ድፍረት ዘለለ፣ ሰይፉን አንጀቱ ውስጥ ሰካበት፡፡
ፎስት አእምሮው በድንጋጤ ስለደነዘዘ ግሬቸንን ሳያናግሯት ወጡ፡፡
ሜፊስቶ ሁለት ምርጥ ፈረስ ገዛ፣ እንዲሁም ኮርቻ፡፡ ወደ ሌላ ከተማ ሄዱ፡፡ እዚያ ሁለት ቀን አርፈው ወደ ሌላ ከተማ ሄዱ፡፡
ሰለስቱ
በሰፊው የህይወት ጐዳና ስድሳ ዓመት አብረው ሲጓዙ ፎስት በሜፊስቶ መሪነት ከምድራዊው የአኗኗር ምስጢር ጋር ተዋወቀ፣ ተለማመደ፣ በአንዳንድ ሱስም ተጠመደ፡፡ እድሜው እየገፋ ሲሄድ ከእርጅናም ጋር ተዋወቀ፣ እንደ ቀድሞው ጐታታ፣ ቀጥቃጣ፣ ጐባጣ፣ ሽበታም፣ ረሲታ ሽማግሌ ሆነ፡፡
የፈመው ግድያ በቂ ቢሆንም፣ እርግጠኛ ለመሆን፣ እሱ ፎስትን እያገዘው ሁለት ተጨማሪ ግድያ አስፈመው፡፡
ፎስት ወሜፊስቶ በበኩሉ ተልእኮውን ችላ አላለም፡፡ ፎስትን ወደ ሲኦል ለማድረስ በግሬቸን ላይ የፈመው ዝሙትና በወንድሟ ላይ ደ ዳግማዊ ህይወቱ መጨረሻ ላይ ሲያስታውሰው እንደ ህልም እየመሰለው ሄደ፡፡ ደግሞስ እነዚያ ስድሳ ዓመታት እንዴት ፈጥነው አለፉ!? ሃይለኛ ነፋስ እንደሚነዳው ዳመና እየተንሳፈፉ እየጠፉ ሄዱ፡፡
እንግዲህ የቀረው ከሜፊስቶፊሊስ ጋር መፋጠጥ ሆነ. . ይሄ ሁሉ ሲሆን፣ ግሬቸን ሰይጣን አሳስቷት በሠራችው ድርብ ኃጢአት ከልቧ ተተች፡፡ ዓለም በቃኝ ብላ መነኰሰች፡፡ ለክሪስቲያንና ለፎስት ነብስ ስትፆም ስትልይ፣ ሻማ ስታበራ ኖረች፡፡ ከቁጣው ምህረቱ የሚበልጠው አምላክ ሎቷን ሰማ፡፡
አርባእቱ
ፎስት ሊሞት ሲያጣጥር፣ ሜፊስቶፊሊስ በደም የተፈረመውን የነብስ ሽያጭ ውል አወጣ፡፡ የመንግሥተ ሰማያት መልእክትና የገሀነም ሰይጣናት ሊሻሙዋት መጡ፡፡
እነዚህ በቀኝ እጇ፣ እነዚያ በግራ እጇ ይዘዋት ሲጓተቱ፣ ሲጓተቱ፣ ሲጓተቱ እመ ብርሃን ብቅ አለች፡፡ ሲያዩዋት መላእክቱ ተበረታቱ፡፡ ሰይጣናቱ ተዳከሙ፡፡ መላእክቱ የምስጋና ዝማሬ እያዜሙ ወደ መንግስተ ሰማያት አጀቡዋት፡፡
ሰይጣናቱም በፀጥታ ሜፊስቶፊሊስን ወደ ገሀነም አጀቡት. . .
[Faust  በጀርመኑ ታላቅ ባለቅኔ (Johann Wolfgang Goete) በግጥም የተደረሰ ረዥም ሥራ ነው፡፡
እንደ ልቦለድም እንደ ትያትርም ቢነበብ እኩል አአምሮን ያስደንቃል፣ ነብስን ያረካል፡፡ ..ፎስት.. አርቲስቱ ገተ በእድሜ ከበሰለ በኋላ የደረሰው ነው፡፡ አርቲስቱ በጐልማሳነቱ The Sorrows of Werther የተባለ ፈር-ቀዳጅ ልቦለድ አሳትሞ Romanticism የሚባለውን የስነ-ጽሑፍ ዘርፍ (literary genre) msrt]
አምስቱ
በጓድ ሊቀመንበር ዘመነ መንግሥት ቁስ አካል እንጂ እግዚአብሔር የሚሉት ነገር የለም ይሉ ነበር አብዮታውያን ጓዶች፡፡ ..ተፈጥሮን በቁጥጥራችን ስር እናደርጋለን.. የሚለውን መሠረታዊ እምነትም በልዩ ልዩ መፈክር ያስተጋቡ ነበር፡፡ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ የአድሀርያንን (እና የጭቁኑን ሰፊ ህዝብ ሃይማኖት በሚመለከት የሚከተለውን የሚመሳስሉ አያሌ ቀልዶች (jokes) ያሰራጩ ነበር፡፡kM{tÜ ሰም ስር የሚገኘው ወርቅ ..በምድር ላይ ገነትን እንዘረጋለን፡፡ ከፈለግንም በትግል መንግሥተ ሰማይን በቁጥጥራችን ስር እናደርጋለን.. ነው””kmNGot ሰማያትና ከገሀነም በእኩል ርቀት ላይ ሰባት light years ከተጓዝክ በኋላ ዘጠነኛው galaxy ትደርሳለህ፡፡ እዚያ ምድራችንን የምትመስል አለም አለች፡፡ እዚያ ..አለም ዘጠኝ ጠጅ ቤት.. በወር አንድ ጊዜ (በልደታ ቀን) ኢየሱስና ሳጥናኤል እየተገናኙ፣ ጠጅ እየተገባበዙ እያወሩ ተዝናንተው ሲያበቁ፣ ወደ የመኖሪያቸው ይመለሳሉ፡፡
አንድ ቀን ሳጥናኤል በደራው ጨዋታቸው ላይ ሰባተኛዋን ብርሌ ጨለጠ፡፡ ፊቱ ጭፍግግ ብሎ ራሱን እየወዘወዘ ..አልቻልኩም!.. አለ በምሬት ..ይሄ ጓድ ሌኒን የሚሉት መላጣ ሀከተኛ ..ፓርቲ.. የሚባል ፖለቲካዊ ማህበር አቋቁሞ ሲበጠብጠን እንዴት ሥራችንን መሥራት እንችላለን!? ንገረኝ እስቲ!..
..ረጋ በል፣ ወንድም ሳጥናኤል.. አለ ኢየሱስ ..ከሦስት ቀን በኋላ ወደኛ ዓለም እናዛውረዋለን..
..እንደ ትልቅ ውለታ እቆጥረዋለሁ፡፡ አንተንማ ከኔ የባሰ ሳያደናቅፍህ አይቀርም..
..አታስብ፡፡ ሰው ስለሆንኩ ከሌኒን ጋር መግባባት እችላለሁ፡፡ ለመሆኑ ይሁዳስ እንዴት ነው?..
..ትጉህ ሠራተኛ! እንዲህ ከቀጠለ አንድ ቀን ገንዘብ ሚኒስትራችን ይሆናል... . .
. . .በገሀነም ካሌንደር ስንቆጥር ሰባት ዓመት አለፈ፡፡ ኢየሱስና ሳጥናኤል እየጠጡ ሲጫወቱ ቆይተዋል፡፡ Chess ግጥምያቸው ትኩረታቸውን በሙሉ ስቦታል፡፡
ከረዥም ዝምታ በኋላ ሳጥናኤል ጨዋታ ለመጀመር ያህል ..ከጓድ ሌኒን ጋር ግንኙነታችሁ ዛሬም ሰላማዊ ነው?.. ጠየቀ፡፡
ኢየሱስ ሂሳባቸውን ለመክፈል ቦርሳውን እያወጣ ..ይቅርታ ወንድም ሳጥናኤል.. አለ ..ጨዋታችንን ማቋረጥ ሊኖርብን ነው..
..ምነው?..
..ይሄ ቼዝ ጨዋታችን አስረስቶኝ ነው እንጂ የፓርቲ ስብሰባ ሰዓት ደርሶብኛል.. ብሎ ተሰናበተው፡፡
እስከሚቀጥለው ቸር ይግጠመን!

 

Read 3274 times Last modified on Saturday, 27 August 2011 13:14