ሲንቄ ባንክ፤ የሲንቄ ኢንቨስትመንት ባንክን ለማቋቋምና የድርጅት ስትራቴጂን፣ ተግባራዊ ስትራቴጂን እንዲሁም የሂደትና ዳግም የማወቀርያ ድርጅታዊ ዲዛይንን ለማዳበር የሚያግዝ የምክር አገልግሎት ለማግኘት ከዴሎይት ጋር ስምምነት ተፈራረመ።
የፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ከትላንት በስቲያ ማክሰኞ ታህሳስ 8 ቀን 2017 ዓ.ም በሒልተን አዲስ ሆቴል መካሄዱ ታውቋል፡፡
የስምምነት ውሉን የተፈራረሙት የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ነዋይ መገርሳና የአጋር ዴሎይት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ አማካሪ ድርጅት መሪ የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ሲሳይ ሲሆኑ፤ በሥነስርዓቱ ላይ የባንኩ ከፍተኛ አመራር፣ እንዲሁም የምስራቅ አፍሪካ የሰብአዊ ካፒታል ሊድ ዳይሬክተር የሆኑት የዴሎይት ማኔጅመንት ዶ/ር ፖል ኦካቴጅ ተገኝተዋል፡፡

